- Advertisement -
ምንጭ :ኢትዮጵያን ሪፖርተር
ቦርከና
ግንቦት 8 2010 ዓ ም
በኦሮሚያ ክልል በአዳበርጋ ወረዳ ኢንጪኒ አካባቢ የዳንጎቴን ሲሚንቶ ፋብሪካን በዋና ስራ አስካሂጅነት የሚመሩት ዲፕ ካማራ ሹፌራቸውና እንዲሁም የ ሶሰት ልጆች እናት የሆነችው ጸሃፊያችው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ታውቌል ፤ በሃገር ውስጥ ያሉ ዜና ተቋማት እንደዘገቡት።
ኮማንድ ፖስቱ ለመንግስት ቅርበት ላላቸው መገናኛ ብዙሃን የሲሚንቶ ፋብሪካው ስራ አስኪያጂ እና ሁለት ኢትዮጵያዊ የስራ ባልደረቦቻቸው መገደላቸውን አረጋግጦ ያልታወቁ ያላቸውን ገዳዮች በማደን ላይ ነኝ ብሏል፤ ከህብረተሰቡም ትብብር ጠይቋል።
ፋብሪካው ከአዲስ አበባ 90 ኪሎ ሜትር ርቅት በአዳበርጋ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ስራ ከጀመረ ሶስት አመታት ገደማ ሆኖታል።