spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeአበይት ዜናየውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ እንዲደረግ ለትውልደ-ኢትዮጵያውያኑ ጥሪ ቀረበ (ኢሳት)

የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ እንዲደረግ ለትውልደ-ኢትዮጵያውያኑ ጥሪ ቀረበ (ኢሳት)

advertisement

ኢሳት
ታህሳስ 19 ፥ 2009

በውጭ ሃገር ያሉ የኢትዮጵያ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ለ3 ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሃገር የመላክ ማዕቀብ ጥሪን አስተላለፉ።

17 የሚሆኑት የሲቪልና የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያውያን ለንግድም ይሁን ለቤተሰብ ድግማ የሚልኩት የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ ማድረግ በሃገሪቱ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ለማድከም ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ መግለጫው አመልክተዋል።

ድርጅቶቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪው መላካቸውን ለ3 ወራት ካቆሙ በኋም ቢያንስ ለቀጣይ 6 ወራት ደግሞ የሚፈለገውን ገንዘብ አንድ ሶስተኛ እንዲቀንሱ ማድረግ በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ለማድከም ይረዳል ብለዋል።

የማዕቀቡ ጥሪ በተላለለፈበት የጊዜ ገደብ ለንግድም ሆነ ለቤተሰብ መላክ የግድ ከሆነ ለስርዓቱ በማይደርስበት መልኩ ቢሆን ተመራጭነት እንደሚኖረውም መክረዋል።

በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚላከው የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ንግድ ይበልጥ ለስርዓቱ ከፍተኛ ገቢ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታል።

በያዝነው የፈረንጆች አመት ማለትም በ2016 ብቻ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ከውጭ የተላከው የውጭ ምንዛሪ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ በህወሃት/ኢህአዴግ በሚመራው መንግስት በቅርቡ የወጣው መረጃ ላይ ተገልጿል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here