advertisement
ቦርከና
ግንቦት 3 2010 ዓ ም
የፌደራሉ ጠቅላይ እቃቢ ህግ ሲዊድናዊ ዜግነት ያላቸውን የልብ ቀዶ ህክምና ሃኪም ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የሌሎች 61 ተከሳሾችን የክስ ሂደት ማቋረጡን አስታውቋል። ሰሞኑን በነበረው ችሎት ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተወሰነባቸው አብዛኞቹ ክሳቸውን እንዲከላከሉ ተበይኖባቸው እንደነበር ይታወሳል። ተከሳሾቹ ባለፈው አመት በቅሊንጦ እስር ቤት በተነሳው የእሳት አደጋም ጋር በተያያዘ ተወንጂለው ሲንገላቱ እንደነበር የሚታወቅ ነው።
“ሰው በመግደል” የተወነጀሉ አራት ተከሳሾች ግን ክሳቸው እንዳልተቋረጠ እና እንደሚከላከሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ኢዜአ ዘግቧል።
በቅርቡ ጊዜ ከተለቀቁ የፖለቲካ እስረኞች ተሞክሮ የክስ ሂደት ከተቋረጠ በቀናት ውስጥ እስረኞች ሲለቀቁ ተስተውሏል። ዛሬ ክሳቸው የተቋረጠላቸው የፖለቲካ እስረኞች ገና አልተለቀቁም።