spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትእንግሊዝ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሁዋላ መሳሪያ ልታደርግን መርዝ ይዛ ተነስታለች : በአይምሮ...

እንግሊዝ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሁዋላ መሳሪያ ልታደርግን መርዝ ይዛ ተነስታለች : በአይምሮ ቁራኛ ተከታተልዋት!

advertisement

የሐረርወርቅ ጋሻው
ኅዳር 9 2009 ዓ ም

ንቃት ፡ ንቃት በቁዋንቁዋችን ፡ በአገራችን ፡ በአሃጉራችን ስም ስለሚፈጠሩ ተግባሩች ሁሉ። አፍሪካን የሚጠቅም አንድም ደግ ስራ ነጭ አያደርግም በፍጹም። ነጪ ሁሌም አንድ መጸሃፍ ይዞ በመጣ በውስጡ በመርዝ የተለወሰ አንብቦ የራስን ማጥፍያ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው እስከዛሬ በዓለም ታሪክ ውስጥ ከታየው በታሪካችንም ካጋጠሙን በመነሳት። ታሪካችንን መጸሐፋችንን እየወሰዱ እና እያቃጠሉ አጥፍተው የእነሱን እየሰጡን አንድም ጥይት ሳይተኩሱ በቋንቋቸው አሳትመው በትምህርት መልክ አሜን ብለን እነሱን የጥበብ መጀመርያ ናቸው እስክንል አምላክን እረስተን ክደን ድረስ የቋንቋቸው እና የፓለቲካቸው ሙርከኛ አድርገውናል። ሬድዮን ምንም ጊዜ የማይለውጠው አዳዲስም ቴክኒዮሎጂ ያለዋወጠው እንደውም ያሻሻለው ትልቅ የሕዝብ መከፋፈያ እና አይምሮውን የመቆጣጥገሪያ ትልቅ መሳሪያ ነው። ልብ በሉ የአገሬሰዎች በሙሉ።

ለጤና እንዳይመስላችሁ አስቡት አፍሪካዊው ሁሉ ነቅቶ መጠባበቅ አለበት እንግሊዝ ትልቅ መሰሪ ተንኮል ይዛልን የኖረች አሁን ዳናልድ ትራምፕ በመመረጡ ደግሞ በመደናገጥ ለረጂም ጊዜ ስታስብበት የነበረውን ተንኮል በአፍሪካ እና ጥቅም በቀረባት አገሮች እና ሕዝብ መሃል ጊዜውን አሁን ተጠቅማ ከሁለተኛው ዓለም ጦነት በሁዋላ ሂትለር የአረቡን አያቶላ በጊዜው ተጠቅሞ ወደ ጀርመን ወስዶ አማካሪው አድርጎ ሾሞ ጭምር እንግሊዝን ከይራቅ ለማስወጣት የሬድዮ አዘጋጅ እና አቅራቢ አድርጎ በመቸረሻም እንግሊዝ እንድትወጣ ስትደረግ ፡ በለመደችው በየደረሰችብት ከፋፍላ መሄድ ልምድዋ በመሆኑ ይቺ ጊንጥ ፡ የአንድ ሕዝብ እና አገር አካል የሆነችውን ኩዌትን አገር ብላ ጠርታ አንድ ቤተሰብ ንጉሳዌ ቤተሰብ የኩዌት መሪ ብላ ልትወጣ ችላለች በጊዜው። ያበሁለተኛው የአለም ጦርነት እንግሊዝ ብሎም ቀደም ብላ በኢንዲያ ሳይቀር ስትሸነፍ የዘራቸው አንድን አገር እና ሕዝብ የመከፋፈል አባዜዋ ሊረሳ የማይገባው ጥሩ ምሳሌ ማለት እስዋን ካላመቻት የወሮ በላነትዋን ማንነት ካልተቀበለ አንድ አገር ሕንዶች በአንድነት ሲያሸንፍዋት በመጨረሻ ኢንዱ እስላሙን ጨቁኖ ሲገዛህ ይኖራል ካሁኑ ፓኪስታን ብለህ ብቻዋን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ፍጠር በሚል የሃይማኖት ልዩነት ከፋፍሎት የማያውቀውን ሕዝብ ከፍላ እስዋ ስትወጣ ወደ ጦርነት እስዋን ያስወጡት ያሸነፉት እርስ በእርስ መፋጀት ቀጠሉ ይሄውም አሁንም አልበረደም በካሽሚር በሚባለው ቦታ መክኒያት።

ስለዚህ ቢቢሲ ትራምፕን በመፍራት ለወሰደችው እርምጃ ቋንቋዬን ቢቢሲ ሊጀምር ነው በሚል ከመደሰት ለምን?በሚለው ላይ እንደሌላው አፍሪካዊ ጥሩ አድርጎ የእንግሊዝን መሰሪነት ብሎም የፈረንጁን የሚያውቀው ለምን አሁን? በሚል እየተነጋገርበት እንዳለው የኢትዮጵያም ሕዝብ ለነጮች ለእንግሊዝም እጁን ሰጥቶ ወይም አሜን ብሎ ተገዝቶ እና ለእንግሊዝ አጥፊነት በወገኑ ላይ ተባብሮ የማያውቀው በታሪኩ ፡ ለምን አሁን? የቢቢሲ ስርጭት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች እንደ አሜሪካኑ እንደ ጀርመኑ እንደ አውስትራሊያው የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ ገንዘብ እና ጊዜ በማውጣት ለምን አስፈለገ ለምን? ለምን? በሚል መነጋገር ማመዛዝን እናም መነጋገርን ጊዜው ግድ ይላል።

ከአክብሮት ጋር።
የሐረርወርቅ ጋሻው

—————————
ያጋሩት! ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ ፤ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here