spot_img
Saturday, September 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትየኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤የጉልበተኞች ታዛዥ እንዳይሆኑ ግን ምርጫው የርስዎ ነው። (አቢይ ኢትዮጵያዊ...

የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤የጉልበተኞች ታዛዥ እንዳይሆኑ ግን ምርጫው የርስዎ ነው። (አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

advertisement

ከ አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
ግንቦት 22 2018 ዓ ም

ዶክተር አብይ አህመድ በሥርዓቱ በሕውሃት የአጭበርባሪነት ተግባር ብዙ ንፁሃን ሰዎች በደም-ሥልጣን እንዲጨማለቁ አድርጎ “የለሁበትም” “ከደመ-ንፁህ ነኝ” በማለቱ ብቻ ስንቶቹ በተንኮል ከንቱ ሆነው ቀርተዋል፤ያበዱትንና አካለስንኩላን የሆኑትን ሳይጨምር።

የችግሩን ምንነት ተረድተን እና የሚደርስብንን መከራ ችለን የቻልነውን ያህል የሞከርነው፣እርስዎ አይሮፕላኑ ውስጥ እንዳሉትሉ የማይሰማዎትን ያህል መብረቅን የመሰለ የሕዝብ የሰቆቃ ድምፅ ከምድር ወደላይ”ዑኡ…ዑኡ”እያለ የግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ጣር ሲያስተጋባ እየሰማንና በአይናችንም ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ስለምናይ ነው፤ሕውሃት ኢሓድግን አምርረን የምንታገላቸው፤እርስዎ በፊርማ ኖሩበት፣አልኖሩበትም።

ይገርምዎታል የችግሩ ግዝፈት ቅጥ አትቶ፦”ሰረቀ” የሚባል ነገር የለም፤”ወደ ዘረፈ”ከተሸጋገረ እና እየባሰም ብሶ”በደም የተነከረ”ነው የሚለው እየበዛ ነው። “በመቶ ሺህ”የሚለው ቀርቶ፤”በሚሊዮን” የተለመደ ሆኗል፤ ብሶም”ብሊዮን አላቸው”የሚባሉትን መቁጠር ከጀመርን ሰነባበተ።

ይባስ እንዳይገርምዎት እነዶክተር መኮንንም ሆኑ እነዶ/ር ፍቅሬ ከስላሳ እና አርባ አመታት በላይ በየሆስፒታል አገልግለው፣እነረዳት ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ስንት ምሁራንን ያፈሩልን፣ሌሎቹም፣እነ እንጂነር እና መምህር አዕምሮ ፈረደ፣ሲስተር አያልነሽ፣እንዲሁም ነጋዴው አባባ ዘርጋው፣ስንቱ ተቆጥሮ ያልቃል ዕድሜ ልካቸውን ለሕዝብ ቀን ከሌት ጥረው ግረው በየሙያቸው ሕዝብን ሲያገለግሉ ያላገኙትን ገንዘብም ሆነ ንብረት፦የዘመኑ ዘራፊዎች ያላቸው ካፒታል ገንዘብና ንብረት ሲታይ ሰርተው ሳይሆን በሕገወጥ ለመምጣቱ ራሱ ሙስና በምሥክርነት ከመቅረብ በስተቀር ምንም ዓይነት ማስረጃ ነፃ ሊያደርጋቸው የሚችል ሊያቀርቡ አይችሉም።የሕዝብም ጥያቄ እና ትግል የሚያርፈው ይህንን ዝርፊያ “ዓይነ-ደረቅ ሌባ ቃጭል ይዞ እንደሚገባ” ዓይነት ጥፋት በደም የተለወስ በደል በሕዝብ አመፅ ለማስቀረት ነው፤ማንም ድግሞ ሕዝብን አይከለክለውም።እርስዎን አማላጅነት ባያመጡና በገላጋይነት በትግላችን ፊት ለፊት ባይደቀኑ ጋብ ብሏል። ንዴታችን ለጊዜውም ቢሆን በተለያዩ ቅርጾች መልክን በመቀያየር ማጭበርበር ይቻል ይሆናል፤ደጋግሞ የሚታለል ጅል-ሕዝብ ግን የለም፣የሆነውም ይሄው ነው።

እንደው ዶክተር አብይ አህመድ በእኔ ይሁንብዎትና ከአናት ጫፍ ጀምረን በኅላፊነት ላይ የነበሩትን፤”እኔና ባለቤቴ የምናገኛትን ደሞዝ አብቃቅተን ነው”ስትለን የነበረችው ፀረ-ሕዝብ የሙስና እናት ተብላ የምትጠራውና “ይህችን ያለችኝን ጃኬት…”እያለ ሲያፌዝብን በነበረው ወቸገሉ ዜናዊ አምስት ብሊዮን ዶላር ልጀምርና በዘመናችን ገንዘብ አላቸው ከሚባሉት መካከል የሕውሃት አባል ያልሆነ አለ? በፍፁም የለም።ሁሉምየሕውሃት አባል ከያንዳንዱ ችግረኛ ኢትዮጵያዊ ላይ፣ቢያንስ ዳቦ እና ውሃውን ዘርፏል።

