spot_img
Wednesday, March 22, 2023
Homeነፃ አስተያየትኢአአግ ቱዋት ፖልና የህወሓት የማሞኛ ዲስኩር-ክፍል 2

ኢአአግ ቱዋት ፖልና የህወሓት የማሞኛ ዲስኩር-ክፍል 2

- Advertisement -

ከዓለማየሁ መላኩ
ህዳር 3 2009 ዓ ም

ባለፈው በክፍል አንድ አጭር ማስታወሻ ስለ ቱዋት ፖልና የኢአአግ ምንነት ፤ አመሰራረት እና መክሰም መግለጤ ይታወሳል። በዚህ በክፍል ሁለት ማስታወሻ ስለቱዋት መሰሪ ተክለ ሰውነት እና ሞቶ ስለተቀበረውና በስሙ ብቻ ስለሚነግድበት ኢአአግ ትንሽ እውነት ለማቅረብ እወዳለሁ።

ባለፈው በጥቂቱ እንደገለጽኩት ቱዋት ፤ የሱዳን ጉዞ እና ትግሉ ፤ ለጄኔራል ኃይሌ መለስ መታሰርና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ፤ የሃሰን አልባሺር መንግስትና የመለስ ግንኙነት ፤ ጠንክሮ በመታየቱ ኢአአግ/ከፋኝ ፤ የኃየሊ መለስ ክንፍና የመድህን ጎሹ ወልዴ ህብረት ግንባር በመፍረሱ ፤ ቱዋት ባለው የስልጣን ጥማት የድርጂቱን ሊቀመንበር የቀደሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም እና አቶ ካሳ ከበደን ከኢአአግ አባርሬ እኔ ሊ/መንበር ሆኛለሁ ብሎ ቀደም ሲል በጋምቤላ ያሰባሰባቸውን የስጋ ዘመዶቹንና ከካኩማ የስደተኞች ካምፕ ወደ ሱዳን የዘመቱ በጣም ጥቂት ከአምስት የማይበልጡ ስደተኞችን በማወናበድ ወደ ኬኒያ ከመለሰ በኋላ ፤ በኬኒያ የኤርትራ አምባሳደር ጋር በመነጋገር የይለፍ ወረቀት ከተዘጋጀለት በኋላ ወደ ኤርትራ ይጓዛል። እዚህ ላይ ለአንባቢያን ማስታወስ የምወደው ነገር ቢኖር ቱዋት ሁኔታዎች ከተበላሹ በኋላ ከካርቱም እንዴት ወጥቶ ተመልሶ ወደ ኬኒያ ገባ ለሚለው አጭር ጥያቄ መልስ መገኘት አለበት።

ይኼውም ከኮሎኔል ጋልዋክ የተባለ በሱዳን መንግስት ምክትል የደህንነት ሚኒስተር የነበረና የኑዌር ጎሳ አባል የነበረ ሰው በኑዎርነቱ ብቻ ከሌሎች ለእናት ሃገሩ ለመሞት ከተጓዙት መኮንኖችና የበታች ሹማምንት ለይቶ ወደ ኬንያ በLife Line Sudan በተባለ ልዮ አውሮፕላን እንዲመለስ አድርጓል። ሌሎች አባላት ትንሽ በለስ የቀናቸው ወደ አውስትራሊያና ካናዳ ሲገቡ ቡዙዎቹ ከኢህአፖ አባላት ጋር በሱዳን መንግስት ርዳታ ተለቅመው ለወያኔዎች በመሰጠታቸው እስካሁን ድረስ እጣ ፈንታቸው አይታወቅም።

ወደ ዋናው ሃሳቤ ስመለስ ቱዋት ወደ ናይሮቢ ከተመለሰ በኋላ ከወያኔ መንግስት ከድተው ከመጡ እንደነ መ/አ አበራ አዳሙን የመሳሰሉ ጥቂት ግለሰቦችን ይዞ ወደ አስመራ ከተጓዘ በኋላ ጥቅምት 17 ቀን 1993 ወይንም 2000 ዓ ም በሻቢያ አስተባባሪነት ፤

1) የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር (ኢአአግ)
2) የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢአአዴን)
3) የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት ግንባር (ኢዴሃአግ)
4)የቤንሻንጉል ሕዝብ አንድነት ንቅናቄ (ቤህነን)

በመሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን (ኢህአግ)መሰረቱ። ከዚያም ለትግሉ እንዲረዳ በሻዕቢያ ርዳታ አንድ የራሺያ አውሮፕላን በመከራየት ከሳዋ በመነሳት በሱዳን አኮቦ ማለትም የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት የነበረው ሪክ ማቻር በሚቆጣጠረው ነጻ መሬት ስንቅና ትጥቅ በማራገፍ ወደ 150 ወጣቶችን አሰልጥኖ ካስመረቀ በኋላ እንደገና ወደ አስመራ ተመለሰ። አስመራ እያለ ከሱዳን ነጻ አውጭ ጦር መሪዎች ጋር በመጋጨቱ እና ከኢትዮጵያ መንግስት በተሰወረ ሁኔታ ከJRIN የነዳጂ ጋምፖኒ ጋር ቱዋት ልዮ ውልና ስምምነት በማድረጉ በ October 20 ፤ 2002 ዓ ም (እኤአ) በሳልቫኪር SPLM ምክትክል ሊቀመንበር እና የጦር አዛዥ ፊርማ ቱዋት ፖል ቾይና የቱዋት ነው የተባለውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ጠራርጋችሁ እንድታጠፉ የሚል ጠንካራ መመሪያ ያስተላልፋል።

በዚህም መሰረት ከእለታት አንድ ቀን ቱዋት ፖል ካሳም በተለመው የራሺያ አውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አኮቦ ሱዳን እያመራ እያለ አውሮፕላኑ በአየር ላይ በሚቆይበት አራት ሰዓት ውስጥ በሳተላይት ስልክ ለSPLA ሰራዊት በተላለፈለት መመሪያ መሰረት የSPLA በወሰደው የቅድሚያ ጥቃት ዶ/ር አህመድ የተባሉ የቱዋት ረዳት እና የምዕራብ እዝ አዛዥ የነበረው ኮሎኔል ተመስገን ጫላ የአነግ ጦር መሪ ሲገደሉ በሕዝብ ከፍተኛ ርብርብ እና ድርድር ቱዋት ተመልሶ ወደ ሳዋ ይመለሳል። ከዚያም የትግሉ ሁኔታ በመበላሸቱ ሁሌ የመሽሎኪያ ብልሃትና ቀዳዳ የማያጣው ቱዋት መ/አ አበረ አዳሙን የድርጂቱ ተወካይ አድርጎ እሱ ወደ ናይሮቢ ይመለሳል።

ከዚያ በኋላ ኢአአግ በውህደት ወደ ኢሕአግ (የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር) ከተቀየረ በኋላ ምንም ድርጂት እና አባላት በሌሉበት ሁኔታ በተለመደው የማጭበርበር ሁኔታ ሶስት አባላትን በማስተባባር

