spot_img
Tuesday, November 28, 2023
Homeአበይት ዜናበኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ደንገዝገዝ...

በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ደንገዝገዝ ያለ መልዕክት አስተላለፉ

advertisement
ሬክስ ቲለርሰን
ሬክስ ቲለርሰን ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ
ምንጭ: ፋና

ቦርከና
የካቲት 28 2010 ዓ ም

በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በሃገር ውስጥ ላሉ ጋዜጠኞች ከወርቅነህ ገበየሁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እንደወትሮው የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ አቋም ደንገዝገዝ ያለ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል።

ሁለተኛው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ገደማ እንደታወጀ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ካወጣው “ጠንከር ያለ” በተባለለት መግለጫ መነሻነት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳ አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ ተብሎ ቢጠበቅም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጠር አርጉት በሚል በለሆሳስ አልፈውታል።

በተጨማሪም “ዲሞክራሲ ሂደት ነው፤ ጊዜ ይወስዳል” በሚል አስተያየት ለ27 ዓመት ስልጣን ላይ የነበረውን ቡድን መታገስ ያስፈልጋል የሚል አንድምታ ያለው መልዕክትም አስተላልፈዋል። የአፍቃሪ ህወሓት ተሟጋቾች እና ደጋፊዎች መጀመሪያ ሬክስ ቲለርሰን ነገር ሊያመጡ ይችላሉ የሚል ስጋት የነበራቸው ቢሆንም ፤ የዛሬውን ንግግራቸውን ከሰሙ በኋላ እፎይታ እንደተሰማቸው በማህበራዊ ድረ ገጽ ከሚያስተጋቧቸው መልዕክቶች መረዳት ይቻላል።

ሬክስ ቲለርሰን ከወርቅነህ ገበየሁ በተጨማሪም ስልጣን ለመልቀቅ ከጠየቁት ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና ስመጥሩ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሰርጌ ላቭሮቭ ለኦፊሲየላዊ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጉብኝታቸው የመቶ ሃያ ዓመት እድሜ ባለው የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ግንኙነት ላይ ያተኩራል ተብሏል። ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ፤ በግብርና እና በጤና ትብብር ከማድረግ በተጨማሪም ለሰማላማዊ ግልጋሎት የሚውል የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባትም ፍላጎት እንዳላት እየተነገረ ነው።
__
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here