በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ወያኔ የሚፈልገውን ይዞ ችግሩን ፈትቻለሁ ይላል ፤ ብአዴንም ይሁንልህ ብሎለታል። ወልቃይቴዎቹስ ምን ይላሉ?

ታህሳስ 7 ፤ 2010 ዓ ም

ወልቃይት ጠገዴን ህወሓት ስልጣን ከያዘ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ከልሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግሪኛ ተናጋሪዎችን ቢያሰፍርም ፤ ከዚያ በፊት ወልቃይት የጎንደር ሁነኛ አካል እንደነበር ህወሓት ራሱ ሊክደው የማይችለው ሃቅ ነው። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ጉዳዮ በስፋት ባይታወቅም ትግሬነት በጉልበት ተጭኖብናል በሚል ወልቃይትን ወደ ጎንደር ለማስመለስ በተደረገው ትግል ብዙ መስዋዕትነት እንደተከፈለ ጉዳዮን የሚያውቁ ሰዎች ያስረዳሉ። በዚህም የተነሳ ህወሓት ብዙ የወልቃይት ሰዎችን በግፍ እንደገደለም ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ጉዳዮ ሃገራዊ መልክ ከያዘ በኋላ ህወሓት በጉልበት የወሰደውን መሬት ለሁለት ክፍሎ አንዱን ክፍል ለትግራይ አንዱን ክፍል ለአማራ ሰጥቸ ችግጉን ፈትቻለሁ ብሏል። ብአዴንም እንደተስማማ እና ችግሩ እንደተፈታ የተቀበለ ይመስላል። ይሰራል ወይ? ይኼ ኢንተርቪው ግሩም እይታ አለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.