spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትየወያኔ ሴራ በ ደቡብ ኮርያ በስደተኞች የተመሰረተው መሐበረ ማሪያም ዉስጥ ሲጋለጥ(የትናየት መልካሙ)

የወያኔ ሴራ በ ደቡብ ኮርያ በስደተኞች የተመሰረተው መሐበረ ማሪያም ዉስጥ ሲጋለጥ(የትናየት መልካሙ)

- Advertisement -

ነሃሴ 30 2009 ዓ ም

“ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ፤ወይም ያሸንፍሃል፤ ቤተክርስቲያንን ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ትዋጋለች፤ተሸንፋም አታውቅም፡፡ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

መሐበረ ማሪያም በ ደቡብ ኮርያ በስደተኞች ስመሰረት እጅግ በጣም ልብ በሚነካ አሳዛኝ ሁኔታ ነበር። መሐበሩን ከመሰረቱት ፩፪ ሰዎች አንዱዋ አህታቸው በስደት ባረፈችበት ወቅት ፈጣሪያቸው በስደት ሃገር አንዲያስባቸው አንዲያበረታቸው በመከራና በወጀብ ጊዜ ፈጣርይ ብሪታቱና ጉልበቱን አንዲሰጣቸው ስሙን ለማሰብ በየቤታቸው በጸበል እና ጻዲቅ መልክ የጀመሩት መሃበር አድጎ ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ዉሲጥ ለሚኖሩት ክርስቲያኖች መሰባሰብያቸው ሊሆን በቅቱዋል። መሃበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስክ ቅርብ ጊዜ ድረስ እጅግ በሚያስቀና እና በሚያስደምም ሁነታ በርካታ ተግባራትን ሲያከናዉን ቆይቱዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም የሚለው ወያኔ ለትምህርት ወደ ደቡብ ኮሪያ በምልካቸው አባላቱ በኩል መሃበሩ ግራ የተጋባና ያልተግባባ በማድረግ በራሱ ሰሪጎ ገቦች በኩል የመሃበሩን አካሄድ ጠምዝዞ ወደሚፈልግበት አቅጣጫ ለመምራት ኢንድሁም ሰው እንቅልፉን አቶ አካሉን አጉድለው መከራዉን እየበላ ለቤተክርሲቲያን ማሰርያና ሙዳዬ ሚጹዋት የሚሰጠዉን ገንዘብ ለመቀራመት ወኪሎቹን አስከ መሃበሩ አመራር በማስረግ ከቻለ ከኢምባስው ቀጥለው መሃበሩን ሁለታኛ ቆንጽላ ጺፈት ቤት ለማዲረግ ካልሆነ ፊርኪስኪሱን ለማውጣት ተግቶ እየሰራ ይገኛል።

ድሮ ሰው ስማርና ስመራመር ለሃገር ዋልታና ማገር ይሆናል በአሁን ሰዓት ግን ወያኔ በራሱ ልክ ሰፊቶ የምያስተምራቸው ተማርዎቹ እንደ ዕንቦጭ አረም የሚለመልመዉን የሚያምረዉን ሁሉ ማጥፋት ስራቸው አደርገዉታል።ይህን ግዜ መማሩስ ምን ይተጠቅማል ብለን ልንጠይቅ አንችላለን። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደዚህ ቢሎ ይመክረናል ተወዳጆች ሆይ፦ ጥበባችሁ ለሥጋችሁም ለነፍሳችሁም የሚጠቅም እንጂ በዚህ ዓለምም ይኹን በሚመጣው ዓለም የሚጎዳችሁ አይኹን፡፡ ነገር ግን የወያኔ ተላላክ ምሁራኖች ዛሬን መኖር እንጅ ነገን ማሰብ ያልፈጠረባቸው ዱኩማን የተማሩትን ትምህርት ለተንኮል እና ለጉዳት ይጠቀሙታል። የሰማያዊ እሳቤያቸውን ከአፈቸው እንጂ ከልባቸው መንግለው ጥለዉታል። አንዳንዴ ሳስባቸው ወያኔ ሆይ በደደቢት የምትኖር ብለዉ ልማታዊ ጸሎት ሁላ የሚያደርጉ ይመስሉኛል። አሁን ጥያቄው በተለያየ አለም ላይ የምትኖሩ ኦርቶዶክስ ክርሲቲያኖች መሃበሩን የመታደግ ሃላፊነት አለባችሁ። ወያኔ መሃበሩን የደደቢት ክፊለ ጦር ለማድረግ የቀራት ጊዜ በጣም አጭር ነው። ስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ ዉስጥ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይመርጣቸው በራሳቸው ስልጣን ዋያኔዉያንን የሰገሰጉት ሳያንስ የማሃበር ደንብ አዘጋጅተናል በሚል ሺፋን ገና ህዝበ ክርስትያኑ ያልተወያየበተን ደንብ የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ በራሱ አጽድቁዋል በማለት መሃበሩን ከመጀመሪያው የመሰረቱትን ነባር ኮሚቴ አባላት በማሰናበት በቁዋምነት የወያኔ አባላተን በመመደብ አስከዛሬ የተሰበሰበውን ገንዘብ እጃቸው ለማስገባትና ሃገር ቤት ልማት ይከናወንበታል በሚል ሰበብ ገንዘቡን የዉሃ ሽታ ለማድርግ ዝግጅታቸዉን ጨርሰው እነሱ እንደምሉት የይስሙላ ምርጫ ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

ንቁ መሃበሩን እንታደግ።

የ እግዚሃብሄር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል

ጸሃፊዋን በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ ማግኘት ይቻላል ፤ melkamuyetnayet@yahoo.com

———
ጽሁፍ በዚህ ገጽ ላይ ለማውጣት ወይንም መረጃ ለማቀበል በ editor@borkena.com ኢሜይል ማድረግ ይቻላል

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here