ቦርከና
ጥር 5 2010 ዓም

ምንጭ : ማህበራዊ ድረ ገጽ
የፋሲል ከነማ እና የመቀሌ ከነማ የእግር ኳስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ከተጠናቀቀ በኋላ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በቴድሮስ አደባባይ በሚጨፍሩበት ጊዜ የየፌደራል ፖሊስ ችግር በመፍጠር የፋሲል ከነማን ደጋፊዎችን እንዳሰረ በማህበራዊ ድረ ገጽ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የፋሲል ከነማ ማሊያ የለበሱ ደጋፊዎችን በጂምላ እንዳሰሩ ነው የተሰማው። የፌደራል ፖሊስ እያሰረ በነበረበትም ወቅት “ወያኔ ሌባ” የሚል መፈክር ተሰምቷል ይላል የማህበራዊ ድረ ገጽ ዘገባ።
የአርቆ አሳቢው እና ጀግናው የኢትዮጵያ ንጉስ የአጼ ቴዎድሮስ ሁለት መቶኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ነገ ስለሚከበር የዛሬው የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ጨዋታ ከፋሲል ከነማ ደጋፊ ውጭ ያሉትንም ኢትዮጵያውያን ትኩረት ስቦ የፋሲል ከነማ ደጋፊ አድርጓቸዋል። የፋሲል ከነማ አጼዎቹ በመባልም ይጠራል በደጋፊዎቹ። ደፋፊዎች የአጼ ቴዎድሮስ ምስል ያለበት ከነቴራ በመልበስ ይታወቃሉ።
የዛሬው ጨዋታው ከመቀሌ ከነማ ጋር መሆኑ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ከመሳቡም ባለፈ የፋሲል ከነማ ደጋፊ እንደሆኑም ተሰምቷል።
ዛሬ የፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ አድርጓል በተባለው የጂምላ አፈሳ ከፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ውጭ በመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ላይም አፈሳ ስለመደረጉ የተሰማ ነገር የለም።
———
ዜናውን ያጋሩት። ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