አንጋፋው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ ኢንጂነት ኃይሉ ሻውል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ

መስከረም 27 2008 ዓ ም

hailu-shawul
ኃይሉ ሻውል የቅንጂት መሪ በነበሩበት ወቅት

አንጋፋው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ከዚህ ዓለም በሞት እንተደለዮ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ቅርበት አላቸው ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል። እንደዘገባው የኃይሉ ሻውል ያረፉት ህክምና እየተከታተሉ በነበረበት በታይላይድ ነው።

ቀደም ሲል በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በተመሰረው የመላው አማራ ሕዝቡ ድርጂት ያገለገሉት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል በኋላም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ሲመሰረት ቁልፍ ሚና የነበራቸው እና ድርጂቱንም ለረዥም ጊዜ የመሩ ነበሩ።

በ97 ምርጫ ፓርቲውን ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በማቀናጀት ቅንጂት ፓርቲን ለመመስረት ከታገሉት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው። ቅንጂት ከተመሰረተም በኋላ በሊቀመንበርነት መርተውታል።

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በበላይነት የሚያሽከረክረው የኢህአዴግ ፖርቲ ተሸንፎበታል የተባለውን የምርጫ ውጤት ቀልብሶ በመላ ኢትዮጵያ ሁከት ከተቀሰቀሰ እና ብዙ ዜጎች “አደገኛ ቦዘኔ” በሚል ከተገደሉ በኋላ ፤ ኃይሉ ሻውል ከሌሎች የቅንጂት አመራሮች ጋር ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል።

እንግዲህ እንደሚባለው (የአሜሪካ ድምጽም ዘግቦታል)ኢንጂነት ኃይሉ ሻውል ገመምተኛ የሆኑት በእስር ቤት የነበረው አያያዝ በጤንነታቸው ላይ ጉዳት ካስከተለ በኋላ ነው ። ላለፉት ሁለት ዓመታት ህመም በርትቶባቸው ህክምና ይከተታሉ እንደነበርም ታውቋል።

የኢንጂነር ኃይሉ ሻውል አስከሬን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገባ የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ዘገባ ይጠቁማል።

በህይወት ዘመናቸው ኃይሉ ሻውል እንደ ማንኛው ፖለቲከኛ ወቃሾች ቢኖሯቸውም(በተለይ ፓርቲያቸው ከመንግስት ጋር አደረገ በተባለው ስምምበት ጋር በተያያዘ) ፤ እጂግ በርካታ ደጋፊዎችም የነበሯቸው ቁርጠኛ ፤ የአርበኝነት መንፈስ ያላቸው እና ኢትዮጵያን አብዝተው የሚወዱ እንደነበሩ ይነገራል። በማደራጀት እና በመምራት ችሎታቸውም ይመሰገናሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.