advertisement
ጥር 2 2009 ዓ ም

Source : Social Media
በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በሚገኘው የኢንታሳል ሆቴል በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አንድ ሰው ሳይሞት እንዳልቀረ የማህበራዊ ሚዲያ ምንጮች ዘግበዋል። የኢሳት የእንግሊዝኛ ዘገባ እንደሚያመለክተው ደሞ አራት ያህል ሰዎች ከቦንብ ፍንዳታው ጋር በተያያዘ ምክንያት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
ሙሉነህ እዮኤል በማህበራዊ ሜዲያ ስለጎንደር መረጃ በማካፈል ይታወቃል። እሱ ያካፈለው መረጃም ጥቃቱ በእርግጥም በጎንደር ከተማ በቀበሌ 18 አካባቢ በሚገኘው የኢንታሳል ሆቴል እንደደረሰ ቢያመለክትም የቁስለኛ ቁጥር አንድ እንደሆነ ያሳያል። ፍንዳታው ደረሰ የተባለው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት እንደሆነም ዘገባው ያሳያል። ሆቴሉ በስርዓቱ ባለስልጣናት የሚዘወተር ነውም ተብሏል።
የቤተ አምሃራ አክቲቪስቶችም በማህበራዊ ተመሳሳይ ዘገባ ይዘው ወጥተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በባህር ዳር ግራንድ ሪዞርት ሆቴል ፍንዳታ እንደደረሰ መዘገቡ ይታወሳል።