spot_img
Saturday, November 25, 2023
Homeአበይት ዜናየባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም እንደቀደሙት አባቶቻቸው ቆፍጣና ስራ ሰሩ

የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም እንደቀደሙት አባቶቻቸው ቆፍጣና ስራ ሰሩ

advertisement

መስከረም 17 2209 ዓ ም

የባህር ዳር ሃገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም ፎቶ ፤ ወንጌል ቲዮብ
የባህር ዳር ሃገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም
ፎቶ ፤ ወንጌል ቲዮብ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ለዓመታት በገዥው ቡድን ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር እንደወደቀ ፤ መንፈሳዊ ግልጋሎት ከመስጠት በላቀ ሁኔታ በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ቅጥ ባጣ አኳኋን እያገለገለ እንዳለ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው። ከዚያው ጋር ተያይዞ የሲኖዶሱ አባላት በአመዛኙ ወይ በፍርሃት ወይ በፖለቲካ የጥቅም ትስስር ተተብትው በኢትዮጵያውያን ላይ ተደጋጋሚ ግፉ ሲደርስ ድምጻቸውን ባለማሰማታቸው ብዙ ትዝብት እና ወቀሳ አትርፈዋል።

በዛሬው የመስቀል አከባበር የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አምርሃም ታሪክ የሚዘክረው አኩሪ ስራ እንደሰሩ ከአካባቢው የመረጃ ምንጭ ዋቢ ያደረጉ የማህበራዊ ድረ ገጽ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ባለስልጣኖች እና የስርዓቱ ወታደራዊ ኃላፊዎች ጭምር ተገኙበት በተባለው በዚሁ በዓል ላይ አቡነ አብርሃም የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል ፤

«ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም ፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?፤ መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዩ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ»

ንግግራቸውን ተሰብስቦ የነበረው ምዕመን በእልልታ እንዳስተጋባው ታውቋል። በበዓሉም በግፍ ህይወታቸውን ለተነጠቁ ጽሎት ተደርጓል።

በመጨረሻም አቡነ አብርሃም ህዝቡ ወደ ቤቱ ሳይገባ በፊት አልሄድም በማለት ፤ ህዝቡ ከተበተነ በኋላ በእግራቸው ወደ ባዕታቸው ገብተዋል። አቡነ አብርሃም በእግራቸው ሲሄዱ የክልሉን ፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ ኃይሎች በመኪና እንዳጀቧቸውም ታውቋል።
**
ካነበቡ በኋላ ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ። ይሄንን ይጫኑ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here