
ምንጭ ፤ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ
ቦርከና
መጋቢት 3 2010 ዓ ም
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ የህወሓት መንግስት ታማኝ ወታደሮች በኢትዮጵያ የድንበር ከተማ ሞያሌ ላይ አስር ያህል ሰዎችን ከገደሉ እና በርካቶችን ካቆሰሉ በኋላ 50,000 የሚሆኑ የከተማው ነዋሪዎች አጋዚ ተጨማሪ ስጋት ሊፈጥር ይችላል በሚል ስጋት ወደ ጎረቤት ኬኒያ መሻገራቸው ተሰምቷል። እስካሁን ባለው መረጃ መረሰት የተሰደዱት ኢትዮጵያውያን ያሉት በሞያሌ ኬኒያ ነው።
50,000 የኢትዮጵያ ሞያሌ ነዋሪዎች ወደ ኬኒያ ሞያሌ መሰደዳቸውን የኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሐንስ ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ አረጋግጠዋል። ከአንድ ቀን በፊት ከንቲባው ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኮማንድ ፖስት አንድ ሻለቃ ጦር ወደ ሞያሌ ኢትዮጵያ የላኩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች እንደገቡ መረጃ ስለደረሰኝ ነው ያለውን ሃሰት ሲሉ እንዳጣጣሉት የሚታወስ ነው። አብዛኛው ግድያ የተፈጸመው ሸዋበር ተብሎ በሚጠራው የንግድ እንቅስቃሴ በነበረበት አካባቢ እንደሆነም አስታውቀዋል። ድርጊቱንም አግባብ አይደለም ሲሉ ከንቲባው ኮንነውታል።
በኬኒያ የቀይ መስቀል ማህበር ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አዳደረገም ተሰምቷል።
የኬኒያ ሞያሌ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)ተዋጊዎች በስፋት የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይሄን ያህል ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በአንድ ጊዜ ኦነግ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ መሰደዳቸው ድርጂቱ አጋጣሚውን በወታደራዊም ሆነ በፖለቲካ አንጻር ሊጠቀምበት ይችላል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው።
__
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።