ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
ሰኔ 11 2010 ዓ.ም
ሥር-ነቀል ለውጥን ከመጀመሪያው ለማወቅ፣ቢያንስ ዛፍ ቆረጣን መገንዘብ ይገባናል ።
“ዛፍም ሆነ እንጨት መቁረጥ በቂ ዕውቀት ይጠይቃል፤አለበለዚያ ያስከፍላል።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ፣ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፰ ይመልከቱ።”
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሥር-ነቀል ለውጥ መምጣት ከሃምሳ ዓመታት በላይ ውድ ልጆቹን ወድዶ ሳይሆን በግዱ፤ያለፈቃዱ በአምባገነኖች ክፋትና የሥልጣን(ሠይጣን)ፍቅራቸው በጭካኔ በየዘመኑ ገብሯል።ባለሥልጣኖቹ ግን በተረከቡት የሥልጣን ኮርቻ ላይ እየተፈናጠጡ፣የኢትዮጵያ ሕዝብን ክደዋል።ክህደታቸው ደግሞ ራሳቸውን አበልፅጓል፣ የሕዝቡን ንብረት እና ገንዘብ በረቀቀ መንገድ እንዲመዘብሩ አድርጓቸዋል፤ስለዚህም ድምጻቸውን አጥፍተውና አድራሻቸውን ቀይረው፣ወይ አገሩ ውስጥ ተደብቀዋል አሊያም ወደ እዚያ ተሰደዋል።
እነዚያ በየወቅቱ የተከሰቱት ለውጦች ወዲያው የተዘረፉ በመሆናቸው ውጤታቸውንም ሕዝብ ስላየ የጥገና ለውጥን ሕዝብ ዛሬም አይፈልግም።እናም በዚህም ትግል ደምና አጥንት የተከፈለው ለሥር-ነቀል ለውጥ እንጂ፣ የባለሥልጣኖችን ቁጥር በመከርከም እና ጉልቻ በመለዋወጥ ወጡን ለማጣፈጥ እንዲሚሞከር አይደለም።”በስብሰናል”በምን ቢባሉ በሥልጣን ላሉን፤ “ተጨማልቀናል”እንዴት ሲባሉ በሙስና ገንዘብ ባይሉም፦በራሳቸው ላይ ባይመሰከሩም እናውቀዋለን። መንግሥት ነን ባዮቹ ባለጊዜዎች ግን የሕዝቡ ጥረቱም ሆነ መስዋዕትነቱ “ለዛፍነት የበቃውን አረም”ከሥሩ መንግሎ ለመጣል መሆኑን ካልተገነዘቡ ትግሉ የመረረ ይሆንባቸዋል።
ዶክተር አብይ አህመድ በወጣትነታቸው”እማዬ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኛለች፤”ብለው፣በፅናት ያኔ ለሚጠራቸው አቤት ብለውና ተልከው፣ለሚነግራቸው ተሰብከው፣መጽሓፍቸውን አንብበው፣ትምህርት አነብንበው፣ጥርሳቸውን ነክሰው፣ ለዓላማቸው አጎንብሰው፣ዓመታትን ቆጥረው፣የሞት ሸለቆን አቋርጠው፣ከባንዳዎች ተቋጥረው፣በታዛዥነት ተላልከው፣ ወጥተው ወርደው፣ደክመው ለምነው፣ሰጥተው ተቀብለው፣ የሚፈለገውን የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለው ጫፍ ላይ ዙፋኑ አጠገብ ደርሰዋል፤ዙፋን የሚባል ሥም የለም እንጂ።
