spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeዜናየኤርትራ መሪ ለሃገሮች መሪዎች አቤቱታ ፃፉ (የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ)

የኤርትራ መሪ ለሃገሮች መሪዎች አቤቱታ ፃፉ (የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ)

advertisement

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ
ታህሳስ 25 ፤ 2006 ዓ ም

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

ዋሺንግተን ዲሲ — ፕሬዚዳንቱ “የሚፈፀመው ኢፍትሃዊ ድርጊት አንድም ምንም ምክንያት ሊሰጠው የማይችል፤ አንድም መሠረታዊ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሞራል ደምቦችን የሚጥስ ነው። ከዚያ በላይ ደግሞ ለክልላዊ ፀጥታና ሰላም አደጋ የሚደቅን ነው” ማለታቸውን ከኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አትቷል።

“የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ብይኑን ከሰጠ አሥራ አራት ዓመታት አልፈውም የኤርትራ ግዛቶች አሁንም በወረራ እንደተያዙባት ናቸው” ያሉት ፕሬዚደንት ኢሣያስ የሃገሮች መሪዎች የህግን የበላይነት ያስከብሩ ሲሉ ጠይቀዋል።

በሀገራቸው ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች “ህገ ወጥና ኢፍትሃዊ ናቸው” ሲሉ የኤርትራው ፕሬዚደንት አማርረዋል ።

“በተንኮልና በሃሰት በተፈበረከ ውንጀላና ሉዓላዊ ግዛታችን በወረራ ተይዞ በካሣ የማይወጡት በደል እየደረሰብን ነው” በማለት አስምረው “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥፋቱን ፈጥኖ ያስተካክል” ሲሉ አሳስበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ማዕቀቦቹ እንዲቀጥሉና የመንግሥታቱ ድርጅት የሶማሊያና የኤርትራ ተቆጣጣሪ አካል ሥልጣን እስከዚህ 2017 ዓ.ም. ታኅሣስ አጋማሽ እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል ።

—————
ስለ ዘገባው የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here