spot_img
Tuesday, October 3, 2023
Homeነፃ አስተያየትየጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች በኢትዮጵያ ፤ አድሃኖም ሃገሩን ሳያድን አለምን አያድን (ዘመን)

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች በኢትዮጵያ ፤ አድሃኖም ሃገሩን ሳያድን አለምን አያድን (ዘመን)

advertisement

ግንቦት 10 ፤ 2009 ዓ ም
ዘመን : zemenatu@gmail.com

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች በኢትዮጵያ
አድሃኖም ሃገሩን ሳያድን አለምን አያድን

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያስጀመረውና በእጅጉ የሚያደንቀው ገዥው ፓርቲ የሚመካበት ገድል ነው-የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች
አገልግሎት::

የተጀመረው በሐምሌ ወር 2001 አ.ም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስፈፃሚነትና በፌደራል ጤና ጥበቃ የበላይ ተቆጣጣሪነት ነው::
ህወሓት/ኢሕአዴግ በጤናው ዙሪያ እመርታ አስመዘገብኩባቸው ብሎ ከሚላቸውና በውጭ እርዳታ ሰጭዎችም ዘንድ ሞገስን አገኘሁበት ብሎ የሚኩራራበት ይኸው የጤና ኤክስቴንሽን ጥራዝ (ፓኬጅ)ነው::

የጤና ኤክስቴንሽን ጥራዙ አስራ አንድ ዋና ዋና ዘርፎች ሲኖሩት: ለምሳሌም የአካባቢ ንፅህና እንዲጠበቅ ማስቻል: ያልተፀዱ አካባቢዎች ንፁህ ለኑሮና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ ማስቻል ይገኙበታል:: ከተጠቃሚው ዘንድ የሚሰሙ ጤናን የሚመለከቱ መረጃዎችን እንደግብአት ወስዶ ቅደመ-ጥንቃቄ በማድረግ ማህበረሰቡን ጤናማ ማድረግ ቁልፉ የጥራዙ መርህ ነው::

መሬት ላይ የሚሰራው ግን ሌላ ነው:: ሁሉም አምባገነኖች እንደሚያደርጉት ዜጎቹ እለት በእለት የሚያስቡትን መከታተልና “ባቄላዋ ሳታድር መቆርጠም” የሚሻው ህወሓት/ኢሕአዴግ ከህዝብ በሚሰበስበው ግብር የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎችን በማሰማራት ሕዝቡን ያፍናል::

የህወሓት/ኢሕአዴጎቹ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ለምርጫ ቅስቀሳና ለፖለቲካ ማስፈፀሚያነት ማገልገል ነው ዋነኛ ተግባራቸው:: እነዚሁ ባለሞያዎች የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረግ: ማህበሮችን (የሴት ልማት ማህበር ለምሳሌ): ሴቶች እርስበርሳቸው ስለጤናቸው እንዲወያዩ ያለመ ቢሆንም የኢህአዴግ አባላት በመመልመል: በእድር ለቅሶ ቤትና ሌሎች ሰዎችን የሚያሰባስቡ ሁነቶች ላይ አገዛዙን በመካብ ህዝቡ ዘንድ ጉጉት እና ቅዤት በመፍጠር ቀላል የማይባል አገልግሎት ይሰጣሉ-ለአፋኙ አገዛዝ:: ሴቶችን በልማት ሊግ ስም በአባልነት መዝግበው የገዥውን ፓርቲ አባልነት መታውቂያ ያድላሉ:: የኢህአዴግ አባላት ቁጥር በአንዴ እንዲያሻቅብ በማድረግ በኩል የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ድርሻ ቀላል አይደለም-በግዴታ የሚመዘገቡ አባላትን በማበራከት::

በዚሁ የቤት ለቤት ተግባራቸው የመቃወም አዝማሚያ የሚታይበትን እንዲሁም የገዥው ፓርቲ አሰራር ልክ እንዳልሆነ የሚያወራ ማንኛውም ሰው ይጠቆራል: ይታሰራል: ይታፈናል: ማስፈራሪያዎች ይደርሱታል: እንዲሸማቀቅና በቀጣይ ከአፉ ቆጠብ እንዲል ይደረጋል:: በአገርአቀፍ ምርጫ ወቅት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ከምረቃ እንደወጡ ዋና ስራቸው ቤት ለቤት እየዞሩ የስልለላና ኢህአዴግን ምረጡ የሚል ሰፊ ቅስቀሳን ማድረግን እንጅ ከጤና ጋር የተያያዘ ስራ መከወን አልነበረም:: ጎርቤት በጎረቤቱ ላይ እንዲመስክር ይበረታታል:: ህዝቡ እርስ በርሱ ተፈራርቶ በሕብረት እንዳይቆምና መሰረታዊዎቹን የንፁህ መጠጥ ውሃ እና የሽንት ቤት ፅዳትን በተመለከተ እንኳን ማውራትን እንዳይደፍር ማሸማቀቅ ይደርስበታል::