በነዚያ የመሆን ወይም የአለመሆን ውጣ ውረድ የግል ፈተና ኑሯቸው ዓመታት:- በህይወት ጉዞ ውስጥ ስለነበራቸው ታሪክ ለማንሳት ሳይሆን፣የትና እንዴት እንደተዘሩና እንዳደጉ ለማመላከት ብቻ ነው።አዎ አሁን እሳቸው አድገው የት እንዳሉ ከነማን ጋር እንደሆኑ ራሳቸውን በሚገባ አውቀዋል።በዚህ አጋጣሚ ጊዜ ነው ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ባለችበት ወሳኝ ወቅት የፈተናው መፍትሄ ለመሆን በሕዝብ ሳይሆን በፓርቲ(በራሳቸው የፖለቲካ ክፍል)ለማሟያነት በትግል የተመርጡት።ኅላፊነቱንም በመሃላ ተቀብለዋል፤በድብቅ ሳይሆን በግልፅ፣ ባደባባይ “የፓርቲዬ የኢሐድግ/ሕውኃት ተመራጭ እኔ ነኝ”ብለው በየክልሉ፣አልፎ ተርፎም በውጭ አገር ሳይቀር ሲሻቸው በኦሮምኛ፣ሌላጊዜ በትግርኛ፣አሊያም በፈረንጂኛ አፍ፣እያሉ በራሳቸው ልሳን “ቀይዋን ያየ!” እያሉ፣”እዩኝ!”ብለዋል።እኔ ግን አሁንም ለማየት አልፈለግኩም፤የጌታቸው ፀጋዬን የቀይ መስመሬን ካርድ ውጤት ሳላይ ካርዴን አልወረውርም፤የሺህዎች ነብሰ-ገዳይ ሰላቢ በመሆኑ።ምክንያቱም ነገሮችን በአንፃራዊነት ነው የማየው።ለምን ቢሉ ሁለት ጆሮዎችና ሁለት ዓይኖች ስላሉኝ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ያግዱኛል፦
አንደኛው ከአባባል ሀ/”የኔ ጥፋት በተሳሳተ ስሌት ባንተ ግዛት ውስጥ መወለዴ ነው፤”(To be born in your kingdom is a miscalculation.”የሚለው የአንድ ሊቅ አባባል ሲሆን፣ ዶክተር አብይ አህመድም የተፈጠረበት ድርጅትም ሆነ ቦታ የፈለገውን ያህል መልካም ሥራ ቢተገብርም የዜሮ ብዜት ውጤት መሆኑ አሳዛኝነቱ አመድ አፋሽ ስለሚያደርገው ነው፤የማይፈለግ የጉጅሌ ድካም ስለሆነ።ለ/ደግሞ መቅደም ያለበትን ስለመምረጥ ሲሆን፣ቢያንስ ከዜጎች የግለሰብ ነፃነት አንፃር በሁሉም በኩል እንድ ዓይነት ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች(ንግግርና ፖለቲካ ወንጀል ሆኖ ከተቆጠረ)በየትኛው ስሌት ነው በዳኝነት ወቅት የሚለያዩት?ነው ወይስ በፖለቲካ ከታሰሩት ውስጥ ሲፈቱ ጥቅም የሚያስገኙት ብቻ ናቸው የሚለቀቁት?!!!ፍትህ ግን አይደለም።
ሁለተኛው/ደግሞ የበለጠ ጥፋት እንዳይሰራ የሚፈፀመውን ጥፋት ወይ ለማስቆም አሊያም ራሱ ለማቆም
በአለመፈለግዎት ነው።
እነዚህም ሁለቱ ወደመረጃዎቼ ሲያያዙ ያስቀመጥኳቸው እርስዎን ለመደገፍ ያሉበትን ሁኔታ ባላውቅም የሕዝብ ጥያቄዎች መሠረታዊ የሆኑት፦
፩ኛ/እስረኞችን በሙሉ ማስለቀቅ፤ማስመሰል ነው:-አርባ እስረኞች እዚህ መቶ እዚያ ሺህ መልቀቅ ከአገር
ቤት ወዘተ ምን ለማለት ነው? በትንሹ የሚታወቁ የፖለቲካ እስረኞች ከስልሳ ሺህ በላይ ናቸው፣በዚህ ሁኔታ ነው መፈታት ያሉባቸው?ያውም ያልታወቁ ቦታዎች የሚሰቃዩበትን ቁጥር አይጨምርም።
፪ኛ/የሰላም እና የዕርቅ ጉባኤ እንዲጠራና በውጭሃገር የሚኖሩ ገብተው ኢትዮጵያ እንዲኖሩ ዋስትና እንዲያገኙ ማወጅ እና ከአገር ቤት ያሉትም ጉባዔ እንዲቀመጡ ለስብሰባ መጥራት ነበር፤ምንም አልተፈፀመም።ሌላው የማይነገር ነጭ ውሸት ነው።
