spot_img
Wednesday, June 7, 2023
Homeአበይት ዜናቴዲ አፍሮ በባህርዳር ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ፈቃድ አገኘ

ቴዲ አፍሮ በባህርዳር ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ፈቃድ አገኘ

- Advertisement -

ቴዲ አፍሮ Teddy Afro
ጥር 4 2010 ዓ ም

ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በባህር ዳር ስታዲየም ሰማኒያሺህ ሰው በሚይዘው ስታዲየም የሙዚቃ ኮንሰርቱን በጥር 12 ቀን ለማቅረብ ከክልሉ እና የከተማዋ መስተዳድር አካላት ፈቃድ አግኝቷል። የሙዚቃውን ድግስ “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ” በሚል ሰይሞታል። ትላንት በፌስ ቡክ ገጹ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል።

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ”
የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር

ቅዳሜ ጥር 12 ቀን በአማራ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው በውቧ ባሕር ዳር ከተማ ከ80 ሺሕ ሕዝብ በላይ ማስተናገድ በሚችለው በታላቁ ብሄራዊ ስታዲየም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር የሙዚቃ ዝግጅቴን እንዳቀርብ ለአማራ ክልላዊ መንግስት፣ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችንን አቅርበን የነበረ ሲሆን ፤ ጥያቄያችንን የተመለከቱት ሁሉም አካላት ያለ አንዳች ቢሮክራሲና እንግልት በጠየቅነው ቦታና ዕለት የሙዚቃ ድግሳችንን ለቱሪስት መስህቧ ባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፣ ከመላው የአገራችን ክፍል ለሚመጡት የሙዚቃ አፍቃሪዎችና አለም አቀፍ ቱሪስቶች ማቅረብ እንድንችል የፈቀዱልን በመሆኑ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል።

እኔም ወደ ሙዚቃው አለም ከገባሁበት በተለይም የመጀመሪዬ አልበሜ ከሆነችው አቡጊዳ ጀምሮ በቅርብ እስካሳተምኩት 5ኛው አለበሜ “ኢትዮጵያ” ድረስ ከፍተኛ ፍቅር የለገሰኝን የሙዚቃ አፍቃሪ ለማስደሰት ከአቡጊዳ ባንድ ጋር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስንሆን፤ ቅዳሜ ጥር 12 ቀን ለመገናኘት ያብቃን እላለሁ።

ከሁሉ አስቀድሞ ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ ፈቃዱ የሆነውን ቅዱስ እግዚአብሄርን ክብር መስጋና ይድረሰው እያልኩ ፤ ለጥያቄያችን አወንታዊ መልስ በመስጠትና ጥር 12 ቀን የምናቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉልን፡

ለአማራ ክልላዊ መንግስት
ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት

በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጋችሁት ለባሕር ዳር ከተማና አካባባዋ ወጣቶች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይህ የሙዚቃ ዝግጅታችን በሌሎችም የአገራችን ከተሞች የሚቀጥል ሲሆን ጊዜው ሲፈቅድ ዝግጅታችንን የምናቀርብባቸውን ቦታዎችና ቀኑን እናሳውቃለን።

ባሕር ዳር ጥር 12 ቀን በታላቁ ብሔራዊ ስታዲዬም በሰላም ያገናኘን!

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,879FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here