
ፎቶ : ከብሩክ አብጋዝ ገጽ የተገኘ
ቦርከና
ግንቦት 23 2010 ዓ.ም
ባለፈው ወር በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለአግባብ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን በመፈታት ረገድ ጥሩ ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ የገዢው ፓርቲ ሃገራዊ መግባባት የመፍጠር አጀንዳ መጠነ ሰፊ የሆነ ተግዳሮቶች እየተስተዋለበት ነው።በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሞው የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ዘር እየተቆጠረ ጥቃት እንደደረሰባቸው እና ከቤት ንብረታቸውም እንደተፈናቀሉ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው።
በተለይ በኦሮሞው የኢትዮጵያ ክፍል ለብዙ አስርት አመታት የኖሩ የወሎ አካባቢ የአማራ ተወላጆች ላይ ከኢሉባቦር አካባቢ በግፍ የማፈናቀል ርምጃ ተወስዷል። በእርግጥ ከጉዳዮ ጀርባ ማን እንዳለበት በዚህ ሰዓት በውል የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም የለማ መገርሳ አስተዳደር የተፈናቀሉትን ወደ ቦታቸው ለመመለስ የወሰዱት እርምጃ እንዳለ እስካሁን አልተሰማም።
በጉዳዮ ዙሪያ ብሩክ አበጋዝ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል።
___
በኦሮሚያ ክልል በቅርቡ የሚካሄደውን መፈናቀል የሚያሳይ አጠቃላይ ዝርዝር ሪፖርት
—————————————————-
የኦህዴድ ሰወች አንድነትን እና ፍትህን ስትሰብኩ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የደገፋችሁ ለሁሉም ወገንና ዜጋ የተሻለ ነገር አላችሁ በማለት ነው። በኦሮሚያ ክልል በተለያየ ቦታ የሚደርሰውን የአማራወች ማፈናቃል ውሰብሰብ በሆነ መልኩ ሲካሄድ ስለ ሁኔታው ማብራርያ ለመስጠት አለመቻላችሁ ሁኔታውን ግራ የሚያጋባ አድርጎታል። በክልሉ ውስጥ ለሚፈጠመው ነገር የክልሉ መንግስት መልስ ሊሰጥበት የሚገባ ቢሆንም ዝምታን መርጧል። እየደረሱን ያሉት መረጃወች የሚያሳዩት በአካባቢው አክራሪ ቡድኖች አማራው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተሰባጥሮ በሚኖርባቸው ቦታወች ላይ ትኩረት አድርገው ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ነው፤ ማፈናቀሉም የዚያው ውጤት መሆኑን ነው።
.
የሆኖ ሆኖ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ራያ ቆቦ የተመለሱ ዜጎች ቁጥር አሁን ባለን መረጃ መሰረት ወደ 500 ደርሷል፡፡ ይኼ ቁጥር በራያ ቆቦ ያሉትን ብቻ የሚያሳይ ሲሆን በሌሎች የሰሜን ወሎ አካባቢወች በተመሳሳይ የተፈናቀሉትን ቁጥር አያካትትም። ተፈናቃዮቹ ቤት ንብረታችን ተቃጥሏል ይላሉ፡፡ በመንገድ ላይ የወለዱ እናቶች፣ ሚስቱ ስትወልድ ምንም ማረግ ባለመቻሉ ትቶ የመጣ ባል፣ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ህጻናት እንዲሁም እድሜያቸው የገፋ አዛውንት ይገኙበታል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እያደረገ አለመሆኑን ለማወቅም ችለናል።
.