1)እያዮ እንዳለው የካኩማ ተጠሪ
2)አቶ አስታወሰኝ የተባለ ግለሰብ በሱዳን
3)ሻለቃ ሲሳይ ሳህሉ የተባለውን ግለሰብ በናይሮቢ አሰባስቦ ከራሱ ጋር አራት ግለሰቦች በኢአአግ ስም NGO በማቋቋም በJRIN ስም ወደ አሜሪካ እና አውሮፖ ለመዘዋወር ባገኘው ፈቃድ በየቦታው ለመመላለስ በአንድ ወቅት የተወሰኑ ሊጆች ሲመረቁ ያነሳውን ቪዲዮ በአቶ መልኬ መንግስቴ አማካይነት አባዝቶ በማሳየት በሆላንድ፤ በጀርመን፤ በዴንማርክ እና በስዊዲን በመዘዋወር ሰፊ የማጭበርበር ተግባር ፈጽሟል። በዚያው በተዘዋወረበት ወቅት ለተገኘው የዲያስፖራ ሕዝብ የገባውን የድርጂቱን ቃል ኪዳን ጭምር አሁን ባደረገው የክህደት ስራ አፍርሷል። ለዚህ ማስረጃ እንዲሆን በእነዚህ አገሮች በተዘዋወረበት ጊዜ ካደረገው ሰፊ ንግግር ውስጥ አንድ አንቀጽ ብቻ እዚሁ ላቅርብ።

“… ኢአአግ በተናጠል የሚደረግ ጥረት ወያኔ በዕብሪት በኢትዮጵያዊነት ላይ ያወጀውን የጎሰኝነት የስነ ልቦና እና የጭፍጨፋ ዘመቻዎችን ለማክሸፍ እንደማያስችል ስለሚያምን ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሃገሬን እወዳለሁ የሚል ሁሉ ከገለልተኛ ተመልካችነት ከጠባብ ድርጂታዊ ስሜት እና ከስልጣን ጥማት ራሳቸውን አላቀው በመተባበር ጎልማሳ እና ጀግና በጉልበቱ ፤ ምሁር በእውቀቱ ፤ ስራተኛና ገበሬው በምርቱ ፤ ሃብታም በሃብቱ አረጋዊያን እና አረጋዊያት በጸሎትና በምርቃን ይህ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከጥፋት ለማዳን የተጀመረውን ትግል ግቡን ይመታ ዘንድ እንዲተባበሩና እንዲያግዙት ኢአአግ አጣዳፊ ኢትዮጵያዊ ጥሪውን በሃቅ የሃገር ፍቅር ስሜት ላይ ያቀርባል” ይላል። ይህ ባለ 16 ገጽ ዲስኩር ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊነት ፤ ስለወያኔ ምንነት እና የትግል ዘዴ ያብራራው ሰነድ በወቅቱ አድናቆት ያገኘ በመሆኑ ከካሊፎርኒያ እስከ ሲድኒ ከኬፕታውን እስከ እስቶኮልም ተሰራጭቶ ነበር።

ከዚህ በኋላ በ2006 እኤአ በስዊድን የሚገኙ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን ባደረጉልን ማስተባበር

1) ኢአአግ
2) ኢብአግ
3)ታጠቅ
4)ኢብአአግ መካከል አንድነት እንዲፈጠር እና ጠንካራ የትጥቅ ትግል እንዲደረግ የተመቻቸውን የመግባቢያ ሰነድ ከተፈረመ በኋላ የውህደቱ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በተደረገው ጥሪ

1) የኢአአግ ሊ/መንበር ቶዋት ፖል ቾይ
2)የኢአአግ ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮ/ል አስራት ቦጋለ ሳይገኙ ቀርተው በጥሪው መሰረት የተገኙት ታጠቅ እና ኢብአግ ከብዙ ጊዜ ድርድር እና መግባባት በኋላ የውህደት ግንባር መስርተው በከፍተኛ ዝግጂት እና ሞራል በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ጉዞ ጀምረው ሳሉ ይህ እሱ ያልተገኘበት እና ነገር ግን በፍጹም ስኬት ያገኘ የትግል ውህደት የእግር ውስጥ እሳት ሆኖበት ከህወሓት ጋር በፈጠረው ከፍተኛ ሚስጥር ከጁባ በድብቅ የሳተላይት ፎን (?) የያዘው ቡድን ፤

