በእውቀቱ ዘኢትዮጵያ
ሰኔ 2 ፤ 2009 ዓ ም
በአሁኑ ወቅት የአገራችን የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ የሆነበትና የአገራችንም ህዝብ ከባድ መከራና ፍርሃት ውስጥ የተዘፈቀበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል፤ የአገሪቱ ሁኔታ ከፍተኛ ሥጋት ላይ መሆኑን ለችግሩ ዋና ምክንያት የሆኑት የወያኔ ገዢዋች እንኳን ሳይቀሩ አገሩ በእሳት ሊቃጠል እንደሚችል በግልፅ እየተናገሩበት ያለ ጉዳይ ነው። ይህ ሁኔታ አገርን በሚጎዳ መንገድ እንዳይሄድ ለማድረግ የምሁራን ድርሻ በጣም ከፍተኛ መሆን ይገባዋል። የአማራውና የኦሮሞ ህዝብያነሱት የፍትህና የእኩልነት ጥያቄዋች በአገሪቱ ገዢዎች መሀከል ዘንድ ከፍተኛ ትርምስ የፈጠረና ሁኔታውም በየት አቅጣጫ እንዲሚሄድ ለማወቅ በሚያስቸግር በመንታ መንገድ ላይ እንገኛለን። የኢትይጵያ ህዝብም የወያኔ የእሳት ማገዶ እንዳይሆን ትልቅ ሥራ ከፊት ለፊት ተደቅኗል። በአማራው ህዝብ የተፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለው ከባድ ግፍና መከራ በአማራው ህዝብ ውስጥ ኃይለኛ ብሶትን ፈጥሯል። ነገር ግን ይህ ብሶት ወደ በጎ ድል እንጂ ወደ ሽንፈት እንዳይሸጋገር ትልቅ ሥራ ያስፈልገዋል።
ሙሉውን ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ
————
መጣጥፍ በዚህ ገጽ ለማውጣት ከፈለጉ በ info@borkena.com ወይንም editor@borkena.com ይላኩ። ትንታኔዎችን እና መረጃዎችን ለማግኘት የፌስ ቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ።