spot_img
Saturday, September 23, 2023
Homeነፃ አስተያየት“እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል (ይፈጸማል።)” ከታምራት ይገዙ

“እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል (ይፈጸማል።)” ከታምራት ይገዙ

advertisement

ከታምራት ይገዙ
ጥር 23 2010 ዓ ም
በፒ ዲ ኤፍ ፋይል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Enkulal እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል የአገራችን የፖለቲካ ቀውስ በየሴኮንዱ እየተለዋወጠ መሆኑን ሁላችንም እየተመለከትነው ነው ትላንትና ወዲያ ኢትዮጵያዊነት ያንገሸግሻቸው የነበሩት አቶ አባ ዱላ ቡዙዎቻችን ኢትዮጵያኖች ዘንድ ተጠልተው ነበር ትላንትና የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ባስነሱትና ባቀጣጠሉት ኢትዮጵያዊነት አቶ አባ ዱላም በተወሰነ ደረጃ ከህወሀት ነጻ ወጥተው ታይተው ነበር ዛሬ ደሞ ከወጡበት ከህወሀት ብብት ተመልሰው ሲገቡ እየተሰተዋለ ነው እኔ ለአቶ አባ ዱላ የምላቸው ነገር ቢኖር እናቶቻችን “አውቀሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” የሚለውን አባባል ነው::

በሌላ በኩል ደሞ የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች መፈክራቸው “ለአገራችን ለኢትዮጵያ ነጻነት የምንታገላውና መሰዋትነትን የምንከፍላው እኛ ድሉ የእግዚአብሔር ነው” ብለውና ተማምለው ትግላቸውን ሲያፋፍሙ ሁኔታው ያላማራቸው አሊያም ከሶስት ወረ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደሳለኝ ሀ/ማርያም ከህወሀት ድህነቶች በተሰጣቸው ትእዛዝ ከሃያ የሚበልጡትን ባለ ስልጣኖች በሙስና ሊከሱ ነው የምባለውን ወሬ የሰሙት አፈ ጉባዪ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በድንገት ተነስተው” የሕዝቤ ክብር በመነካቱ አሁን ባለሁበት ደረጃ ሥራዬን ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስለሌሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ በማለት” ከአፈ ጉባዔነታቸው ለመነሳት ለኢሕአዴግና ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) መልቀቂያ አስገቡ:: ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም አቶ አባዱላ ገመዳ መደበኛ የፓርላማ አፈ ጉባዔነት ሥራቸውን ጀምረዋል:: ከጥቅምት ወር መጀመሪያ መልቀቃያ አስገተው አሁን ተመልሰው ስራቸውን እስከጀመሩበት ድረስ አቶ አባ ዱላ ገመዳ ህዝቤና ወገኔ ለሚሉት የኦሮሞ ህዝብ ምን ለውጥ አምጥተው ነው ስራ የጀመሩት?፡፡

እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት    ይጠፋል በእኔ እምነት አቶ አባ ዱላ በዚያ ወቅት የስራ መልቀቅያ ያስገቡት ምክንያት አንድም የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ከኢሃዴግ/ህወሀት ጋር የተያያዙት ትንቅንቅ አስፈርቶቸው ከዝብ ጋር ለመወግን አስበው ሲሆን በሌላ በኩል ደሞ የስራ መልቀቅያ ያስገቡት በሙስና ከመከሰሳቸው በፊት ስለሆነ የምትከሱኝ ከሆነ ስራዪን በመልቀቄ እጸናለው ብለው በሙስናው እንደማይከሰሱ የተደራደሩበት ሁኔታ ነው የሚታየኝ ምክንያቱም አቶ አባ ዱላ ሲናገሩ ስራ ለምልቀቅ ያነሳሳኝ ” የሕዝቤ ክብር በመነካቱ”የምል ቃል ተጠቅመዋል ታዲያ የት ጋ ነው ስልጣን ከለቀቁ የሳምንታት እድሜዎችም ቢሆኑም ምን ሰሩ? ስንት የኦሮሞ ህዝብን ከእስር አስፈቱ? ያለጥፋታቸው በመንግስት ጥይት በግፍ ለተገደሉትን የኦሮሞ ልጆች ገዳዮቻቸውን ለፍርድ ቤት አቅርብበውና አስፈርደው ነው ወደ ስራቸው የተመለሱት? ፍርዱን ለህዝባችንና ለራሳቸው ሒሊና እተዋለው:: በእኔ እምነት ኢህኣዴግ/ ህወሀት አቶ አባ ዱላን ላለፉት ሀያ አምስት አመታትም ይሁን ወደ ፊትም የሚጠቀሙባቸው ግሪኮች ከትሮይ በር ላይ እንዳስቀመጡት የእንጨት ፈረስ ነው:: ስለሆነም ለህዝባችንና ለአገራችን ነው የተሰለፍነው ለሚሉት የኦሕዴድንና ብአዴንን ከፍተኛ አመራሮች የማስተለልፈው መልእክት ተማሪዎች በነበራችሁበት ግዜ የሰማችሁትን የግሪክን አፈታሪክን ነው ላስታውሳችሁ የምፈልገው ምክንያቱም ታሪኩ የሰሞኑን የኢህአዴግ/ህወሀትን የማጭበርበር ፖለቲካ ጫወታ ጋር ይመሳሰላል ብዪ ስላሰብኩ :: እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት   ይጠፋል

ቡዙዎቻችን የግሪክን አፈ-ታሪክን እንደምናስታውሰው ግሪኮች ትሮይን ወረሩ። ትሮይ የግሪኮችን ጥቃት ገትራ ተቋቋመች። ምሽጓን መስበር አልተቻለም። ትሮይ የማትደፈር መሆኗን ለማስታወስ በአቴና የጦርነት አምላክ ስም፤ግሪኮች ትልቅ የእንጨት ፈረስ ሰርተው ከትሮይ መግቢያ በር ላይ ጥለውት በርቀት የሸሹ መስለው ተደበቁ (ህወሀት ትግራይ ላይ ለአራት ሳምንት እንደመሸገው) ። ምንም እንኳ የትሮይ ዜጎች የሆኑት ላኦኮንና ካሳንድራ፤ ፈረሱ የትሮይን በር አልፎ እንዳይገባ ቢከራከሩም፤ የትሮይ ሰዎች የጦርነት አምላካቸው መታሰቢያ የሆነውን ይህን የግሪኮች የእንጨት ፈረስ ስጦታ በራቸውን ከፍተው አስገቡት። ሌሊት ላይ በእንጨቱ ፈረስ ሆድ ውስጥ፤ ተደብቀው የነበሩት ግሪኮች ወጥተው የትሮይን ቅጥር በር ከፈቱት (አቶ አባ ዱላና አቶ በረከት)። በርቀት ተደብቀው የነበሩት ግሪኮችም(በትግራይ የመሸጉት የህወሀት መሪዎች) በፍጥነት ተመልሰው በተከፈተላቸው በር ገብተው ትሮይን ደመሰሷት። ጠላትን በውስጡ ተሸክሞ የነበረውን ፈረስ በፈቃዳቸው ወደ ከተማቸው ያስገቡት ማስተዋል የተሳናቸው የትሮይ የራሷ ዜጎች ነበሩ (የኦሕዴድንና ብአዴንን መሪዎች )።

እዚህ ላይ መልእክቱ ለኦሕዴድንና ብአዴንን መሪዎች ሲሆን ድርጅታችሁን ከአሁን ቦሃላ ለአቶ አባ ዱላና ለአቶ በረከት እንዲሁም ለህወሀት ሰዎች ክፍት አታድርጉ የሚለው ላይ ነው:: ምክንያቱም ህወሀት መራሹ አቶ አባ ዱላን በኦሮሞ ስም ያስቀመጣቸውና እንደፈርስ የሚጋልባቸው ሰው ሲሆኑ: የሻቢያው መንግስት ደሞ አቶ በረከትን በአማራው ስም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያስቀመጣቸው የሻቢያ ተወካይ ናቸው ህወሀት ደሞ የራሱን ተወካይ በኤርትራ (በሻቢያ) መንግስት ውስጥ የአቶ አቦይ ስብሀትን እህት በከፍተኛ እርከን ላይ ያስቀመጣቸው:: የአገራችንም የፖለቲካ ጉዞ ውስብስብ ከሚያደርገው አንዱ ይሄው ነው:: በእኔ እምነት “ሻቢያና ህወሀት የሳሎን ጸበኞች የጛዳ ፍቅረኞች እንደሚባለው ነው የሚሆኑብኝ”:: ወደ ተነሳሁበት ስመለስ አቶ አባ ዱላ ወደ ህወሀት ብብት ተመልሰው ይግቡ እንጂ በዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች የተቀጣጠለውን ትግል እይቀለብሰውም ምክንያቱም ከመጀመሪያውኑ እነ አቶ አባ ዱላ ነጻ ወጪዎች እንጂ ነጻ አውጪዎች አይደሉም:: ነጻ አውጪዎቹ የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ናቸው::

