- Advertisement -
ከትንሳዬ ኢትዮጵያ
ግንቦት 9 2010 ዓ.ም
መወጠን መባከን
ጭንቀቴን መፍተሉን
ሃሳቤን ማርዘሙን
ይሆን አይሆን ብዬ
መዛወር መዳወሩን
ማርዘም መቆለሉን
ይብቃኝ ማቀርቀሩ
ቋጭቼ ልልበሰው
ሃሳቤን ባጭሩ
ዛሬ አየናት ብለው ነገ የለችም ካሉ
ነገ ማለት ልተው ዛሬ ነው ነገሩ፡፡
እኔ ልምከራችሁ እንዲህ ነው ዘመኑ
ጥንስስ አትጠንስሱ
ትኩስ ትኩስ ኑሩ
እቅድ አታርዝሙ
ጠብም አትጫሩ
ቂምም አታዳፍኑ
ቀና ቀና አስቡ
ታጠቡ ታጠኑ
ደህና አደርክ ተብሎ
ደና እደር ከቀረ
አሁን አሁን ኑሩ
ነገን አትመኑ፡፡
መጣጥፍ ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በeditor@borkena.com ወይንም በ info@borkena.com ይላኩልን።