spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeአበይት ዜናበባህርዳር ግራንድ ሆቴል ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ

በባህርዳር ግራንድ ሆቴል ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ

advertisement

ኢሳት
ታህሳስ 26 ፥ 2009

Grand Hotel, Bahir Dar  ምንጭ ጁማ ትራቭል
Grand Hotel, Bahir Dar
ምንጭ ጁማ ትራቭል

ዛሬ ረቡዕ ማምሻውን በባህርዳር ግራንድ ሆቴል የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በጥቃቱ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም።

በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ባህርዳር ግራንድ ሆቴል ላይ ጥቃቱን ስላደረሱት ወገኖች ማንነት የታወቀ ነገር የለም። ጥቃቱን የፈጸሙት ወገኖች ለምን አላማ እንደፈጸሙትም ግልጽ አልሆነም።

ሆኖም አዲሱን የፈረንጆች አመት በማስመልከት ባለፈው ዕሁድ ይካሄዳል የተባለውን የሙዚቃ ዝግጅት በመቃወም በባህርዳር ከተማ ወረቀት መበተኑን ማስታወስ ተችሏል።
“እናቶች ስለዚህ ትውልድ እንዳያለቅሱ፣ እንዳያዝኑ፣ እንዳይራገሙ እናድርግ” በሚል ርዕስ ባለፈው ሳምንት የተበተነው የተቃውሞ ወረቀት የወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደም ሳይደርቅ የሚደረገውን የሙዚቃ ዝግጅት እንቃወም የሚል ይዘት እንደነበረው ለመረዳት ተችሏል። ሆኖም ይህንን ተቃውሞ የሚመሩት ወገኖች ከዚህ ጥቃት ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው ማወቅ አልተቻለም።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናት በሆቴሉ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች በጥቃቱ ደጃፍ ላይ በመፈንዳቱ በሰዎቹ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም አመልክተዋል። የሆቴሉ ባለቤት ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ከብአዴንም ሆነ ከህወሃት ባለስልጣናት ገር ቅርበት ያላቸው ባለሃብት መሆናቸው ተመልክቷል።
በዚሁ በባህርዳት ከተማ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ማክሰኞ ዕለት አራት የኮማንድ ፖስት አባላት እስማዔል አህመድ የተባለ የ38 አመት ጎልማሳና የአራት ልጆች አባት ቤቱ ደጃፍ ላይ እንደገደሉት መዘገባችን ይታወሳል። ቅዳሜና ዕሁድ በባህርዳር በተካሄደ የትግራይ ተወላጆች ስብሰባ ላይ ህወሃት ለትግራይ ተውላጆች የጥንቃቄ ዕርምጃ እንዲወስዱ ማሳሰቡም አይዘነጋም።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here