spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትሰፊው ህዝብና ጠባብ እድሉ (አሌክስ አብርሃም)

ሰፊው ህዝብና ጠባብ እድሉ (አሌክስ አብርሃም)

advertisement

(አሌክስ አብርሃም)
ሰኔ 12 2010 ዓ ም

ጨለምተኛ አትበሉኝና የአገራችን ፖለቲካ በተዋቡ ቃሎች እና ፖለቲካው ወይም ስርአቱ ሳይሆን የግለሰቦች በጎ ባሀሪ በፈጠረው በጎ አየር እና ተስፋ የተሞላ ፊኛ ነገር ይመስለኛል!! የሄን ፊኛ አምኖ አብሮ መንሳፈፍም ይሁን ይህን ጭላንጭል ላሳዩን ሰዎች ተገቢውን ክብር መስጠት ተገቢ ቢሆንም ያለቀለት መንግስት እና ስረአት ተቀይሮ አዲስ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተቋቋመ አይነት ፈንጠዝያ ግን አረፋ መጨበጥ የመስለኛል! ለምን? ምክንያቱም ይህን ፊኛ ጠቅ አድርጎ ማፈንዳት ይሚችል ጣት ከነፈርጣማ ክንዱ! አለ!!

ዛሬም የጦር ሃይሉ ከነጦር መሳሪያው የትላንቶቹ እጅ ውስጥ ነው!! ዛሬም ገንዘቡ ከነገዛቸው ተላላኪዎች የትላንቶቹ እጅ ወስጥ ነው!! ዛሬም ጥላቻውና የበቀል ሰሜቱ የጦር መሳሪያውና ገንዘቡ እጃቸው ላይ ባለው ስዎች ዘንድ ነው!እስኪ ለደይቃ እናስብ በዚህ ሁሉ ፍጅትና ጥፋት ሙስናና በደል በወቀቱ በቀጥታ ይመሩና ያዙ ከነበሩ ባለስልጣናት አንድ እንኳን የጠቅላይ ሚንስትሩን ሃሳብ ደግፎ የተናገረ ሰው አለ? በግልጽ እንደሚታየው ኩርፊያ ላይ ናቸው!! ጓዶች ይቅርታው ህዝብ በተቀበለው መሪ ይነገር እንጅ ከህዝቡ ከራሱ የመጣ ነው! ሰፊው ህዝብ ያ ጠባብ እድሉ እንዳይከተለው እፈራለሁ! ለምን እፈራለሁ ? ምክንያቱም የአገራችን ታሪክ የሚነግረን ታሪክ እየደገምን መሆኑን ነው!

ደርግ < <ኢትዮጲያ ትቅደም>> ሲል ድፍን አገር < <አሁን ገና ቆራጥ መሪ መጣ >> አለ ቆርጦ ቆርጦ ጣለን! ኢሀአዴግ 1997 አ/ም እንኩ ዴሞክራሲ አለን ልንቀበል የዘረጋነውን እጅ አስር አስር ገርፎ እጅ በደረት አስባለን !ግማሹ እጅ ላይ ካቴና አጠለቀበት !! ያውም ድፍን አለም በሚመሰክረው ሁኔታ በምርጫ ተሽንፎ ሌላዋን ካረድ መዘዛት! ጠብ መንጃ!! አለም አቀፉ ማህበረሰብ ካሽናፊ ጎን መቆም ልማዱ ነውና ትንሽ አጉረምርሞ ብድሩንም እርዳታውንም ቀጠለ!! ያች ጠብ መንጃ ዛሬም እነዛው ሰዎች እጅ ላይ ናት ቢበዛ የአመት ረፍት ወስዳ ቢሆን ነው!!

ዛሬም ወላ ጠቅላይ ሚንስትር ወላ ይህዝብ ተቃውሞና አለማቀፉን ማህበረሰብ ገፍትራ የደም ዙፋኗ ላይ ጉብ ላለማለቷ ስፊው ህብ ማረጋግጫው ምንድን ነው? ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ራሳቸው ማረጋግጫቸው ዋስትናቸውስ ምንድን ነው?

የደረስንበትን ከወደድነው እንደህዝብ < <ፕላን ቢ>> ማሰብ አዋጭ ነው ! አለበለዚያ ግን ሰፊው ህዝብ አገርን ታህል ነገር ለጠባበ እድሉ አሳልፎ መስጠቱ ነው!!

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here