የራያ ቆቦው Yasin Mohamed Ali በቤተሰቡ ጭምር የደረሰውን ነገር በማውሳት መፈናቀሉን በተመለከተ ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልጠዋል።
“ለመጤና ስደተኛ” ነዋሪዎቹ ቀን ቀን ሰላም ነው። ማንም ማንንም አይነካም! ቀኑ ቀንቶ አይቀርምና ይመሻል! ማታ የታጠቁና የተደራጁ ወጣቶች እንዲሁም የጸጥታ አካላትም ጭምር ሆሆሆ ብለው ወደ “መጤዎቹ” ቀበሌ ይመጣሉ። ነዋሪውን ሁሉ ተራ በተራ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ቀጭን ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ አከባቢዎች ይኖሩ የነበሩ በርካታ የራያ ተወላጆች ከዚህ አመት መጀምሪያ ጀምሮ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉና እጅግ በርካሽ ዋጋ እየሸጡ ተፈናቅለዋል። ምንም እንኳን አሁንም በክልሉ በርካታ ወንድም እህቶቻችን እየኖሩ ቢሆንም የተፈናቃዮቹ እጣ ፋንታ እንደማይደርስባቸው ማረጋገጫ የለም።
.
“መጤዎቹና” “ነባሩ” ነዋሪ በአኗኗርም ይሁን በባህል መተሳሰር ቀርቶ በመንደር አመሰራረታቸው ሳይቀር ለየብቻቸው የሚኖሩና “እኛና” “እነሱ” በሚል አጥር በአይነ ቁራኛ የሚተያዩ ናቸው። ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሊማሩ ቀርቶ በኦሮምኛም ለመማር ሁኔታዎች አዳጋች ናቸው። ይሄም መሆኑ ከአማራ ክልል በሰፈራ ሄደው ኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ወገኖች ልጆቻቸው ከዘመናዊው ቀለም የራቁ፣ ከአብርሆት የተፋቱ መሃይም “ሃብታም” አርሶ አደሮች ወይም “ነጋዴዎች” ናቸው። ለአብነት ያክል የአባቴን ታናሽ ወንድም የሲራጅ አሊን ቤተሰብ ታሪክ መመልከት ይቻላል። ሲራጅ በ1985 ኣ.ም ራያን ለቆ ወለጋ ደንቢ ደሎ ገባ። ደንቢ ደሎ ለግብርና ስራ እጅግ ምቹ ነውና ስመ-ጥር ሃብታም የሚባል አርሶ አደር ለመሆን በቃ። ስድስት ልጆችን ወለደ። ሲራጅ ከ1985 አም – 2008 ደንቢ ደሎ ኖረ።
.
24 አመታትን የኖረበት አከባቢ ደንቢ ደሎ ለሱ ከመጤነት ያለፈ ትርጉም አልነበረውም፣ አገሩ እንዳለ ሳይሆን ደቡብ ሱዳን እንደሚኖር አይነት የስደተኛነት እምነት አድሮበታል!! እንዲህ እንዲያምን ሁሉም ነገሮች አስገዳጅ ነበሩ። ቀንም ማታም በተጠንቀቅ ይኖራል፣ ታጥቆ ያርሳል፣ ታጥቆ ይተኛል። የሚያየው ነገር በሙሉ አስፈራው፣ የልጆቹ ነገር አሳሳው በመጨረሻም “የአገሬ ጅብ ይብላኝ” ብሎ ሃብቱን በሙሉ ሽጦ ሳይሆን ጥሎ ማለት ይቻላል ደንቢ ደሎን ጥሎ ቤተሰቡን ሸክፎ ራያ ገባ። አሳዛኙ ነገር ሁሉም ልጆቹ ቀለም ያልነካቸው “ሁሉም ህጻናት ወደ ትምህርት” የሚለው ዘመነኛ መሪ ቃል የራቃቸው ሆነው አገኘኋቸው። እንዴት አልተማሩም ብለው፣ “ስደተኛ ምን ይማራል፣ ማደጋቸውና እዚህ መድረሳቸው መቸ አነሰ? ሌላው ቅንጦት ነው፥ ሲቀጥል ሁኔታዎች በሙሉ ለኛ ልጆች የሚሆኑ አደሉም” አለኝ። ይሄ ምን ይነግረናል ቢባል እጅግ ብዙ ነገር ይነግረናል። የጉዳያችን ዋና ነጥብ መፈናቀል ነውና፣ የአባቴ ወንድም ሲራጅ 24 አመት የኖረበትን ወለጋ ለምን በዛ መንገድ ለቀቀ የሚለው ይሆናል?