፫ኛ/በከፍተኛ እና በአደገኛ ሁኔታ የኢትዮጵያን ገንዘብ ንብረትና ሐብት የዘረፉ ስላሉ አስቸኳይ ርምጃ ስለመውሰድ በሕዝብ የጥቆማ መሪነት እና በይፋ ተጠርጣሪዎች መልቀም የተፈፀመ የለም።እስከዛሬ ስንት እና ምን ያህል ንብረት እንደተጋጋዘ አይታወቅም።የምናውቀው የተጋጋዘ ነገር አባይ ፀሐዬ አስራ ሁለት ልጆቹን ከነቤተሰቡ አጓጉዟል፤ጌታቸው አሰፋም ሙሉ ቤተሰቡን አጓጉዟል፤ሌሎቹም ባለሥልጣናት እንደአቅማቸው አጓጉዘዋል፤የነዚህ ባለሥልጣናት መጥፋትም ሆነ ማጥፋት ተጠያቂው ዶክተር አብይ አህመድ መጀመሪያ እርስዎ ነዎት።የኢሕአድግም የተመረዘ ዛፍ እንደሆነ ውስጡ ሆነው ስለአዩት መበስበሱንና መጨማለቁን ባደባባይ መስክረዋል።በምን እንደተጨማለቀ በትክክል ማየት ባይችሉም በሰዎች-ደም እንደተጨማለቀ የሙታንን ሥም ዝርዝር በይፋ ላቀርብልዎት እችላለሁ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታጋሽ፣አስተዋይ፣ርህሩኅ መሆኑ ቢታወቅም ይህንን ባሕላችንን ከፍርሃት ቆጥረውት የደፈሯት ሁሉ ተደምሠዋል።እንግዲህ በዘመናችን ያለውን ሁኔታ በጥልቅ ስንመረምር የጉጅሌ ሥርዓት ከኢትዮጵያውያን ልጆች መካከል በትግሬ ክፍለሃገር በአድዋ አውራጃ ወራሪው “የጣሊያን ኢምፓየር”ነኝ ይል የነበረው የፋሺሽት መንግሥት በአፄ ምንሊክ የጦር መሪነት በውርደት ተሸንፎ ማቅ መልበስ ከጀመረበት የአድዋ ድላችን ማግሥት ተንኮሉ የተጠነሰሰው፣በራሳችን የባንዳ ልጆች ልብ ውስጥ ርኩሰት ተፈጥሮ በዕርጉምነት ባደጉ የፍሺሽት ጣሊያን አገልጋዮች የተተከለ የአረም ዛፍ ነው፤ብዙዎች ይህንን የኢትዮጵያዊነታችን ጠንቅ የሆነውን አላስተዋልነውም።ብዙዎቹ የአገራችን ማሕበራዊም ሆነ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የመጡት ከሮማውያን እና ከአረቦች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ከታሪክ ማጣራት ይቻላል።
እናም ይህ የፋሺሽቶች ዛፍ በመጀመሪያው ወረራ from 1895 to 1896. ጊዜ ተቆርጦ ቢገነደስም፣እንደገና ውስጥ ውስጡን አቆጥቁጦ ለሁለተኛ ጊዜ ከዓርባ ዓመታት በኋላ ተመልሶ በመውረር እንደገና October 1935 until 1939-1941 ፍፁም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣በመጥረቢያ በመቆራረጥ፣ በየመንገዱ ላይ ባደባባይ አርበኞችን ከመስቀል ጀምሮ፣የዓለም መንግሥታት ባልፈቀደው መርዝ ሕዝቡን በጅምላ በአይሮፕላን በመጠቀም በመቶሺህ የሚቆጠሩትን በመግደል፣አይነ ሥውራንና አካለጎደሎ እንዲሆኑ የተደረጉትን ሳንቆጥር፣ለቁምጥና እና ልዩልዩ በሽታዎች የተያዙት ሰዎች ብዛት ስፍር ቁጥር አልነበራቸውም።
በተለይም በነዚያ የፋሺሽት ጣሊያን አምስት ዓመታት October 1935 until 1939-1941 አርበኞችን በጅምላ አሰቅሎ በማስገደል በተገኘው ጊዜያዊ ድል የተዘሩት የበቀል ፍሬዎች፤የባንዳ የልጅ ልጆችን በመፈልፈል እስከዛሬም ድረስ ርኩሰታቸውን እነከደጃዝማች ጎላ(የአዜብ ጎላ አያት)፣እነሹምባሽ ዜናዊ አስረስ (የመለስ ወይም ለገሠ(ወቸገል)ዜናዊ አያት)ሌሎቹም አውርሰዋቸዋል።ይህ የባንዳ የልጅ ልጆች አረመኔያዊ-ባሕርይ ለሶስተኛ የትውልድ ጊዜ መልኩን ቀይሮና ፍጹም ኢትዮጵያዊ መስሎ ላለፉት አርባ አራት ዓመታት በነፃነት ታጋይ ሥም በተግባር ከነእርኩስነታቸው በልባቸው ውስጥ ተፈልፍሎ በኢትዮጵያ ሕዝብ ማሕበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ላይ ነቀርሳ ሆኖ ለአርባ አራት ዓመታት በሰዎች ደም ሲያሳድጉትና ሲንከባከቡት ዛሬ ዛሬ በቀላሉ የማይቆረጥ ርኩስት የሚፈለፈልበት ርጉም የአረም ዛፍ ሆኖ አድጓል።
ይህ ዕርጉም የገሃነም ዛፍ ሆኖ የዘረኞች ነቀርሳ-አስተሳሰብ መፈልፈያ ሆኖ ያደገው የጉጅሌ ሥርዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል እንዳሰቃየውና ሊ-ወ-ጣ ወደማይችልበት አዘቅጥ እንደከተተው ልንረዳ የምንችለው፣ክንዳችንን አጠንክረን ፈተናውን ተወጥተን ቁልቁል የመጣንበትን መንገድ ጥልቀቱን ተመልክተን ከአረሞች የጥፋት ባህርይ አንፃር ስናየው ብቻ ነው።ለውጣችን በፍፁም በበቀል መፈጸም የለበትም።
በዚህም ምክንያት ይህ በአረም ዛፍ የሚመሰለው ሥርዓት ከሥሩ ተነቅሎ በመመንገል ተቆርጦ መገንደስና መጎንደብ አለበት፤የቀረም ካለ ምሳር በላውም አልበላውም ምንም ሥሩ እንዳይቀር፣እንዳለፉት መከራዎች በይሁንታ መተው የለባቸውም፤እናም በመጨረሻው በሕዝብ ወላፈን መጋየት ይኖርባቸዋል።ይህንን የአረም-ዛፍ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ለመጣል በፖለቲካዊ ልሳን እንደሚባለውም ሥር-ነቀል ለውጥ ብቻ ሳይሆን ድምጥማጡን የሚያጠፋ ስነልቡናዊና ባሕላዊ መፍትሔ ያስፈልገዋል፤መፍትሄውም ይኼው ብቻ ነው።
ስለዚህም እያንዳንዳችን የዛፍን አቆራረጥ ማወቅ ይኖርብናል።ለምን ቢባል የባንዳ ጀሌዎች ቁጭ ብለው አይጠብቁንምና ቅርንጫፎቹ፣የግንዱ የላይኛው፣የመሃሉና በመጨረሻም ከነሥሩ ያለውን ግንዲላ እንደምንገነድሰው ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል፤አለበለዚያ ሥርነቀል ለውጥን ልናውቀው አንችልም።ከዚህ አንፃር በአንፃራዊነት የዛፍ አቆራረጥን ለማወቅ ምን ማድረግ እንደሚገባን በዝርዝር እንመልከት፤አምስት ነገሮች ያስፈልጉናል።
ሀ/በቅድሚያ ዛፍ ለመቁረጥ የሚያስፈልጉን መሳሪያዎች፣ የጦር መሣሪያዎች ከስለት እስከሚተኮስ ሌሎችንም አማራጮች ይጨምራል።
