spot_img
Saturday, May 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትህወሓት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ይፋ ያደረጋቸው የጥገናዊ ለውጥ እቅዶቹ እና...

ህወሓት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ይፋ ያደረጋቸው የጥገናዊ ለውጥ እቅዶቹ እና ችግሮቻቸው

መስከረም 30 2009 ዓ ም

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ በታወጀ ማግስት የህወሓት መንግስት የጥገናዊ ለውጥ ፖሊሲ ርምጃዎች እድቅ የሚመስል ነገር ይፋ አድርጓል።እቅዶቹ ሁሉ የሚጠቁሙት ግን ህወሓት የህዝብን ጥያቄ ማዳመጥ እንዳልፈለገ ነው።

ወጣቱን በሚመለከት የ10 ቢሊዮን ብር ስራ ፈጠራ (ጥቃቅን እና አነስተኛ መሆኑ ነው ሌላ ሊሆን አይችልም) ይፋ አድርጓል። ምናልባትም በቀጣይነት ተጨማሪ የካድሬ መመልመያ መሳሪያ ሊያደርገው ይችላል ፤ ህወሓት ብርቱ የማሰብ እና ስልጣን ማስጠበቅን ከሃገር ህልውና እና ከብሄራዊ ጥቅም በላይ አድርጎ የማየት ችግር ስላለበት። የወጣቱ ጥያቄ ግን የዜግነት ክብር እና የሃገር ባለቤትነት ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎቹ ሲመለሱ ፖለቲካ ወገንተኝነት ሳያስፈልገው በዜግነቱ እና በችሎታው ብቻ እንደዜጋ ሰርቶ ሀገሩንም ሆነ ራሱን መጥቀም ይችላል።

ከእቅዱ ሌላ አንኳር የሚመስለኝ ነገር “የፌደራል መንግስትን በአዲስ መልክና ቅኝት ለማዋቀር ተግባራዊ እርምጃ ይወሰዳል” ያሉት ነው። “አዲስ መልክ እና ቅኝት” ማለት ምን ማለት ነው? አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር ይቀየራል? ያ ከሆነ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት የህወሓት ስልጣን በአየር ላይ ይሆናል (ምናልባትም ትራይን በማይነካ መልኩ ካላደረጉት በስተቀር፤ ለነገሩ በተፈለገው አይነት አወቃቀር ቢዋቀር ትግራይ ትግራይ ሆኖ ነው የሚቀረው ሌላ ነገር መሆን አይችልም። ያንን ታሳቢ ካደረጉ አንድ ነገር ነው። )ያ ከሆነ ፤ ከዚያው ጎን ለጎን የነሱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ተቃዋሚ በጎን አደራጅተው ፤ የፖለቲካ ምህዳር ከፍተናል በማለት ቢያንስ የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን እንዳስጠበቁ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ተመክረው ይሆናል።

በሌላ አንጻር ደሞ የፌደራል መዋቅሩን መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ እንደማይቀይሩት ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ይፋ አድርገዋል። “የኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያለው ልዩ ጥቅም ለመደንገግ የሚወጣውን አዋጅ ጨምሮ ሌሎች በርካታ አዋጆች በያዝነው አመት ይወጣሉ” ብለዋል። መልዕክታቸው ለኦነግም ይመስላል። የፌደራል መዋቅሩ ከሚፈርስብህ ፤ በአዲስ አበባ ላይ ያለህ ጥያቄ ይመለስልህና ፤ ገብተህ “ህጋዊ ተቃዋሚ ሆነህ” ትሰራለህ አትሰራም አይነት መልዕክት ነው። ያው ሲገባላቸው ፤ እግዜር ይስጥህ ብለው ስራቸውን ይሰራሉ። ኦነግም አይተርፉም ከዚያ በኋላ። በኢትዮጵያ የግብጽ አምባሳደር አዲሳባ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተጠርቶ “ጣልቃገብነት” እንዲያቆሙ እንደተነገራቸው ተሰምቷል። ከዚያ ጋር ተያይዞ ፤ ኦነግ ጋር ልታደራድረኝ ትችላለህ ወይ የሚል መልዕክት ለግብጽ መንግስት የሚነሳ ይመስለኛል። ግብጽም በኦነግ በኩል የማይሳካ ከሆነ ወያኔም ራሱ ከኦነግ ብዙ የሚርቅ ስላልሆነ ገላጋይ መስላ ለመግባት አታመነታ ይሆናል። ከአሜሪካ ጋር የሚያላትም ሌላ የራሷም ጉዳይ መጥቶባታል።