መልስ አንድ
————–
ከኦሮሚያ ክልካዊ መንግስት ለነዚህ “መጤ” ለሚባሉ ወገኖቻችን አስተማማኝ የሆነ የደህንነት ዋስትና እንዲሰማቸውና አገራችን ብለው እንዲኖሩ የሚያስችል መድን አላገኙም። ይሄም በመሆኑ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት በተፈጠረ ጊዜ ጭንቀታቸው ያይላል፣ አንዳንዴም እድለኛ ካልሆኑና በግርግር ወቅት ከተገኙ ስሜት የሚነዳው “ዋና ነዋሪ” ለማእከላዊ መንግስቱ ቁርሾ ማብረጃ ያደርጋቸዋል። በነዚህ “መጤ” ተብለው በተፈረጁ ወገኖች ላይ ቀጥተኛና ተዘዋሪ ጥቃት ሲፈጸም አንገታቸውን ደፍተው ከማሳለፍ ባለፈ “ዜጋ ነኝ” ብለው በእኩልነት ለመዳኘትና ፍትህ ለማግኘት አዳጋች ሁኔታዎች ነበሩባቸው። ስለሆነም በውዴታ ግዴታ አከባቢውን ይለቃሉ ወይም ለቀቁ ማለት ነው።
መልስ ሁለት
—————–
ከኤሊባቡር ከተፈናቀሉ ወገኖች ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው የመፈናቀላቸው ምክንያት የተቀነባበረ የሚመስል ስልታዊ ግፍ ነው ። “ለመጤና ስደተኛ” ነዋሪዎቹ ቀን ቀን ሰላም ነው። ማንም ማንንም አይነካም! ቀኑ ቀንቶ አይቀርምና ይመሻል! ማታ የታጠቁና የተደራጁ ወጣቶች እንዲሁም የጸጥታ አካላትም ጭምር ሆሆሆ ብለው ወደ “መጤዎቹ” ቀበሌ ይመጣሉ። ነዋሪውን ሁሉ ተራ በተራ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ቀጭን ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። እርሻቸውን መሸጥም ይሁን መለወጥ አይታሰብም፣ ከብቶቻቸውንና ሌሎች ቋሚ ንብረታቸውን ገዥ እንዳያገኙ “ባዶ እጃቸውን ነው የመጡት ባዷቸውን ይውጧት” በሚል ስልታዊ መዝረፊያ መንገድ ይገፏቸዋል። መተኛት የለም፣ አባውራዎች በሚስትና ልጆቻቸው ፊት ይንገላታሉ፣ ይሰደባሉ።
———————————————
አሳዣኙ ነገር ይሄ ሁሉ በጨለማ ሲፈጸም አገሩ የጸጥታ ሃይል ያለበት አይመስልም። መንጋት አይቀርምና ሲነጋ ፖሊስና የጸጥታ ሃይላት ወደ “መጤዎቹ”ቀበሌ ይዘልቁና ማታ ምን እንደተፈጠረ እንዲያስረዱ በቁስላቸው ላይ እንጨት እየለቀቁ ይጠይቋቸዋል። ሲያደርቋቸውና ሲያቆስሏቸው ይቆዩና “ሚኒም ቺጊር አይሜጣም፣ የቻልንውን ኢናደርጋለን፥ እናንተም ጊን ቲቢቢር አድርጉ” ይሉና ጥለዋቸው ይሄዳሉ። ትብብር አድርጉ ማለት ውልቅ በሉ አይነት “ሆድ ሲያውቅ ዶሮን ማታ” እንዲሉ በአሽሙር ይነገራቸዋል። የልጆቻቸው ነብስ ያሳሳቸው ሃብት ንብረታቸውን ጥለው ወጡ፣ የመጣው ይምጣ ያሉ ባሉበት ዛሬም አሉ። ወንድም እህቶቻችን በኦሮሚያም ይሁን በሌሎች ክልሎች የመኖር ሙሉ መብት እንዳላቸው እነሱም አያውቁ፣ መንግስትም አያውቅ።
በእነዚህ ክልሎች “መጤ” የሚባሉት ዜጎች የመኖርና የመስራት ሙሉ መብት ቢኖራቸው ኖሮ ከበደልና ግፍ ባሻገር አብረው ከሚኖሩት ህብረተሰብ ጋር በተዋሃዱ ነበር፣ በተጋቡና በተዋለዱ ነበር። በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና ሰውነታቸው እንዲገለጥ፥ የአማራና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስታት የሚበጀውን ባበጁ ነበር። እንዲሁም የፌደራሉ ጎጠኛና አሻጥረኛ መንግስት አያሌ አሸማቃቂና አሳሪ ህጎችን ባወጣበት እጁ ለነዚህም ዜጎች የመኖርና የመስራት መብታቸውን የሚያረጋግጥበት ህጋዊ ዶሴ ድሮውኑ ባበጀ ነበር። ሃቁ፣ በዚች በስም ብቻ ባለች አገር ክልሎች አገር ሆነዋል። ክልላዊ ዜግነት እውን ሆኗል፤ አንድ ላይ ብንጠራም ተለያይተናል!! ልብ ያለው ልብ ይበል፣ በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ በመግፋት ዘላቂ ልእልና ማግኘት ከቶ አይቻልም!! ዶ/ር አብይ አህመድ ይህችን ጉዳይ አይንና ጆሮ ካልሰጧት የቱንም ያክል ደግ ቢሆኑ አገሪቱንና ዜጎቿን ከጥፋት አልታደጓቸውም!
===============================
ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ሰወች ሥም ዝርዝር በተወሰነ መልኩ ከጾታ እድሜ የቤተሰብ ብዛት አሁን ያሉበት የመጡበት ቦታ ጋር የሚያሳይ መረጃ Merid Abadi Sharew ያደረሰን ሲሆን መረጃው የተወሰኑትን ብቻ የሚገልጥና ከኦሮሚያ ተፈናቅለው በሀብሩ ሀሮ አካባቢ የሰፈሩትን ሰወች ዝርዝር አላካተተም። የሀብሩወቹን መረጃ ለማግኘት ገና ሙከራ እያደረግን ሲሆን የራያ ቆቦወቹ ወንድ ሴት ድምር ቀበሌ ወረዳ ዞን ወረዳ ቀበሌ እንደሚከተለው ነው።
1) ገዙ አያሌዉ ዳምጠዉ ወ 45 1 1 04 ቀቦ ቆቦ የመን
2) ብርሃን አሊጋዝ ሴ 40 2 1 3 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
3) አበበ ገጀማ ወ 45 1 1 01ቀቦ ዙሪያ ቆቦ ጋምቤላ .
4) አለሙ ይማም ወ 42 4 3 7 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
5) አሰፋ ይማም ወ 83 4 3 7 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
6) መሰለ ዝናቤ ወ 43 3 3 6 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
7) ጌታቸዉ ሰፊዉ ወ 23 1 2 3 01 ቀቦ ዙሪያ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
8) ጎሸ ደርቤ ወ 51 4 3 7 01 ቀቦ ዙሪያ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ ህጉ ኮፈደ .
9) ኩቢ ሃብቱ ወ 56 3 3 6 01 ቀቦ ዙሪያ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ .
10) ተካ ጫኔ ወ 35 1 1 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ .
11) ይማም መኮንን ወ 60 1 1 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ .
12) ሞገስ አራጌ ወ 39 1 1 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ .
13) በላይነሽ ዳርጌ ሴ 16 1 1 04 ቆቦ ቆቦ ቀለም ወለጋ ሰዲ ጫንቃ .
14) ይማም እንድሪስ ወ 45 2 2 4 03 ቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
15) ዘይነብ ሞላ ሴ 40 2 2 4 .
16) መሃመድ አደም ወ 50 2 1 3 .
17) ካሳዉ ጎሸ ወ 45 3 2 5 ቦኖ በደሌ .
