ቦርከና
ጥቅምት 20 2010 ዓ ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) የሃያ አራት ቀን የድርጂት ግምገማውን ሲያጠናቅቅ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን የድርጅቱ ሊቀመንበር ፤ አቶ ሲራጂ ፈርጌሳን ደሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መመረጡን አስታውቋል።
ድርጂቱ በወቅታዊ ሃገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቻለሁ ብሏል። ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች በክልሉ ያለስጋት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ እና አላማቸው እንዲያስተዋውቁ አደርጋለሁ ብሏል።
በተጨማሪም የኃይለማርያም ደሳለኝን ከድርጂቱ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡን ውሳኔ ተቀብሎ አጽድቋል።
ባለፈው ሳምንት ድርጂቱ ያሳለፈው ውሳኔ በማህበራዊ ድረገጽ ከወጣ ከሰዓታት በኋላ መረጃው እንዲነሳ መደረጉ ይታወሳል። በሰዓቱ የተሰጠው ምክንያትም የድርጂቱ የማህበራዊ ድረ ገጽ ባልታወቁ ሰዎች ተጠልፎ የተለጠፈ ነው። ደኢሕዴን አመራሮችን ገና አልመረጠም የሚል ነው።
የሺፈራው ሺጉጤ በሊቀመንበርነት መመረጥ በተቃዋሚው ጎራ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ እንደነበረ ይነገራል። ምክንያት ተቃውሞ ለበረታበት ህወሓት ሺፈራው ሺጉጤ ታማኝ ናቸው በሚል። ኃይለማርያምን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲተካ ህወሓት ያስመርጠዋል የሚለው አስተያየት ጠንከር ይላል።
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።