መ/አ ሞላ አባተ የታጠቅ ኢትዮጵያ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር የጦር አዛዠ ጋር ተጉዞ አኮቦ በደረሱ በሶስተኛው ቀን ጋምቤላ ካለው የወያኔ ጦር ጋር ተገናኝቶ ሁኔታውን ካመቻቸ በኋላ በእሁድ ዕለት ከምሽቱ 12 ሰዓት መ/አ ሞላ አባተን እና ምክትሉን አስወግደው በተዘጋጀላቸው ሄሊኮፕተር በነጋታው ወደ ጋምቤላ ተወስደዋል።
የመ/አ ሞላ ካሜራና የተለያዮ ዕቃዎች እስካሁን በአቶ ቱዋት አባላት እጂ እንዳሉ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተረጋግጧል። እነዚህ ማስረጃዎች ሁሉ ተቀምረው የወያኔ ወንጀለኞች በሚጋዙበት ጊዜ የትም ይሁን የት ቱዋት ፖል ቻይ ከፍትህ በፊት ሳያመልጥ ተጠያቂ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን። ይህ ብቻም አይደለም፤ በቆመለት አላማና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በህያው እግዚአብሄር ስም በገባው ቃል መሰረት ማህላውን በማፍረስ የትም በትኖ እና ለወያኔ የጥይት ራት አድርጎ በበተናቸው ወጣቶች እና አረጋውያን ደም ፍርዱን ያገኛል። ይህም በመሆኑ በኢአአግ የፖለቲካ ቢሮ ቃለ መሃላ ሰነድ ከሰፈሩት 6 ነጥቦች መሃከል በተራ ቁጥር 6 የተመለከተውን ቃለ መሃላ ከዚህ ቀጥሎ አቀርባለሁ።

“…ባጠቃላይ የተሰጠኝን ኃላፊነት በማክበር የወያኔ ጨካኝ መንግስትን ከሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል ኢአአግ የሚያደርገውን የትግል ዓላማ ዳር ለማድረስ ትናንትም ሆነ ዛሬ ላልተቆራረጠች ሀገርና ለልተበታተነ ሕዝብ በጀግንነት ሲጋደሉ የነበሩ አሁንም ከትምክህተኝነት ከማንአህሎኝነት ከአድርበይነትና ከጠባብ የዘረኝነት ስሜት ውጭ በሆነ ተመሳሳይ አቋምና ስሜት ይዘው ወያኔን ለመታገል ከተነሱና ወደፊትም ከሚነሱ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋር ሁሉ በሰላምም ሆነ በትጥቅ ትግል በጋራ ለመታገል የሚያስችል ዕቅድ ለማውጣትና ለማስፈጸም ሙሉ በሙሉ ዕውቀቴንም ሆነ ጉልቤቴን አስፈላጊ ከሆነ ህይወቴንም ጭምር ለተነሳሁበት ዓላማ ለማዋል በእግዚአብሄር ስም ቃል እገባለሁ” ይህንንም የመሃላ ሰነድ ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር ፖስት አድርጊያለሁ።

በአጭሩ ለማጠቃለል ኢአአግና ቱዋት ፖል ከ2003 ጀምሮ ትግሉን ትቶ ወደ ግል ምቶችና ሞቅ ያሉ ትግሎችን በማኮላሸት ላይ የተመሰረተ ግለሰብ ከመሆን አልፎ የተደሰኮረው ተግባርና ማንነት ላም ባልዋለበት በመሆኑ ምንም አያስደንቅም። ለራሱ በቆመለትና ለማለለት ዓላማ ተፈጻሚነት ያልሆነ ግለሰብ ለህወሓት ዓላማ ተፈጻሚነትም አይታገልም። ለመሆኑ የት ነው የቱዋት ጦር? በኤርትራ ምድር? ለመሆኑ የት ነው የተዋት ጦር በሱዳን ወይንም በጋምቤላ ምድር?

በ2006 ዓ ም የህወሓት አጋዚ ከ90 ዓመት ሽማግሌ ሳይቀር ታጣቂ አለ የተባለበትን ቦታ ከቦ እንኳ ሰውና ሳር ቅጠሉን አቃጥሎት ራሱም ይሄንን አውቆ ወደ ድለላ የገባበት ሁኔታ ነው የነበረው። ራሱ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት በሳልቫኪር በኩል በ2002 የኢትዮጵያ አቆጣጠር ጠይቆ መለስ ዜናዊ የደርግ ወንጀለኛ ነው ይቅርታ ጠይቆ ይግባ ብሎት አልነበረም እንዴ? ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው?

ሃቁ ከሆነ ዛሬም ቢሆን ከ1986 ዓም ጀምሮ ኢአአግን የመሰረቱና በግንባር ቀደምነት በኋላም በኢብአግ በፈለገ ኢትዮጵያና በታጠቅ አብዛኛው ወጣትም በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንቦት ሰባት ውስጥ ትግሉ እንዲጧጧፍ እያነደዱት ይገኛሉ። የቱዋት የውሸት የኢአግ ፖሊት ቢሮ የተባሉት

1)ሻለቃ ሲሳይ ሳህሉ ፤ካናዳ
2)አቶ ታደሰ ገላን ፤ አሜሪካ
3)መ/አ እያዮ እንዳለው ፤ አሜሪካ ሌሎች

የኢአአግን ሰራዊት ያሰለጠኑና የሱዳን አኮቦ በርሃ የታገሉ ሻምበል ተስፋየ በአውስርራሊያ ፤መ/አ አበረ አዳሙ በኖርዌ ይገኛሉ። ለዚሁም መ/አ አዳሙን ከኢአአግ አባልነት ነሐሴ 26 ቀን 2002 ጥፋቶች ናቸው ተብለው በተዘረዘሩ ሁለት ነጥቦች ከአባልነት ታግደው ተባረዋል። ይህ የእገዳ ደብዳቤ በእጃችን ስለሚገኝ አስፈላጊ በሚሆን ሰዓት ከሌሎች አስር ደርዘን ማስረጃዎች ጋር መበተን ይቻላል። የዚህ ጉደኛ ግለሰብ የማወናበጃ ወንጀሎች ተዘርዝረው ስለማያልቁ አሁን አፋቸውን ካልዘጉ የሚመሩት ሰራዊትጫካ በትነው ራሳቸው ወደ ናይሮቢ በመሮጥ ትራብል ዶክሜንት አውጥተው ወደ ውጭ ለመውጣት ሲል በተጭበረበረ የኬኒያ የስደተኛነት መታወቂያ ምክንያት ታስሮ በነበረ ጊዜ አቶ ዘለቀው ጀበሮ ከጫካ ወደ ዮጋንዳ በመምጣት 30000 የኬኒያ ሽልንግበአቶ ቢቾክ (በአሁኑ ወቅት እዚህ አውስትራሊያ ባሉ ዘመዱ አማካይነት)ለኬኒያ ዳኞች ጉቦ ተከፍሎለት መፈታቱን የዓይን ምስክሮች ሆነን ያየነው ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ የበለጡ የቱዋት ወንጀሎች በተለያዮ ቦታዎች ሂዶ የተፈራረማቸው ምስጢራዊ ሰነዶች በሙሉ በክፍል ሶስት ለማውጣት የምገደድ ሲሆን አፉን ሸብቦ ወደ 1983 ዓ ም ስልጣኑ ጋምቤላ ተመልሶ በኑዌር ስም ለወራት እንዲነግዱና ለዳግማዊ ስደት ወደ ሱዳን መንገዱን እንዲያመቻቹ ይመከራሉ።

ለዚህ ጽሁፍ የቀረቡ ተያያዥ ሰነዶችን በሙሉ ይሄንን በመጫን ማየት ይቻላል።

ዓለማየሁ መላኩ
ከአውስትራሊያ።

———————————
በቦርከና ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የሚያንጸባርቁት የጸሃፊውን አመለካከት ነው። ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ። እዚህ ይጫኑ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,440FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here