ያልተፈቱ የማንነት ጥያቄዎችንም እፈታለሁ ያለው ፤ ድንግርግር ያለ ነገር ነው። እንደሚታወቀው ለምሳሌ የወልቃይቱ ፤ የራያው ነገር በወያኔ በራሱ የተፈጠረ ችግር ነው። አባይ ወልዱን አነሳ ተባለ። ከዛስ? ምናልባት አዲስ የፌደራላዊ አወቃቀር የተባለው በዚህ አካባቢ ተግባራዊ የሚሆን ሊሆንም ይችላል። እሱም ቢሆን በተወሰነ መልኩ በፊት ከወሰዱት መሬት ላይ በተወሰነ መልኩ እንዲያስቀር አድርገው ስለሚያዋቅሩ ፤ ወይንም ወልቃይት እና ራያን ልዮ ዞን በማድረግ ተጸዕኗቸውን ማስቀጠል ፈልገው ይሆናል።
ባጭሩ ወያኔ የተነሳውን የለውጥ ጥያቄ በዚህ መልክ ይረግብ ከሆነ ለመሞከር ነው የፈለገው፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም በሚፈልግነት ቦታ የመገናኛ ዘዴዎችን በማፈን በሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደሚያደርስ ምንም ጥርጥር የለውም።

ጥያቄው የለውጥ እንጂ ፤ የጥገናዊ ለውጥ አይደለም። ሃያ አምስት አመት ታይቶ ፤ በስተመጨረሻ ከዘረፋ ባሻገር ክፍፍል እና ጥላቻን የዘራ መንግስት ውረድ ማለት ፍጹም ፍትሃዊ ነው። የህዝባዊነት መርህ ትልቁ ነገር ፤ የህዝብን ጥቅም አስቀድሞ ለህዝብ ፍላጎት መገዛት ነው። ወያኔ “ጸረ ሰላም ኃይሎች” እያለ ራሱን እና ምናልባት ብዥ ያለባቸውን የራሱን አባሎች እና የጥቅም ተካፋዮች ያታልል ካልሆነ በስተቀር ማንንም አያታልልም። የለውጥ ጥያቄው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ በወያኔ ምናብ ውስጥ ያሉ “ጸረ ሰላም” ኃይሎች አይደለም።

ይፋ ከሆነው እቅድ በመነሳት ኦነግ ማድረግ ያለበት ብቸኛ ነገር ፤ እሱም እንደወያኔ የሚያደርገውን ድንግዝግስ ያለ ስትራቴጂካዊ የ“ህብረት” አካሄዱን ፤ በሃቀኛ እና በእውነት ላይ በተመሰረተ መርህ ላይ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ( ለምሳሌ በግንቦት ሰባት ጋር ሊሰራ ይቻላል)አብሮ በመስራ ፤ ጉልበት ያለው ቅንጂት ፈጥሮ ትግሉን ማፋፋም ነው። ያለበለዚያ በደጋፊዎቹ እንኳን በራሱ በሂደት ከወያኔ የበለጠ የተቀባይነት ኪሳራ የሚደርስበት ድርጂት ቢኖር ኦነግ ነው። በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለህን አቋም ግልጽ አድርግ ፤ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እስከታች እስከ ግራስ ሩት ድረስ ግንዛቤ ፍጠር። ከዚያ በኋላ ወያኔን በየቦታው መቅብር ይቻላል።

ከድሜጥሮስ ብርቁ

—————————
ካነበቡ በኋላ ያጋሩ ። ቦርካናን በፌስ ቡክ ላይ ላይክ ያርድጉ። ይሄን ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here