ህዳር 29 2010 ዓ ም
የአፋር ነጻ አውጭ ግንባር (አርዱፍ) ትላንት በላከው መግለጫ የህወሓት ሰራዊት ከክልሉ ልዮ ኃይል ጋር በመቀናጀት የአርዱፍን ተዋጊዎች ከአካባቢው ለማጽዳት በሚል በከፈተው ጥቃት በሞጎሮስ አካባቢ ለቀናት የዘለቀ ጦርነት እንደተካሄደ በመግለጽ አስራ ሰባት ያህል የህወሓት ሰራዊት ገድየ በርካቶችን አቁስያለው ብሏል።
“ህወሓት እና የአፋር ልዮ ኃይል አርዱፍን ከአካባቢው ለማስለቀቅ የተጀመሩት ዘመቻ በክልሉ ያለውን የጸጥታ ችግር ያባብሰዋል” በሚል ርዕስ ባሰራጨው በዚሁ መግለጫ ዘመቻው ይፋዊ ያልሆነ ግቦች ነበሩት ብሏል። ለአውሮፓውያን ቱሪስቶች አካባቢው የጸጥታ ዋስትና እንዳለው ማሳየት ፤ በሶማሊ ክልል በአብዲ ኤሊ እንደተደረገው ሁሉ በአፋር በአንድ የአፋር ጎሳ የበላይነት የሚመራ የክልል ፖሊስ አጠናቅሮ ለማዋቀር እና በክልሉ በዲ የሚል አዲስ ስድስተኛ ዞን ለማዋቀር ሁኔታውን ማመቻቸት ይፋ ካልሆኑት ግቦች ውስጥ ናቸው በማለት መግለጫው አክሏል።
በመቀጠልም የውጭ ዜጎች ወደ አፋር አካባቢ እንዳይጓዙ እና በአካባቢው ያሉ ግዙፍ የውጭ የንግድ ተቋማት እና ባለሃብቶች ለደህንነታቸው አካባቢውን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ መክሯል።
በተያያዘ ዜና አንድ የጀርመን ቱሪስት በአፋር ከልል እርታሌ ወረዳ በታጣቂዎች መገደሉን ተከትሉ የካናዳ እና የእንግሊዝ መንግስታት ዜጎቻቸው ወደ አፋር ክልል እንዳይጓዙ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
አርዱፍ በእንግሊዝኛ ያወጣውን መግለጫ እዚህ ላይ በመጫን ማግኘት ይቻላል
——
ቦርከናን በፌስቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