መስከረም 29 2009 ዓ ም
ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። አዋጁ የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው የተባለ ሲሆን ፤ ይፋ የሆነው አዋጁ በስራ ላይ መዋል ከጀመረ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
እንደ ፌደራል አቃቢ ህግ ማብራሪያ አዋጁ የወጣው የህገመንግስቱን አንቀጽ 93 ተገን አድርጎ ሲሆን ፤ በስራ ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ6 ወር ሊበልጥም ሊያንስም ይችላል ተብሏል። አዋጁን የሚያስፈጽመው የተቋቋመ “ኮማንድ ፖስት” ሲሆን ኃይለማርያም ደሳለኝ ይመሩታል ተብሏል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ የሚተገበርባቸው ቦታዎችንም የሚወስነው በኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው ኮማንድ ፖስት ነው ተብሏል።
አዋጁን ባጠቃላይ ስምንት ዋና ዋና የሰብአዊ ፤ የፖለቲካ እና የሲቪክ መንቶችን ይገድባል። “ለህግ አስከባሪ ተቋማት” “ህግ የሚያስከብሩበት ስልጣን” ተጨምሯል። ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመኖሪያ ቤቶችን ሊበረብሩ ይችላሉ፤ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ያለ ማስረጃ ዜጎችን ለማሰር ይችላሉ፤ መኪናንም ሆነ ግለሰቦችን በድንገት በማስቆም ይፈትሻሉ። በተጨማሪም ስልክን ጨምሮ ማንኛውም አይነት የመገናኛ ዘዴዎችን የመዝጋት ፤ የመዝመሰበሰብ እና መሰለፍ እንዲሁም በቡድን ሆኖ መሄድ የመከልከል ስልጣን አለው። የሰዓት እላፊ ገደብም ተጥሏል።
በአማራ እና ኦሮሚያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳይወጣ ከረዥም ጊዜ በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ። ከወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ ጋር በተያያዘ ዋናው የዜጎች ስጋት ፤ ምንም አይነት የህግ አገባብ ሳይገድበው ዜጎችን እንደፈለገ በአጋዚ ሰራዊት ሲያስገድል የነበረው ምንም አይነት ተቀባይነት የሌለው የህወሓት መንግስት ፤ ህጉን ለብቀላ ሊጠቀምበት ይቻላል ፤ የበለጠ የንጹሃን ዜጎች ይህወት ይቀጠፋል። አልፎም ወደ ጂምላ ፍጂት የሚያስገቡ ሁኔታዎችን ሊፈጥርበት ይችላል የሚል ስጋት አለ።
አንዳንዶች ደሞ የህወሓት ሰዎች የዘረፉትን ንብረት እና ሃብት ለማሸሽ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ በስተቀር የህዝቡ ጥያቄ የለውጥ ጥያቄ ነው ህወሓት ሃያ አምስት ዓመት ሳይቀየት በስድስት ወር የሚቀየርበት ተዓምር የለም ይላሉ።