እርግጥ ነው ለአቶ አባ ዱላም ይሁን ለሌሎቹ አመራችሮ በግዜው በዛን ሰሞን በተለያየ መንግድ እድናቆቴን ግልጫለው ይህንንም ያደረኩበት ምክንያት አቶ አባ ዱላም ሆኑ ሌሎቹ ከህወሀት ቀምበር ስር ለመውጣት ፍቃደኞች ሆነው ስለታዩኝ እንጂ እነርሱ በአሁን ሰዓት ያለውን ትግል ይመሩታል ከሚል ህሳቤ አይደለም በእኔ እምነት እነርሱ ራሳቸው በዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ትግል ነጻ ወጪዎች ናቸውና :: እንደ እውነቱ ከሆነ አቶ አባ ዱላ አውቀውም ይሁን ተሳስተው ለትግሉ ትልቅ አስተዋጾ አደገዋል ለምሳሌ ብአዴን ስብሰባላይ የተናገሩት “ኦህዴዶችን የመሰረቱት አባላት መታገያ ቦታ ባጡበት ዘመን መታገያቸው የአማራ ህዝብ ነበር የኦሮሞ ታጋዮች መሄጃ ባጡበት ዘመን ሱዳን መሄድ ይችሉ ነበር ነገር ግን ሱዳኖች ኢትዮጵያኖች አይደሉም:: በአማራ ክልል ስንታገል ዘራችንን የጠየቀን የለም ቆንቆችንን የጠየቀን የለም ሲጠይቁን የነበራው ጉዳይ በርቱና ታገሉ እኛም ከናንተ ጋር እንሰዋለን ነበር የሚሉን የነበረው ይህንን ዓይነት አንድነት የፈጠሩ የጥንቶቹ ህዝቦች ናቸው ስለሆነም በዛ ላይ የመስርተን ዲሞክራሲያዊና አንድነቶ የጠነከረች ኢትዮጵያን መመስረት ይገባናል” ይህንን ዓይነት ንግግር የተናገሩት አቶ አባ ዱላ ከዛ ቀን በፊት ኢትዮጵያ የሚለው የአገራችን ስም እሳቸውም ሆኑ አለቆቻቸው በጎሳቸው ስም ለውጠውት ነበር:: አባቶቻችን “እውነት ሰገባ ውስጥ እንዳለ ጎራዴ ነው ይላሉ::” ልዩነታቸው ጎራዴ ተመልሶ ሰገባ ውስጥ ገብቶ ይታፈናል እውነት ግን ከታፈነበት አንዴ ከወጣ እንድ ጎራዴው ተመልሶ በሰገባ ውስጥ አይታፈንም የመራባት ሃይሉ እየጨመረና እየጠነከረ ይሄዳል :: ይህ የአባቶቻችን አባባል ትክክል ለመሆኑ ምስክሩ በልባቸው ደብቀውት የነበረውን የአገራችንን የኢትዮጵያ አገራዊነትና ከድርጅታቸው ከኢህኣዴግ በላይ መሆኑን በአንደበታቸው እንደተናገሩ ነበር በመላው አለም ሲናኝ በሰዓት ግዜ ውስጥ ነበር:: የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር እሳቸው አቶ አባ ዱላ ወደ ህወሀት ብብት ውስጥ ተመልሰው የገቡት ከአንደበታቸው የወጣውን እውነት የሰማን ሁሉ በጣም ተደስተንና አጨብጭበን ሳንጨርስ መሆኑ ነው:: ወደተነሳሁበት ስመለስ ያለፈ ጹሁፊን የቆጨሁት ሌላው ደሞ ዶ/ር አብይ አህመድ የኦሮሞ ክልል ምክትል መስተዳድር በዛ ሰሞን ለአንድ የመገናኛ ሚዲያ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ እንዲህ ብለው ነበር በማለት ነበር “የአማራ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ በሰርገኛ ጤፍ ይመሰላል ሰርገኛ ጤፍ በወንፊት ልትለየው አትችልም ሰርግርኛ ጤፍ አብሮ ይፈጫል አብሮ ይቦካል አብሮ ይጋገራል አብሮም ይበላል ይህ ህዝብ እንዲህ ነው የተዋለደ ህዝብ ነው” ነበር ያሉት ይህንን ሊሚሰማ ኢትዮጵያዊ ላለፉት ሀያ ዓምስት አመታቶች ሰምቶት የማያውቀውን ሲሰማ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ\ም የጎንደር ወንድሞቻችንና እህቶቻችን “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደማችን ነው” የሚለው የመተሳሰብና የአንድነት ስሜት በስልጣን ላይ ያሉትን መሪዎች እንደ ሰው እንዲያስቡ ያስገደደ ነው ብል ከእውነት መራቅ አይመስለኝም:: በክፍል አንድ ጹሁፌ ላይ እንደገለጽኩት አባቴ እኔን ሀያ ዓመት ሲሞላኝ ነበር “አንተ ሰው” ያለኝ የኦህዴድ መሪዎችም ሆኑ የቤአዴን መሪዎች እድሚያቸውን መቁጠር የጀመሩት ኢሕአዴግ/ህወሀትና ስልጣን ከያዘ ከሀያ አምስት ዓመት ቦሓል መሆኑ ነው መሰለኝ ከልጅነት አመለካከት ወጥተው እንደ ሰው ማሰብ ጀምረዋል ሰው ጀምረዋል ሰው ማለት ሰው ለሚባለው ፍጡር ሁሉ የሚያስብ ማለት ነው; ሰው ማለት በዘር; በጎሳ ; በቆንቆ; በሀይማኖት አድሎ የማይፈጽም ማለት ነው:::: “ከሁሉ በላይ ሰው ማለት እምቢ የማለት ምርጫ ያለው ነጻ ማለት ነው” ኦህዴዶችም ሆኑ የብአዴን መሪዎችም ከቅርብ ጊዚያት ቦሃላ ለህወሓት መሪዎች እሚቢተኝነት እያሳዩ መሆኑንን ቡዙ ማሳያዎች እየታዩ ናቸው ስለሆነም ለኦህዴድና ለብአዴን መሪዎችም “የነብርን ጭራ አይዙትም ከያዙትም አይለቁትም” የሚለውን የአባቶቻችንን አባባል ላስታውሳቸው እወዳለው:: በሌላ በኩል ለውጡ እየመጣ ያለው ከአገር ውስጥና ከራሱ ከገዢው መንግስት ካሉ ድርጅቶች ውስጥ ስለሆነ ነው የአንቁላሉን ምስል ያስቀመጥኩት::

