
ቦርከና
ሚያዚያ 29 ፤ 2010 ዓ ም
ትላንት በኢትዮጵያ ሞያሌ የድንበር ከተማ አካባቢ ደርሷል በተባለ የጎሳ ግጭት በርካታ ዜጎች መገደላቸው ተሰምቷል።
በኦሮሚኛ ተናጋሪዎቹ ቦርናዎች አና በሶማሊኛ ተናጋሪዎቹ ገሪ መካከል ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ እና ብዙ ህይወት የጠፋበት ግጭት እንደነበረ ቢታወስም ትላንት ያገረሸበት ምክንያት በውል አልታወቀም። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እስካሁን በጉዳዮ ላይ ያቀረቡት ዘገባ የለም፡፡
ኢሳት ግጭቱ በሶማሌ ልዮ ኃይል ታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት እንደተጀመረ ፤ የኦሮሞ ክልል ፓሊስ የአጸፋ ምላሽ መስጠቱን ገልጾ ከኢትዮጵያ ሶማሊ ፖሊሶች አምስት መገደሉን እና ከኦሮሞ ፖሊሶች በኩል ያለውን የሟች ቁጥር እያጣራ መሆኑን ገልጾአል፡፡
ግጭቱን ተከትሎ በርካታ ዜጎች ለህይወታቸው በመፍራት ወደ ጎረቤት ኬንያ መሰደዳቸውም ታውቁአል፡፡
ትላንት ባገረሸው ግጭት ባብዛኛው የተገደሉት ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትይጵያውያን መሆናቸውም ተሰምቷል።
የቀድሞ ፈደራል የመንግስት ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት የአሁኑ የኦሮሞ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ ዶር ነገሪ ሌንጮ ትላንት በማህበራዊ ድረገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በሞያሌ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ተቀባይነት የለሌውና የሚወገዝ ነው፡፡ ሃላፍነት የተሰጠዉ አካል አስፈላጕን እርምጃ ወስዶ ጉዳቱን ከወድሁ ማሰቆም አለበት ብለዋል፡፡”