spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeዜናበየመን እስር ቤት ታስረው የነበሩ ወደ 1ሺ የሚጠጉ...

በየመን እስር ቤት ታስረው የነበሩ ወደ 1ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ባልታወቁ ሃይሎች መለቀቃቸው ተገለጸ (ኢሳት)

advertisement

ኢሳት
ጥቅምት 3 2009 ዓ ም

በሰሜን የመን በሚገኝ አንድ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ ወደ 1ሺ አካባቢ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ከእስር ቤት እንዲወጡ ተደርጎ ወደ ሌላ ግዛት መወሰዳቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት ሃሙስ ይፋ አደረጉ።

አታክ በሚባል ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሻብዋ ከተማ እስር ቤት የነበሩት ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ የተቀነባበረ የማስመለጥ ድርጊት እንደተፈጸመባቸውና እስረኞቹ በሙሉ በተሽከርካሪ ወደ ሌላ ግዛት መወሰዳቸውን አል አረቢ የተሰኘ የየመን ጋዜጣ የደህንነት ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

በእስር ቤቱ የነበሩ 1ሺ 400 አካባቢ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን በህገወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሃገሪቱ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የነበሩ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኑ ከእስር ቤት ያስመለጠው አካል አልታወቀም።

አንድ ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከእስር ቤቱ እንዲያመልጡ ከተደረገ በኋላ ማሪብ እና ባይዳ ወደተባለ ግዛት መሄዳቸውን የደህንነት ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

በየመን የሚገኙት የሃቲ አማጺያን ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን በመመልመል ለውጊያ እንደሚጠቀሟቸው አል-አረቢያ ጊዜጣ በዘገባው አመልክቷል።

ይሁንና፣ ከእስር ቤት በተቀነባበረ ሁኔታ አምልጠዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን ለዚሁ ድርጊት ይወሰዱ አልያም ለሌላ ተግባር የተገለጸ ነገር የለም።
የሁቲ አማጽያን የየመን መዲና ሰንዓ ከተማን ጨምሮ አብዛኛውን የሃገሪቱ ክፍል ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ታውቋል።

ወደ አንድ ሺ የሚጠጉት ኢትዮጵያውያን ሄደውበታል የተባለው የባይዳ ግዛት በአልቃይዳ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኑ ወደዚሁ ግዛት የተወሰዱበት ምክንያት በተመለከተ የየመን ባለስልጣናት ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ጦርነት እልባት ወደአላገኘበት የመን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን በመሰደድ ላይ እንደነበሩና ድርጊቱ ስጋትን ማሳሰሩን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ይገልጻል።
በፈረጆቹ 2015 ዓም ብቻ ወደ 80ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የመን መግባታቸውንም የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።

ባለፈው ወር አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ 220 ስደተኞቹን የየመን ባለስልጣናት ወደየሃገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በየመን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸው ይነገራል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here