እንደእውነቱ ከሆነ ሰሚ አጥቶ ነው እንጂ አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዴ አፍሮ) ከሁሉ ቀደም ብሎ ባወጣው የአንድናትና የአብሮነት አልበሙ ላይ የአንድነትና የአብሮነት ጌዜ እንደሚመጣ ሲጠቁም “ያስተሰሪያል” የሚል ዘፈን ተጫውቶ ነበር ይህንን ዘፈኑን ልብ ላለው ልብ የሚነካ ሰው ለሆነ ሰው መጪውን ግዜ በእርጋታ እንዲመለከት ትምህርት የሚሰጥ ዘፈን ነበር ምን ያደርጋል የን ግዜ የኢህአዴግ ስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ የሚያስቡት እንደ ልጅ የእለት ተለታቸውን ስልጣንና ሆዳቸው ሞልቶ ማደሩን ነበር :: አሁን ሰሞኑን ደሞ ሌላው የፍቅርና የአንድነት ድምጻዊ የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ ሁንዴሳ “ነን ሶቤ” (ዋሸው እንዴ) ይለናል ይህንንና ሌሎች የተቀኛጁ የነጻነት ትግል ስመለከት ልቤ በሀሴት (በደስታ) ይሞላል በሌላ በኩል ደሞ መስከረም 2010 ላይ ባወጣሁት ግልጽ ደብዳቤ ላይ

“ጠፍረን ጠፍንገን እንሰረው ሁለት ሺ አስርን በአንድነት ገመድ
የኢህኣዴግ/የህወሀት መንግስት ወደ ሁለት ሺ አስርሃንድ እንዳይረማመድ” የሚል ከትቤ ነበር::

