እንቃሽ/ወገራ ወያኔ ጦርነት ከፈተ (ሙሉነህ ዮሃንስ)

የካቲት 9 2009 ዓ ም

ጎቤን ሊያድን የሄደው ጦር በህዝብ ተባሯል!

ማክሰኞ ማታ እንቃሽ ከደጋው ላይ በወያኔ ሰራዊትና በከፋኝ የጎበዝ አለቆች መካከል ለሰአታት የቆየ ውጊያ ተደርጓል። ሁኔታው አሁንም ውጥረት የበዛበት ነው። ባለፉት ቀናት ውስጥ በአቅራቢያ ወረዳወች የሚገኘው ህዝብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወቃል። እስካሁን በወያኔ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ዝርዝር አልታወቀም። የጎበዝ አለቆች ግን ደህና ናቸው።

ወደ ቆላማው ወገራ በገፍ የዘመተው የወያኔ ሰራዊት ለነፃነት የሚፋለሙትን የከፋኝ የጎበዝ አለቆች ለማደን እየባዘነ ነው። ወያኔወች የጎቤን ሃይል ፍለጋ ሄደው አንድ ሰላማዊ አርሶ አደር ገድለው ሕዝቡ ሲነሳባቸው ወደ ጠገዴ ሸሽተዋል።
ህዝብ ያሸንፋል©!
ሙሉነህ ዮሃንስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.