18) ዘሃራ አድኖ ሴ 33 1 1 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
19) ኢብራሂም አህመድ ወ 40 1 1 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
20) አልማዝ ሽፈራዉ ሴ 30 1 1 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
21) ይመር አደም ወ 40 1 1 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
22) አሊ ሙሃመድ ወ 45 1 1 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
23) አማረ ሲሳይ ወ 57 4 1 5 04 ቀቆቦ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
24) ደርቤ አማረ ወ 42 1 1 2 ደንቢ ዳሎ .
25) በሪሁን በላይ ወ 58 3 1 4 01 አማያ ራያ ቆበ ደንቢ ዳሎ .
26) መለሰ ታደሰ ወ 45 2 1 3 04 ቆቦ ቆቦ ጅማ .
27) ይርጋ አድህነ ወ 43 5 4 9 033 መሃጎ ራያ ቆበ .
28) ሞገስ አያሌዉ ብሩ ወ 35 5 2 7 021 ቡሆሮ ራያ ቆበ ወለጋ .
29) ዘነብ በላይ አሊ ሴ 42 4 5 9 022 አፋፍ ራያ ቆበ ኤሊባቡር በደሌ .
30) ጀነቲ ሞላ ማም ሴ 39 5 4 9 022 አፋፍ ራያ ቆበ ኤሊባቡር በደሌ
31) አብደላ ይመር ደርቤ ወ 48 2 1 3 022 አፋፍ ራያ ቆበ ኦሮሚያ በደሌ
32) አበራ ሲሳይ ወ 50 5 4 9 041 አማያ ራያ ቆበ ኤሊባቡር .
33) አማረ ንጉስ ወ 42 6 3 9 041 አማያ ራያ ቆበ ኤሊባቡር .
34) መለሰ ያሌዉ ወ 38 2 1 3 019 ሚጦ ራያ ቆበ ኦሮሚያ ፈንታሌ .
35) ደሳለ እንግሊዝ ወ 52 2 3 5 044 ድቢ ራያ ቆበ ኤሊባቡር ገች አልጌ .
36) ሸዋየ ይመር ሴ 38 2 4 6 022 አፋፍ ራያ ቆበ ኦሮሚያ በደሌ .
37) ተመስገን ደሳለ ወ 42 3 3 6 044 ድቢ ራያ ቆበ ኤሊባቡር ገች .
38) ደምሌ ሞላ መንገሻ ወ 46 2 4 6 022 አፋፍ ራያ ቆበ ወለጋ ደንቢ ደሎ .
39) ዘዉድቱ ይማም ሴ 36 5 1 6 022 አፋፍ ራያ ቆበ ወለጋ ደንቢ ደሎ አዋግ ገላ .
40) ከድጃ አራጋዉ ሴ 50 3 1 4 022 አፋፍ ራያ ቆበ ወለጋ ደንቢ ደሎ አዋግ ገላ .
41) ሰለሞን ዘዉዱ ወ 54 2 2 4 021 ቡሆሮ ራያ ቆበ ወለጋ አልጌ .
42) ዋጋዉ ታደሰ ወ 45 3 2 5 015 አዋስ ራያ ቆቦ ሁመራ .
43) አብርሃ ሞገስ ወ 47 2 1 3 032 ቆባ ራያ ቆቦ ኦረሚያ በደሌ ገጌች .
44) ደባሽ ደሴ ወ 28 2 2 4 01 ቆቦ ራያ ቆቦ ወለጋ ሰሲቡ ስሪ ወለገልቲ .
45) መንገሻ ነጋሲ ወ 43 2 2 ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ደንቢ ዳሎ .
46) ሞገስ ባቤ ወ 36 3 1 4 ቆቦ ከተማ ራያ ቆቦ መተማ .
47) ስዩም ለገሰ ወ 37 2 2 4 ቆቦ ከተማ ራያ ቆቦ ደንቢ ዳሎ .
48) ተገኘ ትኩየ ወ 56 1 3 4 01 በዋ ራያ ቆቦ ወለጋ .
49) ወርቅየ አለሙ ሴ 45 2 3 5 04 ጃሮታ ራያ ቆቦ ጅማ .
50) አሰፉ ካሳ ሴ 56 3 3 6 ቆቦ ከተማ ራያ ቆቦ ነቀምት ደዳሌ ሰዲ አምባ 2 .