በአሁኑ ሰዓት የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ያቀጣጠሉትን የልውጥ ብልጭታ የሚቀላቀሉ የቀድሞው የኢህኣዴግ አጋር ድርጅቶች በሙሉ ሊረዱት የሚገባ ነገር ቢኖር የኢህኣዴግ/ህወህት መንግስትን ቢቻል ወደ አገራዊ መግባባት እንዲመጣና አገራዊ መግባባቱ ላይ የራሱን አስተዋጾ እንዲያበረክት ማበረታታት ይህንን ችላ ብሎ የሚያልፍ ከሆነ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት ይጠበቅባቸዋል ምክንያቱም የህዝቡ ነጻነት ከናንተ ከኢህኣዴግ አጋር ድርጅቶች ከኦህዴዶችም ሆኑ ከብአዴን ጋር የተቂራኘ ነው ብላችሁ አምናችሁ መሆን አለበት:: ይህ ሳይሆን ቀርቶ እናንተ የመጣችሁት የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ያቀጣጠሉትን ትግል ለመርዳት አስባችሁ ከሆነ ግን ጊዜያችሁን በከንቱ እያጠፋችሁ ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ:: ይህንንም እምነቴን የሚያጠናክርልኝ በአንድ ወቅት አንዲት የአውስትራሊያ ተወላጅ የሆኑ ወይዘሮ ሲናገሩ

    “If you have come to help me you are wasting your time, but if you have come because your liberation is bound up with mine, then let us work together”
    Lilla Watsoa,
    Australian Aboriginal woman

እንደ እውነቱ ከሆነ የድርጅት መሪዎችም እንደ ድርጅት መሪነታቸው ህዝብም እንደ ህዝብነቱ ከገባንበት ማጥ ለመውጣት ከፈለግን ሁላችንም ይህንን አባባል መከተል አለብን ምክንያቱም አገር ቤት ያሉት ህዝቦቻችንም ሆኑ እኛ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ላለፈው ሀያ አምስት ዓመታት ስንለው የነበረው ነጻነት ነጻነት ነበር:: በሌላ በኩል ሁላችንም እንዳየነውና እንደሰማነው ወንድማችን አቶ አበበ ገላው አቶ መለስ በተገኙበት አንድ ትልቅ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተግኝቶ”ነጻነት ነጻነት””ፍሪ ደም ፍሪ ደም” ብሎ በመጮሁ ነበር አቶ መለስን አንገት ከማስደፋት ባለፈ ህልፈታቸውን ያፋጠነላቸው:: እርግጥ ነው ሰው ይሙት ባይባልም እሳቸው ግን አገርን የገደሉ በመሆናቸው ሲያንሳቸው ነው ቢሆንም ቅሉ በበኩሌ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በአገራችን አገራዊ መግባባት እንዲመጣ ከሚፈልጉት ሰዎች ውስጥ አንዱ ስለሆንኩ መግባባት ለመፍጠር ይቅር መባባል ስለሚያስፈልግ በዚህ አጋጣሚ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሄር የአቶ መለሰን ነፍስ ይማር ላማለት መድፈር አለብኝ ብዪ አስባለው:: በሌላ በኩል ደሞ በውጪ አገር ካሉት የዘመኑ ቄሮዎችና ፋኖዎች አንዱ የሆነውና የለውን ግዜውንና እውቀቱን በመጠቀም ወጪም ሆነ አገር ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ የሆን መረጃ የሚያስተላልፈው ውንድማችን ወጣት ቶሎሳ ኢቢሳ በፌስ ቡኩ ላይ እየተገኘ ለሚያደርገው የማያቆርጥ ወቅታዊ መረጃው ላመሰግነውና አምላካችን ቸሩ እግዚአብሔር እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይሰጠው ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን:: እንግዲህ ሁላችንም እንደምናየውና እንደምንሰማው ሐምሌ 24 2008 ዓ/ም ከጎንደር ህዝብ የወጣው “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው የሚለው ቃል” ከተነገረ ቦሃላ በአገራችን ላይ እየመጣ ያለው …… ይቀጥላል

ጸሃፊውን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል ፤ tamiratkyam@gmail.com

***
ማስታወሻ : በዚህ ጽሁፍ ላይ የተነጸባረቁ ሃሳቦች የጸሃፊውን ሃሳብ ያንጸባርቃሉ። በዚህ ድረ ገጽ ነጻ አስተያየት ወይ ሃሳብ ለማካፈል ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ ይላኩልን editor@borkena.com

ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,681FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here