- Advertisement -

ምንጭ: ፋና
ቦርከና
መጋቢት 4 2010 ዓ ም
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሬክስ ቲለርሰንን ከስልጣን አንስተዋል። በምትካቸው የአሜሪካ የስለላ ድርጂት (ሲ አይ ኤ) ኃላፊ የሆኑትን ማይክ ፓምፒዮን ሾመዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ርምጃውን የወሰዱት ከሬክስ ቲለርሰን ጋር በአንዳንድ የፖሊሲ ጉዳዮች (ለምሳሌ በኢራን ጉዳይ) ልዮነት አለን በማለት ነው።
የስልሳ አንድ ዓመት እድሜ ያላቸውን የሲ አይ ኤን ምክትል ዳይሬክተር ጂና ሃስፐልን በሲ አይ ኤ ዋና ኃላፊነት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሁለቱም ተሿሚዎች በአሜሪካ ሴኔት ፊት ቀርበው መጽደቅ አለባቸው የኃላፊነት ቦታቸውን ከመያዛቸው በፊት። ጂና ሃስፐል ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ ባላቸው ዶሴ እስር ቤት እንጂ ሹመት አይገባቸውም የሚሉ ወገኖች አሉ።
__
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።