ቦርከና
መጋቢት 16 2019 ዓ.ም
ዛሬ ለቡ በሚገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን አንዱዓለም አራጌን እና እስክንድር ነጋን ለመሸለም እና ለማመስገን በተዘጋጀ የግብዣ ስነ ስርዓት ፖሊስ በድንገት በመክበብ አንዱዓለም አራጌን እና እስክንድር ነጋን ጨምሮ አስራ ሁለት ያህል ሰዎች እንደታሰሩ ተሰምቷል።
እንደ ኢሳት ዘገባ የታሰሩት ጋዜጠኞች ፤ጦማሪዎች እና ፖለቲከኞች ዝርዝር የሚከለው ነው
፩) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
፪) ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመ ወርቅ
፫)ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
፬) አቶ አንዱዓለም አራጌ
፭) አቶ አዲሱ ጌታነህ
፮) ጦማሪ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ
፯) ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን
፰) ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
፱) ወይንሸት ሞላ
፲) ይድነቃቸው አዲስ
፩፩) ስንታየሁ ቸኮል
፩፪) ተፈራ ተስፋዬ
በገዢው ፓርቲ ማህበራዊ ደረ ገጽ ሰሞኑን የሚለቀቁ መልዕክቶች የህወሓት ቡድን ኢሕአዴግን እንደገና ሙሉ በሙሉ እደተቆጣጠረ የሚያመላክቱ እንደሆኑ እና ፓርቲው ወደ ቀደመ የጭቆና እና የአፈና አገዛዝ ለመመለስ መወሰኑን የሚያመላክቱ ናቸው የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች አሉ::
በተያያዘ ዜና ዛሬ በባህር ዳር ተመሳሳይ አፈና እና እስር የነበረ ሲሆን የዮኒቨርሲቲ መምህራኞች ጭምር አንደታሰሩ ታውቋል:: ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታየ ደንደዓ እንደታሰረ ይታወሳል::
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።