ጎርጎራ ከተማ በቻይና ድርጅት ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ ሰወች ተጎዱ
3 ሰወች ሞተው 4 ቆስለዋል ተብሏል
አስናቀው አበበ እንደዘገበው
መጋቢት 26 2009 ዓ ም

ከጎንደር ከተማ 60 ኪ.ሜ. እርቆ በቆላድባና በጎርጎራ መካከል በመንገድ ተቋራጭነት የተሰማራው ዩራፕ የተባለው የቻይና ድርጅት የሚገለገልባቸው መኪኖች የቆሙበት ካምፕ ላይ ትናንት ሰኞ ሌሊት በተሰነዘረ ጥቃት የተኩስ ልውውጥ ተነስቶ 3 ሰወች መሞታቸውና 4 መቁሰላቸው ከአካባቢው የተገኘው ማስረጃ ያሳያል።
ቻይና ለወያኔ ሙሉ ድጋፍ መስጠት በመቀጠሏ ከባድ ትችት ሲሰጥ ቆይቷል። ከስልክ ጠለፋ የስለላ ስራ እስከ መሳሪያና ገንዘ እርዳታ ያደርጋሉ። ይባስ ብለውም ወያኔ የተከሰተበትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ በባህላችን እጅግ ጠያፍና ተደርጎ የማያውቅ የአህያ ስጋ ቄራ መክፈታቸው ቁጣን ቀስቅሷል። ይህ የተሰነዘረው ጥቃት በማን እንደሆነ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም። ወያኔ ግን መረጃው እንዳይወጣ ለመደበቅ ሲጣጣር መታየቱ ይበልጥ ጥያቄ አጭሯል። የትናንትናውን የቦንብ ጥቃት ጨምሮ ጎንደር ውስጥ በስፋት እየደረሱ ስላሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶች በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወቃል።
ክትትል እያደረግን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን።