spot_img
Tuesday, January 31, 2023
Homeነፃ አስተያየትበመንሰራፋት ላይ የሚገኘው የዘር መድልዎ በኢትዮጵያ፡- የውስጥ ቅኝ አገዛዝና በክልል ደረጃ ያለው...

በመንሰራፋት ላይ የሚገኘው የዘር መድልዎ በኢትዮጵያ፡- የውስጥ ቅኝ አገዛዝና በክልል ደረጃ ያለው የተዛቡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎቹ (ግርማ ብርሃኑ)

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -
Round Trip Flights under $199! Get up to $20 off◊ our fees on flights with promo code RT20

ግርማ ብርሃኑ
ከጎተንበርግ ዩኒቨርሲቲ
የካቲት 29 2010 ዓ ም

በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

(1) መግቢያ

Girma Berhanu -ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ቢባል ማጋነን አይሆን። ሃገሪቷ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በተከታታይ ሁኔታ በተቃውሞዎችና ግጭቶች እየታመሰች ነው። ።አጠቃላይ የህብረተሰቡ መነሳሳትና ብሶት የሚያመለክተን ኢትዮጵያን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ጨቋኝ ጥምር መንግስት ማለትም ከአነስተኛው የትግራይ ክልል በመጣው ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ(ህወሃት) የበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢሀአዴግ) ባለፉት ዓመታት ብሄሮችን በማግለሉ የተፈጠረ የተስፋ ማጣት ድምር ውጤት ነው። አጠቃላዩ ህዝብ በተለይም አማራዎችና ኦሮሞዎች ከሃገሪቷ የፖለቲካ ሂደትና ኢኮኖሚ ልማት በወሳኝ ሁኔታ እንዲገለሉ ተደርጓል። በአሁኑ ጊዜ የሚታየው ግጭትና በስፋት እየተካሄዱ ያሉት ሰላማዊ ሰልፎች የብዙ ሰው ህይወት የተቀጠፈባቸው፣ በመላ ሃገሪቷ የሸቀጣሸቀጦችና አገልግሎቶች እንቅስቃሴዎች የተገቱበት፣ በዚህም በክልሎች አንገብጋቢ የሆኑት መዋቅራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነት የተጋለጠበት ሁኔታ ነው። በ1991 ኤ.አ በመሣሪያ ሃይል መንግሥት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ በህወሃት ቁጥጥር ስር የወደቀው ሥርዓት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የሥልጣን ሞኖፖሊዎችን በማደራጀት በሌሎች ብሔሮች ላይ ጫናውን አሳርፏል። በህወሃት በኩል የፖለቲካ ሥልጣንና ሃብትን ለማጋራት ያለው እምቢተኝነት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ቁጣን የፈጠሩ የተቃውሞ ሰልፎች እያስነሳ ነው።(Ethiopia at an Ominous Crossroads, Jan. 02, 2018) በአብዛናዎቹ የ2017 ወራቶች ባለማቋረጥ የተካሄዱት የፖለቲካ ተቃውሞዎችና ግጭቶች መላ ኢትዮጵያን በማጥለቅለቅ በመንግስት አገዛዝ አቋም ላይ የተፈጠረውን ከፍተኛ ሥጋት እየጨመረ ነው። በገዢው ፓርቲ ውሰጥም ያለው የሥልጣን ትግልም ተጧጥፏል። ሁለቱ ፣ ማለትም በገዢው ፓርቲ ውስጥ እንዲሁም በገዢው ፓርቲ አባል ድርጅቶች መካከል የተጠናከረና ጭንቀት የተጠናወተው የሥልጣን ትግልና ሃገሪቷን ያዳረሱ ተቃውሞዎች በሥርዓቱ ህልውና ላይ ሥጋት ፈጥረዋል። መንግሥት በተለይ በአማራና ኦሮሞዎች ተቃውሞዎች ጥምረት ምክንያት የአስተዳደር ቁጥጥር በማጣቱ ከፍተኛ ሥጋት አድሮበታል። በተጨማሪም አለመረጋጋቱና ተቃውሞዎቹ ብዙሃኑን መሠረት ያደረጉ፣ ሥር የሰደዱና ከዚህም ሌላ የፖለቲካ አድማሱም በፍጥነት አየተስፋፋ መምጣቱ በሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋትን አሳድረዋል። እንደምዕራባውያን ታዛቢዎች ሁኔታው ትኩረት ካላገኘ ካለፈው በፍጥነት እየተባባሰ የሚቀጥል ነው። ይህም በሰሞኖቹ ተከታታይ ክስተቶች እንደታየው መንግሥት ተቃውሞዎቹን ለማንኮታኮት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ማሰሩን ከማመኑም በተጨማሪ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ለመፍታትና የእስረኞች ማሰቃያና በአስከፊነቱ የታወቀውን እስርቤት ለመዝጋት ዕቅድ እንዳለው ገልጾአል። በዚህም፤ “ብሔራዊ ዕርቅን በማራመድ ዴሞክራሲያዊ መድረኩን ለማስፋት” ጥረት አደርጋለሁ ብሏል። ይህ እንግዲህ ገና የሚታይ ነው የሚሆነው። እነማን እንደሚፈቱ ወይም መቼ እንደሚከናወን አስከ አሁን ግልጽ የሆነ ነገር የለም ። ይህ ጽሁፍ በተዘጋጀበት ጊዜ ( Jan. 8/2018) የፖለቲካ እስረኞች የሚባሉት የትኞቹ እንደሆኑም ብዥታ አለ። የመንግሥት አካሄድ እርስ በርሱ … ሙሉውን ለማንበብ ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
__
ማስታወሻ : ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ ይላኩልን editor@borkena.com , info@borkena.com

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,121FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here