advertisement
ቦርከና
ሃምሌ 19 : 2010 ዓ. ም.
የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጂ በመሆን በታታሪነት ሲሰሩ የነበሩት ኢንጂንር ስመኘው በቀለ ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ተገድለው ተገኝተዋል።
አስከሬናቸው ያሽከረክሯት በነበረ ቪ ቲዮታ መኪና ውስጥ ከመስቀል አደባባይ ዋናው መንግድ ገባ ብሎ እንደተገኘም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀማል ዘይኑ ተናግረዋል።
አስከሬናቸው በጥይት መመታት ምልክት እንዳለበት እና በቀኝ እጃቸውም ሽጉጥ ይዘው እንደተገኙም አክለው ገልጥጸዋል። አስከሬናቸውም ለምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩ ታውቋል፥ፖሊስ ለምርመራው ይጠቅመኛል ያለውን መረጃ እንደሰበሰበ እና ምርመራው እንደተጠናቀቀም ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አሳውቋል።
የተቀናበረ ግድያ በሚመስለው በዚህ ድርጊት ቁጭት የገባቸው ኢትዮጵያውያን በመዲናዋ በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር የተቃውሞ ሰልፍ እንዳደረጉም ታውቋል።
የቦርከና ድረ ገጽ ዝግጂት በኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሳዛኝ ግድያ የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ይመኛል።
ቪዲዮ ምንጭ : የኢትይጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን