advertisement
ቦርከና
ሰኔ 3፤2010 ዓ. ም
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ “የክልኩን እና የሃገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ እገመግማለሁ” በሚል አስቸኳይ ስብሰባ እንደጠራ ለድርጂቱ ቅርበት አለው የሚባልለት የፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ዘግቧል።
ድርጂቱ ስብሰባውን እንዳጠናቀቀ የገመገማቸውን ነጥቦች እና የደረሰበትን አቋም ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ከባድማ ጋር ተያይዞ ገዢው ፓርቲ ሰሞኑን ያሳለፈው ውሳኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ተገምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኡጋንዳ ወደ ግብጽ አቅንተው የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት ነው የህወሓት ማአከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የተጠራው። በዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹሙን ሳሞራ ዩኑስን በጡረታ አሰናብተው በምትካቸው ጀኔራል ሰዐረ መኮነንን መሾማቸው ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና ትላንት በኢሮብ ትግራይ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከአስራ ስምንት ዓመት በፊት ከኤርትራ ጋር በአልጀርስ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመቀበል ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ ለመስጠት የደረሰበትን ውሳኔ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።