51) አሰፋ በሪሁን ወ 36 2 3 5 04 ጃሮታ ራያ ቆቦ ወለጋ ወለጋ .
52) ሞገስ በሪሁን ወ 45 1 1 04 ጃሮታ ራያ ቆቦ ወለጋ ወለጋ .
53) ገነት በሪሁን ወ 34 1 1 04 ጃሮታ ራያ ቆቦ ወለጋ ወለጋ .
54) ምናለ ገቤ ወ 45 4 2 6 01 ቀቆቦ መተማ መተማ .
55) እርጎ ፈንታየ ሰጠኝ ሴ 39 2 2 4 03 አዩብ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
56) ጃኖ ለገሰ ሴ 67 1 2 3 02 ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
57) ወርቁ ደርቤ ወ 56 1 2 3 02 ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
58) አሰፋ ጉበን ወ 45 3 3 6 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
59) ዋጋየ አለሙ ሴ 47 3 5 8 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
60) ነጋ መንገሻ ወ 34 1 2 3 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
61) ጣይቱ ጉበን ወ 45 1 3 4 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
62) ሻምበል ደስየ ወ 39 2 2 4 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
63) አየነ ደሱ ወ 35 3 3 6 03 ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ .
64) ያሲን ኑርየ ይማም ወ 45 3 2 5 040ገደመዩ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
65) ጀነቲ ይመር መንገሻ ሴ 56 1 1 2 040ገደመዩ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
66) ሰይድ ሰኒ በሽር ወ 43 3 2 5 040ገደመዩ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
67) ኩቢ መንገሻ ወ 47 3 4 7 040ገደመዩ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
68) አማረ ሰማዉ ትኩየ ወ 41 5 2 7 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ኤሊባቡር በደሌ .
69) ደስየ በየነ ጓንጉል ወ 45 3 3 6 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ኤሊባቡር በደሌ .
70) ገበያዉ ዱባለ ወ 34 4 4 8 044 ዲቢ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ አለም ተፈሪ .
71) አንጓች ዱባለ ሴ 45 3 4 7 044 ዲቢ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ አለም ተፈሪ .
72) ትኩ ሁሴን ወ 34 1 1 2 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ዳሌለዶ .
73) ኑርየ ትኩ ወ 37 1 2 3 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ዳሌለዶ .
74) አብዱ ትኩ ወ 38 1 1 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ዳሌለዶ .
75) መሪማ ትኩ ሴ 40 3 2 5 06 መንደፈራ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ዳሌለዶ .
76) ለምለም ጠቋሬ ሴ 34 6 2 8 03 አዩብ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ . .
77 ጉኒ እያሱ ሴ 45 3 4 7 044 ድቢ ራያ ቆቦ .
78) አበባ እያሱ ሴ 39 4 2 6 044 ድቢ ራያ ቆቦ .
79) ታክላ አለሙ ዳኛዉ ሴ 45 1 1 2 032 ቆባ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ጉቴ ጎዶ .
80) ደርበዉ ረደ ወ 47 2 4 6 04 ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ ደንቢደሎ .
81) ትግስት ደርበዉ ሴ 34 2 2 03 ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ ደንቢደሎ .
82) አረጋሽ ይማም ሴ 45 2 2 022 አፋፍ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ
83) ማሪቱ አያሌዉ ሴ 45 2 3 5 041 አማያ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ሚዛን ተፈሪ
84) በቀለ አባተ ወ 39 3 3 6 09 ራማ ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ ደንቢደሎ .
85) ወዳጅ አበበ ወ 37 4 1 5 01 ሮቢት ራያ ቆቦ ኦረሮሚያ ወለጋ ደንቢደሎ .
86) አድና አገዘ ሴ 40 4 2 6 01 ቆቦ ዙሪያ ቆቦ ከተማ ኦረሮሚያ ወለጋ ደንቢደሎ .
