spot_img
Wednesday, March 22, 2023
Homeአበይት ዜናከቤንሻንጉል ጉሙዝ በተፈናቀሉ አማራ ተወላጆች ጉዳይ የመስተዳደሩ እጂ አንዳለበት የሚጠቁም ሰነድ ተገኘ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በተፈናቀሉ አማራ ተወላጆች ጉዳይ የመስተዳደሩ እጂ አንዳለበት የሚጠቁም ሰነድ ተገኘ

- Advertisement -

Benshangul

ቦርከና
ግንቦት 1, 2010 ዓ.ም.

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ተብሎ በተዋቀረው የኢትዮጵያ ክፍል “አማራ ናችሁ ወደ ሃገራችሁ ሂዱ” በሚል ወከባና ፤የንብረት ማውደም በደል ከደረሰባቸው በኋላ ከአምስት መቶ የሚበልጡ አባወራዎች ወደ ባህርዳር በመሸሽ በቤትክርስቲያን ተጠልለው እንዳሉ መዘገቡይታወሳል፡፡

የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን በቤንሻንጉል ክልል የብአዴን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው የተባሉትን አቶ ተመስገን ኃይሉን በማነጋገር በጉዳዮ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ሞክሮ ነበር፡፡

አቶ ተመስገን አንደሚሉት በቅርቡ የተከሰተው መፈናቀል በጥቅምት ወር በሁለት ሰዎች ግጭት ምክንያት ተከስቶ በነበረ ችግር ምክንያት ስጋት የገባቸው ሰዎች ከዚያን ጊዜ በኋላ በተለያዮ ጊዚያት እየተፈናቀሉ ወደ ባህር ዳር መምጣታቸውን ለማስረዳት ሞክረው ነበር፡፡

ሆኖም ዛሬ በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው አማካይነት በማህበራዊ ሚዲያ ተለቀቀ ነው የተባለ ሰነድ እንደሚያሳየው በቤንሻንጉል ክልል ለበሎ ዴዴሣ ነዋሪ የነበሩ የአማራ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ፤ የማይወጡ ከሆነ በግዳጂ አንዲወጡ እንደሚደረግ በቀበሌ አመራሮች ትዕዛዝ እንደተላለፈባቸው ያሳያል፡፡

በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን እልቂት የሚቃወሙ የመብት ተሟጋቾች ሰነዱ በአማራ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እንደተፈጸመ አስረጂ ነው ይላሉ፡፡

ከዚህ በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ይኖሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አማሮች ናችሁ በሚል በአቶ ሺፈራው ሺጉጤ ትዕዛዝ ተመሳስይ በደል ደርሶባቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉ ይታወሳል፡፡

በቤንሻንጉል ክልል መስተዳደር ሾልኮ የወጣ ነው የተባለው ደብዳቤ ከላይ በፎቶ ያለውን ይመስላል፡፡

———
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,440FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here