spot_img
Saturday, September 23, 2023
Homeአበይት ዜናየገዥው ፓርቲ ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ...

የገዥው ፓርቲ ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል

advertisement
Abiy Ahmed
ዶ/ር አብይ አህመድ

ቦርከና
መጋቢት 16 2010 ዓ ም

ከሳምንት በላይ በዝግ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየው የገዠው የኢህአዴግ ፓርቲ ምክር ቤት የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጂት ሊቀመንበር የሆኑትን ዶ/ር አብይ አህመድ የኢሃዴግ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ድርጂቱ ዛሬ በማህበራዊ ድረ ገጽ በለቀቀው መግለጫ አሳውቋል። በነበረው ምርጫ ተፎካካሪ የነበሩት የደህዴን ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። የብአዴን ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት እንዲቀጥሉ ወስኗል።

ተሰጠ በተባለው ድምጽ ዶ/ር አብይ አህመድ ከ180 ድምጽ 108 ያገኙ ሲሆን ሺፈራው ሽጉጤ ደሞ 59 ድምጽ እንዳገኙ ታውቋል። የኢሃዴግ ምክር ቤት 180 አባላት ያሉት ሲሆን የድርጂቱ አራት አባል ፓርቲዎች እያንዳንዳቸው 45 አባላት አላቸው። በዚህም መሰረት ዶ/ር አብይ ካገኙት 108 ድምጽ ውስጥ ከ60 ፐርሰንት በላይ ድምጽ ያገኙት ከኦህዴድ ፓርቲ ውጭ ካሉ የኢሃዴግ አባል ፓርቲዎች ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢሃዴግ ውስጥ በጎሳ ከተደራጁ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ብአዴን እና ኦህዴድ የህወሓትን ቅጥ ያጣ ተጽዖኖ ለመቀልበስ የትብብር መንፈስ ሲያሳዮ እንደነበር በተለያዮ ወገኖች ሲዘገብ ቆይቷል። ዛሬ ይፋ በሆነው የምርጫው ውጤትም የብአዴን ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።

የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ዛሬ ማምሻውን ምርጫውን በሚመለከት በማህበራዊ ድረ ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት የሚከተለውን ብለዋል ፤

    “የኢህአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ስብስባውን ሲያጠናቅቅ ዶክተር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ቀደም ብሎም የአቶ ኃይለማርያምን አርአያነት ያለው የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ አፅድቋል። በሂደቱ ብአዴን ለድርጅቱ ብቁ መሪ ለመምረጥ ይበኩሉን ሚና ተጫውቷል ። መላው የኢህዴግ አባላት እና የኢትዮጵያውያን ሁሉንም ሂደት ትዕግስት እና አስተዋይነት በተሞላበት ሁኔታ በመከታተል ለነበራቸው አስተዋፅኦ ክብር ይገባቸዋል።”

የዶ/ር አብይን በገዥው ፓርቲ ሊቀመንበርነት መመረጥ በአወንታዊ መልኩ የሚያዮ ኢትዮጵያውያን የመኖራቸውን ያህል ፤ መዋቅራዊ እና ሪዮተዓለማዊ ለውጥ በሌለበት ሁኔታ የዶ/ር አብይ መመረጥ የገዥውን ፓርቲ ፕሮግራም ከማስፈጸም የዘለለ ርባና የለውም የሚሉም ወገኖች አሉ።

ከውጭ ክህወሓት ቡድን ወደ ስልጣን መምጣት ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳው የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ የነበሩት ኸርማን ኮኸን የዶ/ር አብይን ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ቀደም ብለው ከተናገሩ “ተንታኞች” ግንባር ቀደሙ ናቸው።

ዶ/ር አብይ በውትድርና እስከ ሌተናል ኮለኔልነት ማዕረድ ደርሰው እንደነበር እና በርዋንዳም የተባበሩት መንግስታት ድርጂት ሰላም አስከባሪ አባል ሆነው እንደሰሩ ታሪካቸውን የሚያውቁ ይናገራሉ። በገዥው ፓርቲም ውስጥ በክልል እና በፌደራል ደረጃ በተለያዮ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።
___
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,676FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here