spot_img
Wednesday, March 22, 2023
Homeዜናበባህር ዳር አንድ የአጋዚ ወታደር በጩቤ ተወግቶ ተገደለ

በባህር ዳር አንድ የአጋዚ ወታደር በጩቤ ተወግቶ ተገደለ

- Advertisement -

መስከረም 21 2016

በማህበራዊ ድረ ገጽ ስለ አማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ መረጃ እና ሃሳብ በማካፈል የሚታወቀው አቻምየለህ ታምሩ በፌስ ቡክ ገጹ እንዳጋራው ዛሬ በባህር ዳር አንድ የፌደራል ፖሊስ በጩቤ ተወግቶ ተገድሏል። ስለ ተገደለበት ሁኔታ ያቀረበው መረጃ ከታች ያለው ነው።

ባህርዳር ጥግ ጢስ አባይ ቀበሌ ውስጥ አንድ የፋሽት ወያኔ ነፍሰ በላ አጋዚ ሁለት ሰላማዊ የአማራ ወጣቶችን «ህዝቡን ትቀሰቅሳላችሁ» በማለት እየደበደበ ወደ ባህር ዳር በታክሲ አጋብቶ «ወደ ብርሸለቆ ትሄዳላችሁ» በማለት በመውሰድ ላይ ሳለ፤ ቀድሞ ከታክሲው የተሳፈረ ይሁን በኋላ ወደ ወደ ታክሲው የተሳፈረ መሆኑ ያልታወቀ አንድ ወጣት አጋዚውን በጩቤ አንገቱ ስር በመውጋት መሳሪያውን ቀምቶ ሁለቱን ወጣቶች በማስለቀቅ መኪናውን አስቁሞ ሁለቱን ወጣቶች ይዞ በመውረድ አብሯቸው ካካባቢው ተሰውሯል። በፖሊስ ሲያዝ «ህግ ቦታ ውሰዱኝ» ማለትን ባህሉ አድርጎ የኖረው ሰላም ወዳዱ ህዝብ፤ ህግ ስለሌላ፣ ፍትህ ስለጠፋ፤ እስር ቤት ቢገባ በእሳት መንደድና ገላው በትግራይ ወታደሮች መተልተል መሆኑን የተገነዘበው ወጣት ራሱን እየተከላከለ ይገኛል። ግፈናው አገዛዝ የአዋቂዎችን ምክር፣ የአገር ሽማግሌዎችን ተግሳጽና የሚመለከታቸውን ሁሉ ጩኸት ባለመሰማቱ ሰላማዊ ትግል ታፍኖ ነገሮች ወደዚህ እንደሚያመሩ አድርጓቸዋል። የፖሊሱ አስከሬን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ለቀብር ተልኳል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,440FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here