spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeአበይት ዜናየወያኔ አስነዋሪ ድርጊት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ ጀግኖች (አስናቀው አበበ)

የወያኔ አስነዋሪ ድርጊት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ ጀግኖች (አስናቀው አበበ)

አስናቀው አበበ
ሚያዚያ 2 2009 ዓ ም

ጀግኖች ሰማዕታት
በሰሜን ሸዋ ወያኔን ጋር ሲፋለሙ የወደቁ ጀግኖች ሰማዕታትን ወያኔ ፋሺስት ጣሊያን ሲያደርግ እንደነበረው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ሁኔታ አስከሬናቸውን በዚህ መልክ ተጫውቶበታል

ከቅርብ ወራት ወዲህ በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴና ብዙ አካባቢወች በመንቀሳቀስ ለስርዓቱ ታማኞች ራስ ምታት ሆነው ጥቃት በማድረስ ላይ ከነበሩ የጎበዝ አለቆች ሁለቱ መገደላቸው ተሰማ። እራሳቸውን አደራጅተው ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በመንግስት ተቋማት እና ባለስልጣናቱ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት በማድረስ ለወያኔ የእግር እሳት እንደነበሩ ከአካባቢው ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

እነዚሁ ታጣቂዎች፣ ባለፈው ጥር 7 ቀን 2009 ዓም፣ እነሱን ለማደን ቅኝት ላይ በነበረ የወያኔ ሃይል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ሰንዝረው መኪናው በመገልበጡ በርካታ ወታደሮች መሞታቸው ተነግሮ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ወታደራዊ ፒካፕ መኪናው ታጣቂዎቹ እንደሚገኙበት ወደተገመተው አካባቢ ሲያመሩ አስቀድሞ መረጃው የደረሳቸው ታጣቂዎቹ አድፍጠው ባደረሱት ጥቃት ከሶስት በላይ የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ ሌሎችንም ቁስለኛ አድረገው እንደነበረ ተዘግቦአል።

ሆኖም በጎበዝ አለቆቹ እንቅስቃሴ የተደናገጠው ወያኔ ከፌደራል ደህንነት፣ መከላከያ ሃይል እና አማራ ክልል ፀጥታ ቢሮ አባላቱን ወደ አካባቢው በማሰማራት ህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረግ እና ጠቋሚዎችን በገንዘብ በመግዛት በተደረገ ክትትል ሁለቱን ታጣቂዎች ደቡብ ወሎ ወረኢሉ አካባቢ በተደረገ ግጥሚያ መሰዋታቸውን የሰማነው በጥንቅ ሃዘን ላይ ሆነን ቢሆንም ጀግንነታቸውን ስናስብ የፈነጠቁትን የትግል ጮራ እያሰብን እንፅናናለን።

በታጣቂዎቹ ድርጊት ተበሳጨተው የነበሩት የወያኔ ባለስልጣናት በጥይት የተጎዳ አስከሬናቸውን ለህዝብ እንዲታይ በማድረግ ኢ-ሰብአዊ ግፍ መፈጸማቸውም ታውቆአል። ይህ የተለመደ ወያኔያዊ ቀሪውን ህዝብ የማሸማቀቅ እና አንገት የማስደፋት ስራ የአካባቢው ህዝብ ለወያኔ ያለውን ጥላቻ የበለጠ ያባባሰ እና ለትግል መነሳሳት መፍጠሩን ያካባቢው ምንጮች አስረድተዋል። “ይህ አይነት ድርጊት ፋሺስት ኢጣልያ የአርበኞችን አስከሬን አደባባይ በመስቀል ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ለማሸማቀቅ ቢሞክርም የአርበኝነቱን ትግል አላዳከመውም” በማለት አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌ፣ “ይህ የወያኔ አረመኔያዊ ድርጊት የመራህቤቴን ህዝብ አስቆጥቷል ለበለጠ ትግል ያነሳሳል እንጂ አያሸማቅቅም” ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ አካባቢው ምንጮቻችን ከሆነ አሁንም በዱር መሽገው የሚገኙ ቀሪዎቹ የነጻነት ሃይሎች በጓዶቻቸው ሞት ቢያዝኑም ለበለጠ ፍልሚያ እራሳቸውን በማዘጋጅት ላይ እንዳሉ ታውቁአል። በሰሜን ሸዋና በጎጃም እየተጠናከረ የመጣው የትጥቅ ትግል ጎንደር ውስጥ በስፋት ከሚካሄደው ፍልሚያ ጋር እየተቀናጀ መምጣቱ ወያኔን ክፉኛ አስደንግጧል።
ይህን እጅግ ኢሰብአዊ የሆነ እንግልት የደረሰባቸውን የተሰው አስከሬን ህዝብ እንዲያየው የለጠፍነው ሃቁ መጋለጥ ስላለበት ነው። አወን እነዚህ ጀግኖች አስከሬናቸው ተጠቅልሎ በገመድ ተጎትቷል፣ ተቀጥቅጧል፣ አካላቸው እንዲጎድል ተደርጎ ገቢያ ላይ ለትርኢት እንዲቀርብ ሁኗል። ይህ የፋሽሽት ጣልያን በአርበኞቻችን ያደረገውን ግፍ ያስታውሰናል። ወያኔ ባእድ ጥቁር ፋሽስት ነው። ከሃገራችን ተነቅሎ መጥፋት አለበት።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here