ጥቅምት 3 2009 ዓ ም

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተክትሎ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በተለያዮ አካባቢዎች በተለይም በጎንደር እና በጎጃም ጦርነት የሚመስል ነገር እንዳፋፋመ ይታወቃል። ዓላማው ትጥቅ ማስፈታት እና የህልውና እና የማንነት ጥያቄ ያነሳውን አማራውን ወደ ፍጹም ባርነት የመቀየር ምኞት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።
ትላንት በማህበራዊ ሚዲያ በወጣ መረጃ በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ ዶጋው አካባቢም 5ኛ ተወርዋሪ የሚባለው የወያኔ ጦር ጦርነት ከፍቶ እንደነበር ታውቋል። በአካባቢው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አበራ ጎባው በመባል የሚታወቀው ጀግና አስራ አምስት የሚደርሱ የህወሓትን ወታደሮች ገድሎ ተሰውቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጀግናው ኮሎኔል ደመቀ የምርመራ ፋይሎች እንደተዘጉ ጠበቃው መከተ ካሳሁን ከኢሳት ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ ማወቅ ተችሏል። የተከፈቱት የምርመራ ፋይሎች ነብስ በማጥፋት እና በሽብርተኛነት በሚል ሲሆን የመጀመሪያው ፋይል ላይ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ተዘግቶ ለአቃቢ ህግ ተላልፏል። አቃቢ ህግ መረጃው እንደተላከት በ15 ቀናት ውስጥ ክስ መመስረት የነበረበት ሲሆን ፤ ያንን አላደረገም። የሽብርተኛነት ፋይሉ በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መታየት የማይችል ነው በማለት እሱም ተዘግቷል።
—————————
ቦርከናን ላይክ ማድረግ አይርሱ።