spot_img
Friday, June 21, 2024
Homeአበይት ዜናከቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን የድረሱልን ጥሪ

ከቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን የድረሱልን ጥሪ

ነሃሴ 11 ፤ 2009 ዓ ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ካህናት ወንድሞች ዲያቆናት የክርስቶስ ቤተሰቦች።

በካናዳ በመጀመሪያ የተመሰረተው የቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ዜና ወደ እናንተ ሳደርስ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው። እሁድ August 6, 2017 ወይም ሀምሌ 30,2009 አ.ም የእመቤታችንን የፍልሰታ ጾም ለመጀመር በዋዜማ ላይ በነበርንበት ሰአት በብፁእ አቡነ ማትያስ በቀሲስ ሀይለማርያም (Derrick Fagan)አና በቀሲስ ተክለ ድንግል ምእመናንን የመከፋፈል ዘመቻ በተበረዙ የቦርድ አባላት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ረብሻ ተነስቷል።

የቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ ገብረ ሚካኤል የክህነትን ስልጣን ቤተክርስቲያኒቷን ከመሰረቷት ከተወዳጁ አባታችን ከብፁእ አቡነ ይስሀቅ ተቀብለው ሲያገለግሉንና ሲመሩን ቆይዋተል። በዚህም የአገልግሎት ዘመናቸው ቤተክርስቲያን አንዲት ናት በማለት ሁሉንም አባቶች እንዲባርኩንና እንዲያገለግሉን በመጋበዝና እሳቸውም በሁሉም ቦታ በመገኘት ለሁሉም አባቶች ያላቸውን ከበሬታና ፍቅር አሳይተዋል።

ይህ በቶሮንቶ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ቤተክርስቲያን ዛሬ ግን በታላቅ ፈተና ውስጥ ወድቋል። ይኸውም

1ኛ. ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሀይለ ማርያም(Derrick Fagan)ከ20 አመታት በፊት በዚሁ ቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ከብፁእ አቡነ ይስሀቅ ድቁና ተቀብለው ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው በዚሁ ቤተክርስቲያን ማገልገል ጀምረው የነበሩ ሲሆን ባሳዩት የስነምግባር ችግር በብፁእነታቸው የመወገዝ እድል ገጥሞአቸው ነበር። ቀሲስ ሀይለ ማርያም(Derrick Fagan) በጊዜው ከጥፋታቸው ታርመው ብፁእ አቡነ ይስሀቅ ውግዘቱን እንዲያነሱላቸው ከመጠየቅ ይልቅ በማን አለብኝነት ወደ አሜሪካ በመሄድ ቅስናን ተቀብለዋል ።

ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሀይለ ማርያም(Derrick Fagan) ከአሜሪካ ተመልሰው የየመጀመሪያ ስራቸው የአደረጉት ከቀሲስ ተክለ ድንግል ጋር በመሆን የቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያንን ህንፃ በድንገት መጥተው የመንጠቅ ሙከራ ነበር። ይህውም በጊዜው በፖሊስ ሀይል ከሽፏል። ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሀይለ ማርያም(Derrick Fagan) ቅስና ከተቀበሉ በኋላ ትዳራቸውን ሁለት ጊዜ ያፈረሱ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የፈረሰውን ጋብቻቸውን የመሰረቱት በግብፅ ቤተክርስቲያን ነበር። የሳቸው ድርጊት ተባባሪ የሆነው ቀሲስ ተክለ ድንግልም አሁን በሁለተኛ ትዳር ላይ ይገኛሉ።

ይህን ሁሉ እያወቁ ብፁእ አቡነ ማትያስ እነኚህን ሁለት ቀሳውስት በቅስና አገልግሎት ውስጥ ሆነው እየፈቱና እያገቡ ቤተመቅደሳችንን እንዲያረክሱ መፍቀዳቸው አልበቃ ብሎ በቶሮንቶ ውስጥ ከእነርሱ በስተቀር ካህን የሌለ ይመስል ሁለት ጊዜ ፈትቶ ያገባ ሰው በሊቀ ካህንነት መሾማቸው አላማው ምን ይሆን?
2ኛ የቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያንን ለረጅም ዘመን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሲያገለግሉ የቆዩትን ቀሲስ ገብረ ሚካኤል ወደ ጎን ትተው በማን አለብኝነት ብፁእ አቡነ ማትያስ የቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያንን

ከዚህ በኋላ በእኛ አስተዳደር ስር ነው መጥተንም እንደገና ህንፃውን እንባርካለን የሚል ደብዳቤ በመላክ ለህንፃው እንጂ ለምእመናኑ ደንታ የሌላቸው፣ ለዘመናት በፍቅር በኖሩ ወንድማማቾች መካከል ከፍተኛ ጠብና ጦርነት ሲያነሱ ለሰው ልጆች ህይወት ምንም ዋጋ የማይሰጡና ህንፃ ቤተክርስቲያን ለመቆጣጠር የትኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ አሳይተዋል።

በካናዳ በብፁእ አቡነ ማትያስ የአስተዳር ብልሹነትና ህዝብን የመከፋል አካሄድ ስንት አብያተ ክርስቲያናት በሳቸው አመራር በተመረሩ ሰዎች እንደተመሰረቱ ሁሉም ያውቀዋል። አሁን እነኚህ አብያተ ክርስቲያናት ያሉበትን ጥንካሬ ስናይ የአምላክን ስራ የማያደንቅስ ማን አለ።

የእዚህ ፅሁፍ አላማ የአባቶቻችንን ገበና ለመግለፅ ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ አባቶች ካህናትና ምእመናን በሙሉ በብፁእ አቡነ ማትያስና በመልከተኞቻቸው በቶሮንቶ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንድትረዱና ዘወትር በፀሎታችሁ እንድታስቡን እየጠየቅን በቶሮንቶና በአካባቢው ያላችሁ ምእመናን እነኚህ ከስርአተ ቤተክርስቲያን ውጪ ያሉ ቀሳውስት (ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሀይለ ማርያም(Derrick Fagan) ና ቀሲስ ተክለ ድንግል) መቅደሳችንን እንዳያረክሱና በብፁእ አቡነ ማትያስ ምትክ ለበጎቹ የሚራራ እውነተኛ አባት ምእመኑ እንዲያገኘ በምናደርገው እንቅሰቃሴ ከጎናችን እንድትቆሙልን እንጠይቃለን። 1ኛ ጢሞ ምዕ 3 ቁ 1-5 ኤጲስ ቆጶስ የአንድ ሴት ባል የሆነ እንዲሆን አያዝምን? እንዲሁም ቲቶ ምዕ 1 ቁ 5-7 የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ወይም ካህን የአንድ ሚስት ባል የሆነ ይላል።
___
ማሳሰቢያ ከድረ ገጹ : ይሄ መረጃ ጉዳዮ ይመለከተኛል ከሚሉ ግለሰብ የተላከ ነው። አስተያየት ያደረሱንን ግለሰብ በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ ማግኘት ይቻላል። icareformychurch@gmail.com

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here