87) ሸንተሞ በላይ ሴ 40 1 2 3 035 መቅደላ ራያ ቆቦ ደቡብ ሞኮ
88) ሙሃመድ ጀማል ወ 47 2 2 4 022 አፋፍ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ኤሊባቡር ኖጳ
89) ስመኝ ዝናቤ ሴ 37 3 3 6 03 ቆቦ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ ኤሊባቡር መቱ
90) አበራ በላይ ሴ 45 3 3 6 035 መቅደላ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ኤሊባቡር ገች
91) አበበ ማርየ ወ 42 3 2 5 035 መቅደላ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ
92) በላይ ከበደ ወ 55 3 2 5 022 አፋፍ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ ሚዛን ቴፒ
93) ሃብታም ዋናዉ ሴ 35 3 3 6 020 ዱርለበስ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
94) አበበ አየነ ወ 71 1 2 3 012 ወረምኛ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
95) ካሳየ ሃሰን ወ 57 5 3 8 012 ወረምኛ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ .
96) አድና ጎሹ ሴ 60 3 3 6 020 ዱርለበስ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
97) ሞገስ መንገሻ ሴ 30 2 1 3 020 ዱርለበስ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
98) ደጀን ደርበዉ ሴ 43 1 3 4 020 ዱርለበስ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
99) አንጉታ ሰማዉ ሴ 38 1 3 4 020 ዱርለበስ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
100) ንጉስ ታደሰ ወ 22 3 1 4 04 ቆቦ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ ጅማ ደደሳ በፊት የመጣ
101) አበበ አየነ አበራ ወ 70 1 2 3 012ወረምኛ ራያቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
102) ካሳየ ሀሰን ወ 57 5 3 8 012ወረምኛ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
103) ወዳጆ አበበ ወ 30 2 2 4 012ወረምኛ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
104) አበባ ሲሳይ ሴ 35 4 1 5 022አፋፍ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
105) አበራ ደምሌ ወ 35 1 4 5 09ራማ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
106) ፍሬው ዝናቤ ወ 35 1 4 5 09ራማ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
107) ፈንታው ገላጋይ ወ 47 2 1 3 09ራማ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ
108) መንገግስቱ አንዳርጌ ወ 36 2 2 4 09ራማ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ወለጋ ጉሊሶ
109) መንግስቴ አበበ ወ 45 2 3 5 04ጃሮታ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ ኤሊባቡር
110) ገነት ተሾመ ሴ 42 2 1 3 040ገደመዩ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ አለም ተፈሪ
111) ደስየ ዉዱ ወ 44 1 1 04 ቆቦ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ ወለጋ ደንቢ ደሎ
112) አድሱ ሞላ ገበየሁ ወ 45 2 2 4 04 ቆቦ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ መቱ ደረኔ ወረቦ
113) ብርቱካን ዘለቀ ወ 37 2 2 4 04 ቆቦ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ ደንቢ ደሎ መቻሬ ከተማ
114) በየነ አያሌዉ ወ 43 3 1 4 04 ጃሮታ ራያ ቆቦ ኦሮሚያ በደሌ ገች
115) አንጓች ራሱ ሼ 32 1 3 4 03 ቆቦ ከተማ ቆቦ ከተማ ኦሮሚያ ወለጋ ደንቢ ደሎ
.
ተፈናቃዮቹ አሁን ያሉበት ሁኔታ
.
1) በአሁኑ ሰዓት በተፈናቃይነት የተመዘገቡ ከ480 በላይ ወገኖቻችን ሲሆኑ በየዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠግተው ይገኛሉ፡፡
2) የተፈናቃዮቹ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ እና ችግሮቻቸውም እየሰፉ መሄዳቸው።
3) የብርድልብስ እና ስንዴ እርዳታ እስካሁን 180 ለሚሆኑ ወገኖች ብቻ ነው ማዳረስ የተቻለው፡፡
.
ከዚህ መረዳት የምንችለው
.