የአካል ልባሶች፣እጅጓንትን ጭምሮ፣ሞባይል ባይኖር እንኳን የጋራ መግባቢያ ምልክቶች
ከግዑዛን ዕቃዎች መጥረቢያ፣ገመዶች፣(ጫማዎች፣ፊትን መከለያ፣ወዘተ…በሠለጠኑት አገሮች)አካፋ።
ለ/ማስጠንቀቂያዎች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ ይገባል(የኤሌትሪክ መስመር፣ዕቃዎች፣ንብረቶች… አለመኖራ ቸውን)ዓለም-አቀፍ ሕጎችን ማወቅ ይገባል።
፩ኛ/ዛፉንና የአካባቢውን ሁኔታ ማየት በእያንዳንዱ ክልል ያለውን ሁኔታ በእርግጠኛነት ማወቅ።
፪ኝ/በየትኛው አቅጣጫ እንደሚወድቅ ማጣራት መጀመር ያሉባቸውን የትግል ሽምቅ ቦታዎች ማወቅ
፫ኛ/የዛፎቹን ቁመት የቅርንጫፎቹን ብዛት መገመት የባለሥልጣን ቤቶችን መለየት።
፬ኛ/ወደታች በመቆፈር ቀሪውን ከምድር ውስጥ ጉቶዎቹን መመንገል በውጭ አገር ያሉትን ደጋፎውችና ጀሌዎችን በተደራጀ መንገድ ማወቅ
፭ኛ/በእርግጠኝነት የተቆረጡትን በሙሉ ማሰባሰብ።እነማን ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን መዝግቦ መያዝ።
ማጠቃለያ:-
እንግዲህ “አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ያዢ”ነውና እንድናውቅ ይረዳናልና በዚሁ መሠረት ነው የሚፈፀመው።ዛፍ ሲቆረጥ ቅርንጫፎች እንደየውፍረታቸው በየደረጃቸው ከተቆረጡ በኋላ፣የሚቀጥለው መቆረጥ ደግሞ ከጫፉ ወደመሃል የመጣው ዋናው ግንድ ሲሆን፣ቀጥሎ ከስሩ በላይ የለው ግንዲላ ይሆናል፤በመጨረሻም ጉቶውን ከነሥሩ መንግሎ በማውጣት እንክትክት አድርጎ መቸፍቸፍ በየመልክ በየመልኩ ማስቀመጥና መደርደር ይጠበቅብናል።
ጥብቅ ማሳሰቢያ *** ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቅርንጫፎቹን ብቻ መመልመልና መቁረጥ ስሙ”መከርከም”ስለሆነ እና የካንሰሩን ዛፍ ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ እንጂ ከሥሩ ሳይነቀል በመቁረጥ ብቻ አንዳችም የሚረዳ አይሆንም። ይልቅስ አዳዲስ ቅርንጫፎች እንዲፈጠሩለት እገዛ ያደርጋል።
ዶክተር አብይ አህመድም ይህን ሐቅ ተቀብለው በጊዜ ጠቅላይ ሚኒሥቴርነቱን በሽግግር መንግሥት ለመተካት አሊያም ለሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሥልጣንዎን ቢያስረክቡ ሕዝብ እርስዎን በሚገባ ይመርጥዎታልና በሥር-ነቀል ለውጥ “የቀን ጅቦችን” ለማስወገድ እንድንግባባ! ! !እመክርዎታለሁ።
“ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!”
ትንቢተ ኢሳይያስ ም-፭ ቁ-፳
__
ማስታወሻ: በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በeditor@borkena.com ወይንም በ info@borkena.com ይላኩልን።