- Advertisement -
ጥር 2 2009 ዓ ም

በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ ተሸላሚነቱን በማረጋገጥ የመጨረሻውን መስመር ሲያቋርጥ የተቃውሞ ምልክትን በማያየት ዓለምን ያነጋገረው አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ እና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዚህ ወር በሎንዶን በሚደረገው ዓለም ዓቀፍ የማራቶን ውድድር ይወዳደራሉ።
ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው መስከረም በበርሊም ማራቶን 2:03:03 በሆነ ሰዓት በመግባት በታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን የማራቶን ሰዓት ማስመዝገቡ ይታወሳል። ከሎንጎኑ ማራቶን በፊት 200 ሺ ዶላር በሚያስገኘው የዱባይ ማራቶን ይሳተፋል።
አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ በማራቶን ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት 2:04:52 ሲሆን እ ኤ አ በ2012 በቺካጎ በተደረገ ማራቶን ወድድር ነው ያስመዘገበው። ከሪዮ ኦሎምፒክ መልስ የአክቲቪዝም ስራ በመስራት ተጠምዶ የነበረው ፈይሳ ሊሌሳ ለሎንዱኑ ማራቶን በቂ ዝግጂት እንዳደረገ ይነገራል።