በዚህ የዝርፊያ መሐል ነው እንግዲህ እርስዎ በሕውሃት ግማሽ አካል ተፈብርከው በሚሥጥራዊ መንገድ ለሥልጣን እንዲበቁ የተደረጉት።የወይዘሮ አዜብ ጎላ ማንነት ከእርስዎ አስተዳደግ ጋር ተመሳሰለብኝ፤እርሷም በልጅነቷ ወጥቤት ገብታ ትግራይን ለማስገንጠል ስትቀላቀላቸው ዕውነት የትግሬ ዘር የሆነች መስሏት እድሜ ልኳን ተጭበርብራ ያለወልቃይትነቷ እንዳደገች ያወቀችው በቅርቡ ሐቁን እና ታሪኳን የሚያውቁት በኢሳት ቀርበው አባቶች ሲያስረዱ ነው፣ ያመነችው። እርስዎም አባትዎ ያላመኑበትን ምክንያት ተገንዝበው አይመስለኝም፣ሕውሃትን ለትግል የተቀላቀሉት።ይሁንና እንዲያም አድገው የማያውቁዎት ሰዎች እስከዛሬም ከሕውሃት ግማሽ አካሉ አባላት”ይሄ ደግሞ ከየት መጣ?እኛን አይመስልም እንደኛም አይናገርም”ሲሉ፣አንድ አፍታ የበላኸውን ስታሳያቸው”ቧ!”ብለው ወዲያው ቤተመንግሥት አስገቡህና”እንግዲህ ይሄ ሁሉ ያንተው ነው፣ከወዳጆቻችን ጋር ሳይቀር ወዳጆቻችንን እንደ ጠላት ታግለናቸው ላንተ የታግለንልህ ይኸው ብለው” ወንበሩ ላይ አስቀመጡህ።እንግዴ ዕውነተኛ ታሪክዎ በአጭሩ ይኼው ነው።

እርስዎም”እማዬ ድሮም ሕፃን ሳለሁ ብላኛለች”ብለው ወዲያው ፊጥጥ አሉበት፤ከአገር ወደአገር፣ውጭ አገር ሳይቀር በረሩበት፤በሥልጣንዎ።የሚያደርጉት ንግግር የሕውሃት ጀሌዎችን በጠበጠ፣ጀሌ ድሮስ ምን ሥልጣን አለው? እንደውሻ ከመጮህ በስተቀር።”ዑኡ ዑኡ…አሉ፤”ሰሚ አጡ፤አስቸኳይ ስብሰባም ጠሩ ዶለቱ፡ማብራሪያ ተሰጣቸው፤ብላ..ብላ…ብላ…ሦስት ቀናት ሙሉ በተከታታይ ተደረገ፤”አልገባንም”አሉ።ሌሎች ቀናት ተደገሙላቸው፤”ብላ…ብላ…ብላ!!!” ገብቶናል አሉ፤ምንም የተለየ ነገር ሳይነገራቸው ስብሰባው ተገባደደ።እነሱም ለካስ”ቆሻሾች፣ብስብሶች ነበርን…”የሚል ሰፊ መግለጫ አውጥተው ስብሰባዎቹ ዳጎስ ባሉ አበሎች ተጠቅጥቀው፤አንዳንዶቹም አብበው ተጠቃለሉ።እርስዎ ግን ጉዞዎትን ቀጠሉበት።

አቤት ቤተመንግሥት ሊመለሱ ሲሉ የነበረው ግርግር፣በዓይነ-ሕሊና ይታየኛል።”ስማንዶ ብልዓላይ ግበሮ፤እንታዩ ምውስዋስ፣ዝብለካ.. አይተረዳአኒ …እወ!”አቤት ሩጫው፣”አቤሎ ሓጎስ? ሒቦም ንዘራይ…?ሕፀዎ…”በጀሃ አበይ ኬዶም ንሽፈራው ሓዌ?”አብዚያ ጠጠው በል…ተወዲዩ።”እርሶዎ ገቡ ከፅህፈት ቤትዎ፤ጠረጴዛዎን አቤት የሚፈረሙ ደብዳቤዎች ብዛት! ትዝ አለዎት አሁን”ምንድነው ይሄ? ጋሼ ሥዩም ተመልክተኸዋል?አልፈርመውም”ያሉት??? እና ኋላም ብፈርመውም ይዘግይና ይውጣ፣አደገኛ ሹመት ነው ተልዕኮዬን ያሰናክለዋል ማለትዎትን አስታወሱት?”እኔ እዚያ አልነበርኩም ከመረጃዎቼ ነው የምስልልዎት ጠንቋይ ሆኜ አይደለም።ከጉዞ ወደጽህፈት ቤትዎ ሲመለሱ ጭቅጭቅ እንደነበረ ይታወቃል ምን እምቢ ብለው እንደተጬቃጨቁበት ይፋዊ መረጃ አልነበረም፤ነገር ግን ያልተፈታ ነገር እንዳለ ታውቋል።

