spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትየነጃዋር ቡድን ሸፍጥ እና መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ

የነጃዋር ቡድን ሸፍጥ እና መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ

advertisement

መስከረም 28 2009 ዓ ም

ትኩረታችን ወያኔ ላይ ይሁን የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በዚህ ሂደት የሚስተዋሉ ምናልባትም በኋላ የከፋ ችግር የሚፈጥሩ ነገሮች እየነቀሱ ማስታወሱ ተገቢና አስፈላጊ ነው።
የጃዋር እና ከበስከጀርባው ያለው ጽንፈኛ ቡድንም የሚሰራውን ሸፍጥ እና ያለውን እኩይ አላማ ማስታወስ የሚያስፈልገው በዚህ ምክንያት ነው።

የኦሮሚያ የሽግግር መንግስት ምስረታን ጨምሮ ስለ ዘር ተኮር ቻርተር ፤ ወታደርና ሌሎች ተቋማት ግንባታ የተናገሩት በስህተት ወይ ከአተረጓጎም ችግር ነው ብሎ የሚያምን ሰው ካለ እውነታውን ማየት የማይፈልግ ሰው ነው። ይሄንን እቅዳቸውን ይፋ ሲያደርጉ ፤ በተመሳሳይ ጊዜ “የኦሮሞ አብዮት”የሚል የበይነ መረብ ዘመቻ መጀመራቸውን ልብ ይሏል።

የቢቢኤን ሬዲዮ ጃዋር ጉዳዮን እንዲያብራራ ጠይቆት ነበር፤ ለማስተባባል በሚያደርገው ጥረት እንኳን እየደጋገመ ሳያስበው የሚያመልጠው የጽንፈኝነቱ ነገር ነው። ኦሮሞ ይልና ጎረቤቶቹ ይላል። ሌሎች ሀገሮች ያለበትም አገባብ አለ። ማነው የኦሮሞ ጎረቤት? ወቅቱ የሚጠይቀው ፤ ህዝቡም እየጠየቀ ያለው አንድነት ሆኖ እያለ ፤ ልዮነትን የሚያስረግጥ ቻርተር እየተካለቡ በአጀንዳነት ማቅረብ ምናልባትም ይሄ ቡድን ያመልጠኛል ብሎ ያሰበው ነገር እንዳለ የሚጠቁም ይመስለኛል። ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ወደ አንደነት ጎራ ከገባ ፤ የነሱ የጎጥ ፖለቲካ ውሃ ሊበላው ነው።

በብሄር እንደራጅ የሚሉ ድርጂቶች ህዝባዊ ትግልን እስከማምከን ድረስ የሚሄዱ ከሆነ “በመብታቸው ነው” ሂሳብ እና በይሉኝታ ዝም መባል የለባቸውም። በሌላ በኩል ግን በአባልነት ባንሳተፍ እንኳ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድርጂቶች የሚያስፈልገውን እና የሚቻለውን እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል። በበኩሌ ለምሳሌ የአማራ ተጋድሎ ተብሎ የተነሳው ዘመቻ ሙሉ በሙሉ ደጋፊ ነኝ። ምክንያት በኢትዮጵያ ህልውናም ይሁን በህዝባዊ ትግል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደማያሳድር እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው። በአንጻሩ ደሞ የነጃዋርን ቡድን በሚሰዋልበት የተምታታ እና ግልጽነት የጎደለው አካሄድ ሙሉ በሙሉ እቃወማለሁ ፤ ከጽንፈኝነት የተጣባ አፍራሽ ተልዕኮ ያለው ፤ ነገሮች ባሰበው መንገድ ቢመቻቹለት ከህወሓት የማይተናነስ ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን እንደሆነ በእርግጠኝነት ስለማውቅ ነው።

የነጃዋር ቡድን አመታት ያስቆጠረውን የሃገር ውስጡንም ፤ የዓለም አቀፉንም ዘመቻቸውን (የበይነ መረብ ፤ የዲፕሎማሲ ፤ እና ሌሎች ጉዳዮች) የቀረጹት የጎሳ ፖለቲካቸው “ፍትሃዊ” እና ብቸኛ መፍትሄ በሚያስመስል መልኩ ነው። በዛ መልክም በዓለማቀፍ መድረክ ጭምር ተቀባይነት ያገኘ ይመስላል።

ስለነገድ ችግሮች ይወራ ከተባለ እውነት ለመናገር በህወሓት አስተዳደር ዘመን እንደ አማራ ህዝብ ጥቃት የደረሰበት የለም። ይሄ ማስረጃ ያለው ጉዳይ ነው። የጥቃቱ ልክ ግን እንኳን በዓለም ዓቀፉ መድረክ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንኳን በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ አልተፈጠረም። አንድም በቅንጂት እና ትኩረት እና ትጋት ማጣት ችግር ምክንያት ። አንድም ደሞ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን ችግር ከማንጸባረቅ አንጻር በአማራ ላይ የደረሰው ጥቃት የመዝለል እና አይቶ የማለፍ ዝብባሌ ስለነበረ። ዛሬ እነጃዋር በአዲስ ጉልበት ያነሱት ሪዮት ራሱ ከወያኔ እኩል በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ለማድረስ መሳሪያ ሆኗል። ለረዠም ዘመን ስንሰማ የነበረው ነጠላ ዜማ ግን የወያኔ ሰው “የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ኦሮሚኛ ይናገራሉ” ያለውን ነበር። ትክክል ነው ወያኔ እና ኦነግ ከተጣሉ በኋላ ብዙ ኦሮሞዎች በኦነግ ስም በወያኔ ተጠቅተዋል። ወያኔ እንደዛ ያደረገበት አንደኛው ምክንያት የኦሮሞን የጎሳ አስተሳሰብ ለማጠንከር እና በተለይ አዲስ በሚወጣው ትውልድ ጸረ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ ከመቅረጽ አንጻር ጥቅም ይኖረዋል ብሎ ስለገመተ ነው። ዛሬ ለወያኔም ለራሱ ተመልሶ የጉሮሮ ላይ አጥነት ሆነበት እንጅ። ስለ እውነት ሲባል መናገር ካለብን ባለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያ ለአማራው ከእስር ቤትነት ባለፈ የግፍ ጽዋ የተቀበለባት ሆናለች። አማራው እስር ቤት አልታሰረም። ኢትዮጵያ ሰፊ እስር ቤት ሆናበታለች። ህጻናት ልጆቹ ሳይቀሩ ታርደውባታል። እንደ አማራ ጥቃት የደረሰበት እንደሌለ ግልጽ ነው።

አሁንም ጥያቄው ለምን የችግሩ መጠን በዓለም ዓቀፍ እና በሃገር ውስጥ በሚገባው ደረጃ አልታወቀም?አማራ ቢደራጂ ራሱ የአረብ ሃገሮች እንደነ ጃዋር እና ወያኔ ያለውን ቡድን ለመርዳት እንደተሯሯጡት ሳይሆን ፤ እንዲያውም ጥፋት እንደሚደግሱለት መገመት ከባድ አይደለም። ወያኔ እና ሱዳን እኮ ወታደራዊ የድንበር ላይ ስምምነት ሲፈራረሙ ታሳቢ ያደረጉት የነጃዋርን ቡድን አይደለም!መሬት ሁሉ ከኢትዮጵያ ተቆርሶ ለሱዳን ተሰጥቷል። በቡዙ ሚሊየን የሚቆጠር አማራ ራሱን እና ቤተሰቡን ሳይመግብ በችግር እየኖረ የተጠላበት እና በዛ ላይ የሚጠቃበት ወንጀሉ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ ወንጀሉ ኢትዮጵያዊነት ነው።

የጽንፈኛው ኦሮሞ ቡድን በዓለም ዓቀፍ መድረክ (ሜዲያ ተቋማትን ጨምሮ )እና ሀገር ቤትም በግራስ ሩት ደረጃ ለመቀስቀስ እና ለማደራጀት የተጠቀመውን ሞዴል በጥንቃቄ ማጥናት ያስፈልጋል። (በነገራችን ላይ እንደ African Argument ያሉ ድረ ገጾች ግብ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ነው?) ብዙ አይነት ስትራቴጂ ተጠቅመዋል። በማህበራዊ ድረ ገጽ እንኳን የተለያየ አካሄዶችን ተጠቅመዋል። ለኢትዮጵያ ያገባናል ግድ ይለናል የምንል ሰዎች ግን ባብዛኛው የሚስተዋልብን ያልቀናጀ ፤ አንዳንዴም ግብታዊ አጠቃቀም ነው። ከነጭራሹ “ፖለቲካ በሩቅ” እያለም ነገሩን ወደጎን ይገፋ የነበረውም ቀላል ቁጥር ያለው ሰው አይደለም። ፖለቲካ የማይነካው ማህበረሰባዊ ገጽታ ያለ ይመስል። አሁንም ቢሆን ከጃዋር እና እሱ ከሚወክላቸው ቡድን ጋር ያለው ግንኙነት ሁኔታ ይመርመር፤ ጥርቅም አድርጎ በሩን ለመዝጋት ፍላጎት ከሌለ ቢያንስ ራሳቸው ከፍተው እንዲገቡ በሩ ይዘጋባቸው። በአንጻሩ ደሞ እንደ ኦሮሞነታቸው ሁሉ ኢትዮጵያዊነቷቸውን የሚያከብሩትን እና የሚፈልጉትን ደሞ ድጋፍ ይደረግላቸው፤ ከእነሱ ጋር ለመስራትም ሁኔታዎች ይመቻቹ።

ጸሃፊውን ድሜጥሮስ ብርቁን በፌስ ቡክ ላይ ለማግኘት ይሄንን ይጫኑ።

_____
ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ ፤ ካነበቡ በኋላ ያጋሩ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here