ቬሮኒካ መላኩ
ኅዳር 12 ፣2009 ዓ ም

ምንጭ : “Ethiopia Under Mussolini and the Colonial Experience” By Alberto Sabacci.
via Veronica Melaku
አዲስ አበባ እንደገና የፅንፈኛው ጎራ አጀንዳ ሆናለች። የእነ ኤርምያስ ለገሰ ትንታኔ ተከትሎ ይመስላል ። እንኳን በከተማዋ ብዙ የሰራበት ኤርሚያስ ይቅርና እኔም በፅንፈኞች የሚመራውና ሰበታ የደረሰው የኦሮሞ አመጽ አዲስ አበባ ውስጥ እንደማይገባ 100% እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ምክንያቱም ራሱን በራሱ ማጥፋት የሚፈልግ ማህበረሰብ ስለሌለ፡፡
ለንደን ላይ “ትበታተናለች ” እያለ የፎከረና አትላንታ ላይ “ኮንቬንሽን ” የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው የመገነጣጠልን አጀንዳ እያራገበ እንኳን የአዲስ አበባ ሊቀበል ይቅርና ሙሉ ኢትዮፕያ ፉርሽ አድርጎታል።
…
ከዚህም በተጨማሪ ” አዲስአበባ የማን ናት? ” የሚለው ጥያቄ መልስ አላገኘም ። አማራም የእኛ ናት ይላል ። ኦሮሞውም የእኔ ናት ይላል። በማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን መረጃ መሰረት ከ55 % በላይ የከተማው ነዋሪም አማራ መሆኑንም ማወቁ ለብዙ ጥያቄወች መልስ እና ፍንጭ ይሰጣል።
…
ወያኔ በመጀመሪያ ስልጣን ሲይዝ የተጠቀመው ካርታ እና የፌደራል አወቃቀር ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮፕያን ሲይዝ የተገበረውን ካርታ ነበር ። በብሔር የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ካርታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራው የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ በ1936 እ.ኤ.አ ሲሆን፤ አላማውም የጎሳና የብሔር ግጭትንበማነሳሳት ሰላም አልባ ኢትዮጵያን መፍጠር ነበር፡፡ ጣሊያኖች ለገዛ አገራቸው ለእነ ሮማ እና ቬነስ ያላደረጉትን የብሔር ክፍፍል ካርታ ለእኛ ለመስጠት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነበር፡፡
ከ50 ዓመት በኋላ ግን በአቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት የጣሊያኖች ምኞት ሊሳካ ችሏል፡፡ ልዩነቱ የጣሊያን ካርታ በዚህ ሰሞን ግራና ቀኛቸውን መለየት የተሳናቸው
የኦሮሞ ፅንፈኞች የሚሟገቱበትን የአዲስ አበባንና አካባቢዋን የኦሮሞ ሳይሆን የአማራ ግዛት አካል ማድረጉ ነበር፡፡ጣሊያን አማራን የሚባለውን ብሄር አምርሮ ቢጠላም አዲስአበባ እና ሸዋ የዚህ ብሄር ታሪካዊ ግዛት መሆኑን ተቀብሎ ነበር ። መለስ ዜናዊና ኦነግ የአማራን ብሄር ከጣሊያን የበለጠ ይጠሉ ስለነበር አዲስአበባን ከአማራ ክልል ካርታ ላይ ሊፍቁት ችለዋል።
…
በሌላ ወገን የወያኔ-ትግሬ ፍርሃት በሰሜናዊና ምስራቃዊ አዲስ አበባ ላይ አለ፡፡ በክልሎች ክፍፍል ጊዜ ኦነግና ወያኔ ሃገር ሲከፋፈሉ አማራ ክልል መግባት የሚገባቸው ነገር ግን ሆን ተብለው ያለአግባብ ወደትግራይ፣ ኦሮሚያና አዲስ አበባ ክልል የገቡ ብዙ ቦታዎች አሉ፡፡ ኦነግም በጊዜው የትክፍፍሉ አካል ስለነበር ሁኔታውን ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች የተሻለ ይረዳል፡፡ በጊዜው ተነስተው ከነበሩት ጥያቄዎች መካከል የፍቼ አማራነት ጥያቄ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ወያኔ ምስራቃዊ አዲስ አበባ የአማራ ክልል ግዛት አድርጎ ስለሚያስበው ፋብሪካዎችና መሰረተ ልማቶች ባጠቃላይ ማለት በሚቻል መልኩ ከምስራቃዊና ሰሜን ምስራቃዊ አዲስ አበባ በራቁ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲገነቡ ያደርጋል፡፡
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ቁጥር የሌላቸው ፋብሪካዎችና ኢንቨስትመንቶች የተሰሩትና የታቀዱት በናዝሬት መስመር፣ በሰበታ አካባቢ ነው፡፡ በደብረ ብርሃን መስመር በስህተት ከተሰሩ ጥቂት ፋብሪካዎች በስተቀር ምንም የለም፡፡ ወያኔ ይህንን ያደረገው በአማራ ጥላቻ ነው፡፡ ኦነግ ደግሞ ይህንን የሚያየው በተቃራኒው በመሬት ነጠቃ ነው፡፡
———
ቬሮኒካ መላኩ (የብዕር ስም ይመስላል) በፌስ ቡክ ላይ ትችት አዘል አስተያየት በመጻፍ ትታወቃለች።
ጽሁፉን ማጋራት አይርሱ።