advertisement
ቦርከና
መጋቢት 8 ፤ 2010 ዓ ም
ባለፈው ሳምንት የእንግሊዝ መንግስት በእንግሊዝ ሃገር ተመርዟል ከተባለው ሩሲያዊ ጣምራ ሰላይ ሰርጌይ ስክሩፖል ጋር በተያያዘ ሃያ ሶስት የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከሃገሯ ማባረሯን ተከትሎ ሩሲያ ሃያ ሶስት የእንግሊዝ ዲፕሎማቶችን በማባረር አጸፋውን አንደመለሰች የሩሲያ የዜና ምንጭ “አር ቲ” ዘግቧል::
ሩሲያ በተጨማሪም በሩሲያ የሚገኘውን ብሪቲሽ ካውንስል መዝጋቷም ታውቋል:: እንግሊዝ የበጎ አድራጎት ነው የምትለው ይሄው ድርጂት በባህል ግንኙነት እና በትምህርት ጉዳዮች ላይ እሰራለሁ የሚል ሲሆን በተለያዮ ሃገራት እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል::
__
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።