advertisement
መጋቢት 3 2009 ዓ ም

በአዲስ አበባ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መጣያ መሬት መንሸራት ምክንያት ቢያንስ ከሃያ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ታውቋል። ከጥቂት ሰዓትት በፊት አሶሲየት ፕሬስ የሞቱን ቁጥር 15 በማለት የዘገበ ቢሆንም አሁን በብዙ ሜዲያዎች እየወጣ ባለው ዘገባ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 24 ሳይደርስ እንዳልቀረ ታውቋል። 37 ያህል ሰዎች በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።
መሬቱ በአካባቢ በነበሩ ቤቶች ላይ ነው የተደረመሰው ተብሏል።
አደጋው የደረሰው ትላንት ማታ ከምሽቱ በስምንት ሰዓት አካባቢ እንደነበር ፋና ባወጣው አጭር ዘገባ አስታውቋል።
አቶ አሰፋ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ለአሶሲየት ፕሬስ እንደተናገሩት አደጋው ሲደር በአካባቢው ከ150 በላይ ነበሩ ብለዋል። ስድስት ያህል የመቆፈሪያ መኪናዎች በፍለጋው ሂደት እንደተሰማሩ የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።
የእግሊዝኛው ዘገባ እዚህ አለ