በቅርቡ አሰቃቂ አደጋ በደረሰበት በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሃያ ሁለት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያወች ይንቀሳቀሳሉ-እስከአምና በነበረው ቁጥር:: ላለፉት ዘጠኝ አመታት እነዚሁ ባለሞያወች የቆሼን አካባቢ አሰቃቂ አደጋ ሊታደግ የሚችል ዘገባ አላቀረቡም:: ሰውን የሚቀርቡት ለሌላ አላማ ስለሆነ ገዥውን ፓርቲ ለማዳን ብለው ሕዝቡን አደጋ ላይ ጥለውታል::

ህዝቡ ደሞዛቸውን ይከፍላል: በምላሹም ሲሸማቀቅ ይውላል:: በአንድ ለአምስት አሰራር ተጠርንፎ ተቃውሞ ማሰማትን እንደጦር ይፈራል:: አዲስ አበባ አሁን ያለችበት የዝምታ ድባብ አንዱ ምንጭ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ትሩፋት ነው::
የአንዲት የዋህ ፀሐፊ ገጠመኝ

ገዥው ፓርቲ መቶ ከመቶ መድፈን ልምዱ ስላደረገው የጤናው ዘርፍም የቁጥር ጨዋታው በተዋረድ ደርሶታል:: እቅድና ክንውን በሚመዘገብበት ወረቀት ያቀድኩትን በሙሉ አሳክቻለሁ በማለት እንድትሞላ የተነገራት አንዲት ካድሬ ወደ አንድ ጤና ጣብያ በመሄድ ፀሐፊዋን ሁሉንም መስመሮች መቶ ስትል እንድትሞላ: አድካሚ እንዳይሆንባት ግን አንድ ጊዜ መቶን ፅፋ የቀሩትን በአንዳፍታ የምትሞላበትን አሰራር ታሳያታለች:: ነገሩ ወዲህ ነው: ቤት ውስጥ ስትወልድ የሞትች እናት እና በወሊድ ምክንያት የሞቱ ሕፃናት ቁጥርን በተነገራት መሰረት የታቀደው ከተሳካው አንፃር መቶ እንደሆነ ሞልታ ዘገባውን ትልካለች:: ታዲያ ስኬት ማለት ሁሌ መቶ መድፈን ሳይሆነ ዜሮም ዋጋ እንዳላት ያልተረጠረችው ሰራተኛ በሌሎች የጤና ባለሞያዎች ዘንድ መደናገጥን ፈጥራ ነበር::

ወደቁምነገሩ ስንመለስ ገዥው ፓርቲ ግብረሰናይ ድርጅቶችን ከአገር በማስወጣቱ በጤናው ዘርፍ እየተከሰቱ ያሉ ክፍተቶችን በሌላ ፅሁፍ የምንመለስበት ቢሆንም የኤች አይ ቪ ከእናት ወደልጅ መተላለፍ: የእናቶች በወሊድ ወቅት መሞትና: የሕፃናት ከአምስት ዓመት በፊት ሞት መበራከት የጤናው ዘርፍል ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል::

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሀገራቸውን ሳያድኑ አለምን ለማዳን የምረጡኝ ዘመቻቸውን ባጧጧፉበት በዚህ ሰዓት የኮሌራ ወረርሽኝን በአተት ስም እያስቀየሩ የፈፀሙት የፓርቲ ታማኝነት ዋጋ ሊያስከፍላቸው እንደሚችል የዚህ ፅሁፍ አርቃቂ ቢያምንም: በቀሩት ጥቂት ቀናትም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የግለሰቡን ተያያዥ ወንጀሎች በማጋለጥና ሃገራት ድምፃቸውን ኢንዱነፍጉት ጥረቱ ይቀጥል እላለሁ::
====

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here