- Advertisement -
ቦርከና
ሃምሌ 1 2010 ዓ ም
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን እና የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔን በመምራት ዛሬ ጧት አስመራ ገብተዋል። የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለአብይ አህመድ እና ለመሩት የልዑካን ቡድን ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የአስመራ ከተማ ነዋሪዎችም በአስመራ ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ለኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስተር ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ላለፉት ሃያ አመታት በመካከላቸው የነበረውን አለመግባባት ታሪክ ማድረግ ገንቢ የሆነ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ይከፍታሉ የሚል ትልቅ ተስፋ በሁለቱም ሃገራት ህዝቦች ይንጸባረቃል።
አቀባበሉን የሚያሳይ ቪዲዮ ከታች አለ