ጊዜውን ጠብቆ የነአዜብ ጎላ ሹመት እንደፈንጂ ወጥቷል፤ገና ሕዝብ ውስጥ አልፈነዳም፣ምክንያቱም ከፖለቲካ ጨዋታዎች አንደኛው ማዘናጋት በመሆኑ፣በአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የሹመቶችን መርዛማነት ሕዝቡ እንዳያይ አድርጎታል፤ሽቦዋ ስትላቀቅ መፈንዳቱ አይቀርም።ለዚህም የሕዝብ አመፅ መፈንዳት ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል እንጂ ማወናበድ ለወቸገል ዜናዊም አልረዳም፤ምክንያቱም ታሪክ እየረገመው ሊመዘግበው ጀምሯል።

ማስመሰል አያዋጣም፤ማወናበድ ትንሽ ያስኬዳል እንጂ፣አያዛልቅም፤መዋሸት ግን በየትኛውም መመዘኛ ቢታይ፣በአፍ ጢም ይከሰክስ እንደሆን ነው እንጂ በፍፁም አይጠቅምም።ከዚህ አንፃር ሕሊናዎት ዳኝነት ካልተቀመጠ እና ለሥጋዎት ካደሩ ነገ የእርስዎ የሚሆንበት መንገድ አይኖርም።በአሁኑ ጊዜ እያደረጉት ያለው በጎና መልካም ነገሮች ዋናው መሳሪያቸው፤ልሣንዎ እና ኢትዮጵያዊነትዎ ብቻ ናቸው።ተግባርዎ እየተጠበቀ ነው፤ማንነትዎን ለማወቅ ሕዝቡ ማጉሊያ መነፅር አስፈልጎታል።

መልካምነትዎ እንደተነገረው በተግባር ትክክል ናቸው፣እሳቸው ያሰቡት ያለምንም ሰምና ወርቅ አነጋገር ቀጥታ ታዛዥነታቸው ለሕዝብ በሕግ እንጂ ሕውሃት ለተባለው እጅግ በጣም ደግ፣አዛኝ፣ሰው እንዲገደል የማይፈልግ፣ለተራቡት የሚያዝን፣የሕብን መፈናቀል አጥብቆ የሚቃወም፤ፍትሕ ሲጓደል ማየት የማይወድ፣ ጉልበተኞችን እንጂ፣ሕጻናትንና አዛውንቶችን የማይገድል ድርጅት ነው ብለው ካመኑ ቤትዎ መስተዋት ይፈልጉና ራስነትዎትን ለማረጋገጥ ይሞክሩ።እኛ ግን ይኸው እንዳለን አለን።አሁን የደረስንበትም የትግል ደረጃ ሁለት ምርጫዎችን ብቻ የያዘ ነው፤ከሁለት አንዱ የመምረጥ።በታሪክ ምሳሌነት የታዋቂውን የእንግሊዝ ገጣሚና ደራሲው ባለቅኔ አቶ ተምዘግዛጊው ጦር(ሼክ ስፒር)ግጥምን አስታወሰኝ።አንዷ መስመር ነጠላ ስንኝ
“መሆን ወይም አለመሆን፣እዚህ ላይ ነው ችግሩ …።” ችግር የለም? ? ?

ዶክተር አብይ አህመድም በጥንቃቄ ያስተውላሉ ብዬ ሙሉ በሙሉ ተስፋ አደርጋለሁ፤ዕምነት ግን የለኝም፣ምክንያቱም ገንዘብና ሥልጣን የሚሰጡት ከሰይጣን በመሆናቸው ልብን ወዲያው ድንጋይ ያደርጉና ሕሊናን ቀፍድደው እንደሚይዙት ጠንቅቄ ስለማውቅ ነው፤ሆኖ ነው እንጂ ቢያንስ ወ/ሮ አዜብ ጎላን አያውቋትም ብዬ አላምንም።እናም ዛሬም እላለሁ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልምና ምርጫው የርስዎ ብቻ ነው፤ሕዝብ ወይስ መንግሥት?

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
———
ማስታወሻ: በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በeditor@borkena.com ወይንም በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,705FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here