1) የችግሩ መጠን እየሰፋ ሄዶ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት የመላውን ኢትዮጵያዊ አፋጣኝ ድጋፍ ይፈልጋል፡፡
2) ወገኖቻችን ካሉበት ሁኔታ አንጻር ፍጥነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
3) የሚደረገው ድጋፍ ሁሉን አቀፍ መሆን አለበት፡፡ የቁሳቁስ፣ የገንዘብ፣ ግፈኞቹን የማጋለጥ እና በሕግ እንዲጠየቁ የማድረግ፣ የጉልበት፣ የምራል እና የመሳሰሉትን
4) የወገኑ ጥቃት የማያመው ሰው የለም መቼም። በመሆኑም ሁሉም ሰው የበኩሉን ድርሻ ያበረክት ዘንድ የግድ ይለዋል፡፡
.
ለኦሮሚያ ክልል መንግስት ሁኔታውን እንዲያስቆም እንደ መፍትሄ የኦህዴድ አመራር ይሄንን በስውር የሚደረግ የማፈናቀል ተግባር ማሥቆም ከፈለገ በይፋ መግለጫና ማሳሰቢያ መስጠት አለበት። በክልሉ ለሚኖሩ ኦሮሞ ላልሆኑ ዜጎች ማንኛውም አካል በስውርም ሆነ በይፋ ለሚያደርገው የውጡልኝ ጥያቄ እምቢ የሚል ምላሽ እንዲሰጡና ይህ ነገር ሲገጥማቸው በቀጥታ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ወይም ጉዳዩን ለሚከታተል ኃላፊ ሪፖርት የሚያደርግ ከየማህበረሰቡ የተወከሉ ሠዎችን ማሥመረጥና የሚፈለገውን ቀጥተኛ የግንኙነት መሥመር መዘርጋት አለበት። ይኼን መመሪያም በክልሉ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ማወጅና ወደ ታች በማውረድ መመሪያውን ተላልፎ የማዋከብ ተግባር እየፈጠመ መሆኑ በተወካዩቹ የተጠቆመበት ሰው/ቡድን የሚወሰድበትን ህጋዊ እርምጃና ቅጣት በማሥቀመጥ ሁኔታውን ማስቆም ይቻላል።
.
የመገናኛ ብዙሀን ዝምታ
.
ለመሆኑ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ኤጂንሲ የሚባለው ተቋምስ በጉዳዩ ዙሪያ የሰራው ዘገባ ምንድን ነው? በአደባባይ ባንናገረውም ይኼ ተቋም ለምስራቅ አማራ ክፍል እንዳንታማ በማለት ከሚሰሩት ፕሮግራም በቀር ትኩረታቸው ደካማ ነው። ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ወደ ራያ ቆቦ የሄዱ ሰወች ወደ ሁለት ሳምንት በላይ ቢሆናቸውም ጉዳያቸውን ከተፈናቃዮቹም ሆነ ከሁለቱ ክልል መንግስታት ለማጣራት የሞከረ አንድም የመገናኛ ብዙሀን የለም። ይኼን እኛ ጠቁመናችሁ ሳይሆን ራሳችሁ አስባችሁ መስራት ይገባችሁ ነበር። ከእናንተ መረጃ ማግኘት ሲገባን እኛ መረጃ ልንሰጣችሁ አይገባም።
.
በመጨረሻም
.
የመንግስትም ሆነ የግል መገናኛ ብዙሀን ይኼን ጉዳይ ተከታትላችሁ የሚመለከተውን አካል ማብራርያ እንድትጠይቁ እንፈልጋለን።
===============================
ምስሉ የሚያሳየው ተፈናቃይ የራያ ሰወች በቆቦ ከተማ ጊዜያዊ ድጋፍ ሲደረግላቸው ነው። ነገር ግን የራያ ቆቦ ወረዳ ተፈናቃዮቹ ቁጥራቸው በመበርከቱ የሌላ አካል ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። ለእነዚህ ተፈናቃይ ወገኖች ማንኛውም በጎ አድርራጊ ግለሰብም ሆነ ተቋም የሚቻለውን ያክል ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግላቸው ለመጠየቅ እንወዳለን። መፍትሄው ሰወቹን ወደ ቀደመ ኑሮና ሕይወታቸው መመለሰ ብቻ ቢሆኑም እስከዚያው ችግራቸውንና እንግልታቸውን መጋራት ለነገ የማይባል ተግባር ነው።