advertisement
ቦርከና
መጋቢት 2 2018
ትላንት የመንግስት ታማኝ ወታደሮች በኢትዮጵያ ኬኒያ የድንበር ከተማ ሞያሌ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ሞተው ከአስራ ሁለት በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ የተሳሳተ መረጃ ይዘው በነበሩ የመከላከያ አባላት የተፈጸመ ነው ብሎ አምስት ወታደሮች እና አንድ ሻለቃ ትጥቃቸውን ፈተው በምርመራ ላይ እንደሆኑ አሳውቋል። የተሳሳተ የተባለውን መረጃ ማን እንደሰጣቸው የተገለጸ ነገር የለም።
የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ግን ሆነ ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት እንደሆነ ይናገራሉ። የተገደሉት በአብዛኛው ወጣቶች ሲሆኑ ከሟቾቹ ውስጥ አንደኛው አቶ ተማም ነጌሳ የተባለ በዛው በሞያሌ ባለ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር እንደነበረ ታውቋል።